ዲቮሽን ቁ.18/2007 እሁድ፣ መስከረም 18/2007 ዓ.ም.
(በመጋቢ ተስፋሁን ሐጢያ)
(በመጋቢ ተስፋሁን ሐጢያ)
መልስ ይሰጣሉ! መልስ እንሰጣለን!
…ከእንግዲህ
በሚቀረው
ምድራዊ
ሕይወት
እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ
እንደ ስጋ ምኞት አይኖርም፡፡
አሕዛብ
ፈቅደው
እንደሚያደርጉት
በመዳራት፣
በስጋዊ
ምኞት፣
በስካር፣
በጭፈራ፣
ያለ ልክ በመጠጣት፣ በአስጸያፊ
የጣኦት
አምልኮ
የተመላለሳችሁበት
ያለፈው
ዘመን ይበቃል፡፡ ይህን በመሰለ
ብኩን ሕይወት ከእነርሱ ጋር
ስለማትሮጡ
እንግዳ
ሆኖባቸው
በመደነቅ
ይሰድቧችኋል፡፡
ነገር ግን በሕያዋንና በሙታን
ላይ ሊፈርድ ለተዘጋጀው መልስ
ይሰጣሉ
(1ኛ ጴጥ 4:1-5)
በምድር
ላይ ምን ያህል ዘመን
ቀርቶን
ይሆን? አንድ ቀን ብቻ?
አንድ ሳምንት ብቻ? አንድ
ወር ብቻ? አንድ ዓመት
ብቻ? አምስት ዓመት? አስር
ዓመት? ምን ያህል ጊዜ?
በምድር
ላይ የቀረልንን ዘመን በትክክል
አናውቀውም!
ነገር ግን፣ በሚቀረን ሕይወት
እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ
እንደ ስጋ ምኞት መኖር
እንደማይገባን
ይህንን
እናውቃለን፡፡
ቀድሞ የኖርንበት የዓለማዊነት ዘመን
ኑሮ እንደበቃው እናውቃለን፡፡ ያ ዘመን
ላይመለስ፣
ያ ሕይወት ላይከለስ፣ እንዳለፈ
እናውቃለን!
የዓለማዊነት
ኑሮ እንደበቃው፣ እንደተውነውና እንደጣልነው እናውቃለን!
ሰዎች በምድር ላይ ሲኖሩ
ምርጫ አላቸው – ወይ እንደ
እግዚአብሔር
ፈቃድ መኖር፣ አሊያም እንደ
ስጋ ምኞት መኖር፡፡ ለእውነተኛ
አማኞች
ግን እግዚአብሔርን እየመሰሉ ከመኖር
ሌላ ምርጫ የላቸውም፡፡ ለመንፈሳዊ
ሰው እንደ ስጋ ፈቃድ
የመኖር
ምርጫ አልተሰጠውም፡፡ ስለ ስጋ
ማሰብ ሞት ነውና፣ ስለ
ስጋ ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል
ነውና፣
በስጋ የሚኖሩ እግዚአብሔርን ደስ ሊያሰኙት
አይችሉምና
በስጋዊ
ልማድ እንዲመላለስ አልተፈቀደትም፡፡
መንፈሳዊ
ሰው እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ
ይኖራል፡፡
እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መኖር
ግን ዋጋ ያስከፍላል፡፡ መከራን፣ ነቀፋን፣
ስድብና
ስደትን
ያስከትላል፡፡
ቢሆንም፣
መንፈሳዊ
ይህን ገና ከጅምሩ አውቆ
ይገባበታል፡፡
በውሃ ጥምቀት ጊዜ ‹‹ከእንግዲህ
ለኃጢአት
ሞቻለሁ፣
ለጽድቅ
እኖራለሁ፤
ዓለማዊነትን
ጥዬ፣ ክርስቶስን ለብሼአለሁ፤ ሞቱን
ሞቼ፣ ትንሳኤውን እነሳለሁ›› እያለ
በሕዝብ
ፊት ቆሞ የሚመሰክረውም ለዚህ ነው!
አሕዛብ
ግን ፈቃዳቸውን እያደረጉ ይኖራሉ፡፡
በመዳራት፣
በስጋዊ
ምኞት፣
በስካር፣
በጭፈራ፣
ያለ ልክ በመጠጣት፣ በአስጸያፊ
የጣኦት
አምልኮ
ይመላለሳሉ፡፡
ነገር ግን ስለሚሰሩት ስራ፣
ስለሚያደርጉት
ነገር ሁሉ አንድ ቀን
ለጌታ መልስ ይሰጣሉ፡፡ ስለምኞታቸው፣
ስለመጎምኘታቸው፣
ስለአይን
አምሮታቸው፣
ስለዝሙታቸው፣
ስለነውረኛ
መዳራታቸው፣
ስለግብረሰዶማዊነታቸው፣
በጌታ ፊት ቆመው መልስ
ይሰጣሉ፡፡
ይህም ብቻም አይደለም፣ አሕዛብ
ዳግመኛ
የተወለዱ
አማኞች
በእነርሱ
ድርጊቶች
ስለማይተባበሩ
ያጠቋቸዋል፣
መከራ ያመጡባቸዋል፣ ችግር ያበዙባቸዋል!
እውነተኛ
አማኞች
በምድራዊ
ኑሮአቸው
እግዚአብሔርን
እየመሰሉ
ሊኖሩ ስለሚወድዱ ያሳድዷቸዋል፡፡ የኃጢአትን መንገድ
ስለሚጸየፉ
ይሰድቧቸዋል፡፡
ዓለማዊነትን
ስለሚንቁ
ያዋርዷቸዋል፡፡
ለስማቸው
ክብር፣
ለስጋቸው
ጥቅም የሚሰጡ ነገሮችን ስለሚንቁ
አሕዛብ
በአማኞች
ላይ ይስቁባቸዋል፣ ይሳለቁባቸዋል፡፡ ነገር ግን
ስለዚህ
ስራቸው
ሁሉ አንድ ቀን ወደ
እግዚአብሔር
ችሎት ይቀርባሉ፡፡ በሕያዋንና በሙታን
ላይ ሊፈርድ ለተዘጋጀው መልስ
ይሰጣሉ፡፡
እኛም አይቀርልንም! በዚህች ምድር
ላይ እንዴት እንደኖርን፣ እንዴት
እንደተመላለስን
በሕያዋንና
በሙታን
ላይ ሊፈርድ ለተዘጋጀው መልስ
እንሰጣለን!
ስለ ሰራነው ስንፍና፣ ስለጣልነው
ቅድስና፣
ስለ ቀዘቀዘው ፍቅር፣ ስለ
ደከመው
ስነምግባር፣
ስለ ክርክራችን፣ ስለ ፍጭታችን፣
ስለ ግጭታችን፣ ስለ መለያየታችን
ለጌታ መልስ እንሰጣለን!
(ይህን
ዕለታዊ
ዲቮሽን
ላይክ እና ሼር ያድርጉ፣
ወዳጅ ጓደኞችዎም እንዲያገኙ ያግዙ፡፡
ዲቮሽኑ
ሳይቋረጥ
ዓመቱን
ሙሉ እንዲቀጥል በጸሎትዎና ጌታ
በልብዎ
ባስቀመጠው
ማናቸውም
ነገር ሁሉ ይደግፉ፡፡ ጌታ
ይባርክዎ፡፡)
No comments:
Post a Comment