Thursday, February 19, 2015

አዲስ ዜና! Eagle Amharic Radio 24/7 መጀመሬን በደስታ አሳውቃለሁ፡፡

አዲስ ዜና!

ከዛሬ ጀምሮ፣ Eagle Amharic Radio  24/7 መጀመሬን በደስታ አሳውቃለሁ፡፡

ዲቮሽኖቼንና ሌሎች ትምህርቶቼን በዚህ በራሴ ሬዲዮ በቀን ለ24/7 ማዳመጥ ይቻላል፡፡ በየትኛውም ዓለም የሚገኙ አማርኛ አድማጮች  http://zenoradio.com/en/listeners/ET/Eagle+Amharic+Radio/ በመጫን ሊያዳምጡ  ይችላሉ፡፡ አሜሪካ ሀገር የሚኖሩ በነጻ ስልክ (605) 562 4274 ማዳመጥ ይችላሉ፡፡
ዲቮሽኖቹ ከማርች 2005 ጀምሮ ይቀርባሉ አሁን የሙከራ ስርጭት

Announcement!

I Started Broadcasting a 24/7 Eagle Amharic Radio


Kindly Listen to My Teachings on: http://zenoradio.com/en/listeners/ET/Eagle+Amharic+Radio/

የመታደስ ዘመን ይመጣላችኋል!

ዲቮሽን .162/07፣ ሐሙስ የካቲት 12/07 ..
(
በፓ/ ተስፋሁን ሐጢያ)


የመታደስ ዘመን ይመጣላችኋል!

እንግዲህ ኃጢአታችሁ እንዲደመሰስ ንስሐ ግቡ፣ ከመንገዳችሁም ተመለሱ፣ ከጌታም ዘንድ የመታደስ ዘመን ይመጣላችኋል (የሐዋ 3፡19)።

መንፈሳዊ ሕይወት ዕለት ተዕለት እየታደሰ መሄድ ይገባዋል፡፡ ይህ ተሐድሶ የሚመጣው ደግሞ፣ ንስሐ በመግባትና ከመንገዳችን በመመለስ ነው፡፡ ንስሐ ኃጢአትን የሚደመስስ መንፈሳዊ ኃይል ነው፡፡ የመታደስ ዘመን የሚመጣው ኃጢአታችንን ትተን፣ ከገዛ መንገዳችንም በንስሐ የተመለስን እንደሆነ ነው፡፡

ወዳጄ ሆይ፣ የመታደስ ዘመን እንዲመጣልዎ ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ ኃጢአትን ይተዉ፣ ከገዛ መንገድዎም ይመለሱ! በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነውና(1 ዮ 1፡9) በኃጢአታችን እንናዘዝ፣ ከመንገዳችንም እንመለስ። ይህ ሲሆን ነው፣ የመታደስ ዘመን የሚመጣልን፡፡


የመታደስ ዘመን ይሁንልዎ!