ዲቮሽን ቁ.10/2007 ቅዳሜ፥ መስከረም 10/2007 ዓ.ም.
(ፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)
(ፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)
ቸኩለህ አትውጣ!
ሙሴ ጎበዝ በሆነ ጊዜ
ወደ ወንድሞቹ ወጣ… በእኛ
ላይ አንተን አለቃ ወይስ
ዳኛ ማን አደረገህ? ወይስ
ግብጻዊውን
እንደገደልከው
ልትገድለኝ
ትሻለህን?
አለው… ፈሪኦንም ይህን ነገር
በሰማ ጊዜ ሙሴን ሊገድለው
ፈለገ፡፡
ሙሴ ግን ከፈሪኦን ፊት
ኮበለለ
(ዘጸ 2፡11-15)
እግዚአብሔር
ሕዝቡ ነጻ እንዲወጣ ይፈልጋል፡፡
ለዚህም
ዓላማው
ሰው ያስነሳል፡፡ ለዚህ ዓላማ
የተነሳ
ሰው ታዲያ ወደ ስራ
ለመሰማራቱ
በፊት በትዕግስት የጌታን ጊዜ
መጠበቅ
ይገባዋል!
ታውቃላችሁ፥
ያለ ጊዜው ለጌታ ስራ
መሰማራት
ዋጋ ያስከፍላል፡፡ ያለጊዜው ቸኩሎ
መውጣት
ለኪሳራና
ውርደትም
ይዳርጋል!
ከሙሴ ሕይወት ያየነው ይህን
ነው፡፡
ሙሴ ጎበዝ በሆነ ጊዜ
ወደ ወንድሞቹ ወጣ፡፡ ወንድሞቹ
ተቃወሙት፡፡
ፈሪኦኑም
ሊገድለው
ፈለገ፡፡
ሙሴ ቸኩሎ በራሱ ጊዜ
ወጣ - ኪሳራ ደርሶበት ከአገር
ወጣ! ታውቃላችሁ፥ ቸኩሎ "እዩኝ፥
እዩኝ" ማለት "ደብቁኝ፥ ደብቁኝ"ን
ያስከትላል፡፡
ሮጦ እንደ ሽንበቆ መውጣት
በኋላ እንደ ሙቀጫ ያንደባልላል!
ሺህ ጊዜ ሺህ እውቀት
ይኑር፥
እልፍ ጊዜ እልፍ ብቃት
ይኑር፥
ለጌታ ስራ ያለ ጊዜው
መውጣት
አደጋ አለው! ኪሳራ አለው!
ከሙሴ የምንማረው ይህን ነው፡፡
ሙሴ የግብጾችን ጥበብ ሁሉ
የተማረ፥
የተመራመረ
ነበር! በግብጽ አገር ይሰጡ
የነበሩ
የትምህርት
ፊልዶችን
ሁሉ የጨረሰ፥ በርካታ ዲግሪዎችን
የበጣጠሰ
ሊቅ ነበር፡፡ የማናቸውንም ትምህርቶች
ቴዎሪና
ተግባር
ጠንቀቆ
ያወቀ ምሁር ነበር፡፡ ሕግና
አስተዳደሩን፥
ፍልስፍና
ሎጂኩን፥
ማኔጅመንት
ፋይናንሱን፥
ንግድ ኢንዱስትሪውን፥ ፖለቲካ ኤኮኖሚውን
ፈልፍሎ
ያወቀ ነበር፡፡ እነዚህን ችሎታዎችና
ብቃቶች
ይዞ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ለመምራት
ወጣ፡፡
ነገር ግን ተቀባይነት አጣ፥
አፍሮና
ተዋርዶ
ከአገር
ወጣ!
ታውቃላችሁ፥
ሙሴ በምድራዊ እውቀቱ ለሕዝብ
አስተዳደር
ስራ ከሚፈለገው ችሎታ በላይ
(Over Qualified) ነበር፡፡
ለጌታ ስራ ግን ከደረጃ
በታች (Under
Qualified) ነበር፡፡
ለጌታ ስራ ከላይ የሆነ
ሰማያዊ
ጥበብና
መንፈሳዊ
ብቃት ሊኖር ግድ ይላል!
ይህ ደግሞ ከየትኛውም ምድራዊ
ትምህርት
ቤት የሚያገኙት ሳይሆን ከእግዚእብሔር
ከራሱ የሚሰጥ ነው፡፡ ሰማያዊ
ጥበብ ራስን በማዋረድ፥ በጾምና
በጸሎት
የሚቀበሉት
ነው፡፡
ሰማያዊ
ጥበብ የራስን ፈቃድ ለእግዚአብሔር
ፈቃድ በማስገዛት የሚያገኙት ነው፡፡
ይህ ጥበብ ለመንፈስ ቅዱስ
ምሪት በመታዘዝ የሚጎናጸፉት ነው፡፡
ታውቃላችሁ፥
የእግዚአብሔር
ስራ በእኛ ችሎታና ብቃት
አይሰራም!
እውቀትና
ልምዳችን፥
ችሎታና
ብቃታችን
ለጌታ ስራ ተጨማሪ እሴት
ሊሆን ይችላል፡፡ ዋናው ግን
ከላይ የሚመጣው ነው! ከላይ
የሚመጣው
ከምድራዊው
ይበልጣል!
የታችኛው
ጥበብ ሰውን ያለ አቅሙ
ያስኮፍሳል፥
ያለ ደረጃውም መሰላል ላይ
ይሰቅልና
አንሸራትቶ
ከመሬት
ላይ ይከሰክሳል!
ስለሆነም፥
ወደ እግዚአብሔር ስራ ጊዜውን
ጠብቀን፥
ድምጹን
ሰምተን፥
ቃል ተቀብለን እንውጣ! ጌታን
አይተን፥
ራዕይ ይዘን፥ ተቀብተን እንውጣ!
እግዚአብሔር
ይርዳን፡፡
(ይህን
ዲቮሽን
ላይክ ያድርጉ፥ ለወዳጅ ጓደኞችዎም
ያስተላልፉ)
No comments:
Post a Comment