ዲቮሽን ቁ.15/2007 ሐሙስ፣ መስከረም 15/2007 ዓ.ም.
(በፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)
(በፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)
የእግዚአብሔር “ታቱ” !
ጽዮን ግን፦ እግዚአብሔር ትቶኛል፤
ጌታም ረስቶኛል አለች። … እኔ
ግን አልረሳሽም። እነሆ፥ እኔ
በእጄ መዳፍ ቀርጬሻለሁ፥ ቅጥሮችሽም
ሁልጊዜ
በፊቴ አሉ። (ኢሳ 49፡14-16)
በቅርቡ
አንድ ወጣት ታክሲ ሾፌር
ከኮሌታው
ስር ባለው አንገቱ ላይ
የሴት ልጅ ስም በጥቁር
ቀለም ተነቅሶ አየሁና ምኑ
እንደሆነች
ጠየቅሁት፡፡
ወጣቱ በስሜት ተውጦ፣ በቅርቡ
ሚስቱ የመጀመሪያ ሴት ልጅ
እንደወለችለትና
ለጨቅላዋ
ያለውን
ፍቅር ለመግለጽም በስሟ “ታቱ”
መሰራቱን
አጫወተኝ፡፡ የልጁ ሁኔታ ዛሬ የማካፍላችሁን
መልዕክት
እንዳሰላስል
አደረገኝ፡፡
ታውቃላችሁ፣
እግዚአብሔር
በስማችን
“ታቱ” ተሰርቷል! እግዚአብሔር ለእኛ
ካለው ብርቱ ፍቅር የተነሳ
በእኛ የተሰራው “ታቱ” ከአንገቱ
ላይ፣ ከጀርባው ላይ ወይም
ከሌላ ቦታ ላይ ሳይሆን፣
ከእጁ መዳፍ ላይ ነው!
አሁንም፣
አሁንም
በስስት
ከሚያየን
ቦታ ላይ! ሃሌሉያ!!
ታውቃላችሁ፣ እኛ ለእግዚአብሔር የእጁ ላይ ጌጡ ነን! አሁንም፣ አሁንም በስስት የሚያየን የመዳፍ ላይ ጌጡ! የመዳፍ ላይ ሀብቱ፣ የመዳፍ ላይ “ታቱ”፣ የእጁ ንቅሳቱ ነን! ከእጁ የማይሰረዝ፣ ከእጁ የማይበረዝ፣ የማይከለስና የማይደበዝዝ ታቱ ነን! በቀላሉ የማይፋቅ፣ የማይለቅና የማይወድቅ ታቱ ነን! ማንም ከእጁ የማይሰርቀን፣ የማይነጥቀንና የማይነቀንቀን የመዳፉ ታቱ ነን! ሃሌሉያ!
ታውቃላችሁ፣ ያለነው በእግዚአብሔር እጅ ላይ ነው! ባሕር በከፈለች፣ ቅጥር ባፈረሰች፣ መና ባዘነበች፣ አለትን ሰንጥቃ ምንጭን ባፈለቀች እጅ ላይ! ዘንዶውን በወጋች፣ ረአብን በቆራረጠች እጅ ላይ! ደመና ሳይደምን፣ ዝናብም ሳይዘንብ ባዶውን ሸለቆ በውሃ በሞላች እጅ ላይ ነን! ሃሌሉያ!!
መከራና ጭንቀት፥ ረሃብም ሆነ ስደት፥ ፍርሃት ራቁትነት፥ ሕይወትም ሆነ ሞት ከመዳፉ አይለየንም! ከፍታው ዝቅታው፣ ሐዘንና ደስታው፣ ሕመምና ጤናው፣ ያለው የሚመጣው … ከእጁ አይለየንም! በእጁ መዳፍ ላይ ተቀርጸናላ! በእግዚአብሔር መዳፍ ላይ የተቀረፅን የእግዚአብሔር “ታቱ” ነና!
No comments:
Post a Comment