ዲቮሽን ቁ.46/07 እሁድ፣ ጥቅምት
16/07 ዓ.ም.
(በመጋቢ ተስፋሁን ሐጢያ)
እንዲሁ
ታመልከዋለህ?
ሰይጣንም
ለእግዚአብሔር እንዲህ ብሎ መለሰለት። በውኑ ኢዮብ እግዚአብሔርን የሚፈራ በከንቱ ነውን? እርሱንና ቤቱን በዙሪያውም ያሉትን
ሁሉ አላጠርህለትምን? የእጁን ሥራ ባርከህለታል፥ ከብቱም በምድር ላይ በዝቶአል። ነገር ግን እጅህን ዘርግተህ ያለውን ሁሉ
ዳብስ በእውነት በፊትህ ይሰድብሃል (ኢዮብ 1፡9-11)።
ወዳጄ
ሆይ፣ እግዚአብሔርን የሚያመልኩት ለምንድነው? በእርስዎና
በቤተሰብዎ ዙሪያ ሰላሙን ስላፈሰሰ ይሆን? ይህ ባይሆንስ ያመልኩታል?
ወዳጄ
ሆይ፣ የሚያመልኩት በሀብት በንብረትዎ ዙሪያ አጥር ስለሠራ ይሆን? ይህ ባይሆንስ፣ ያመልኩታል?
እግዚአብሔርን
የሚያመልኩት ሥራ ስለሰጠዎ፣ እንጀራ ስለሰጠዎ፣ የእጆችዎን ሥራ ስለባረከልዎ፣ በንግድ ትርፍ ስለሰጠዎ ይሆን? ይህ ባይሆንስ፣
ያመልኩታል?
ወዳጄ
ሆይ፣ የሚያመልኩት ትዳር ስለሰጠዎ፣ ልጅ ስለሰጠዎ፣ ጤና ስለሰጠዎ፣ ወዳጅ ጓደኛ ስለሰጠዎ ይሆን? በእውነቱ ይህ ባይሆን
እንዲሁ ያመልኩታል?
ወዳጄ
ሆይ፣ ጌታን የሚያመልኩት በቁሳዊ ነገር ምክንያት ከሆነ አደጋ ላይ ነዎት! የአምልኮዎ ምክንያት ቁሳዊ ነገር ከሆነ በዲያብሎስ
ዒላማ ላይ ነዎት! በብዙ ቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ከቁሳዊ ነገር ጋር ያላቸውን ቁርኝት ዲያብሎስ ያውቃል! ቁሳዊ ነገራቸው
ሲነካ እምነታቸው እንደሚነካ ያውቃል! ቁሳዊ ነገራቸው ቢፈርስ እምነታቸውም አብሮ እንደሚፈርስ ያውቃል! ስለሆነም፣ የእምነት
ሰዎችን በዚህ ይፈትናቸዋል!
ወዳጄ
ሆይ፣ ጌታን የሚከተሉበት ዋናው ምስጢር ስለበሉና ስለጠጡ፣ በሰላም ስለገቡና ስለወጡ፣ ዛሬ ወዳሉበት ከፍታ ላይ ስለወጡ ከሆነ
አደጋ ላይ ነዎት! ስለሆነም፣ ጌታን ከቁሳቁስ ጋር ሳይደባልቁ ብቻውን ያምልኩ! ጌታን ጌታ ስለሆነ ብቻ ያምልኩ!
ቢሰጥ
ቢነሳ፣ ቢጎድል ቢሞላ ለጌትነቱ አምልኮትን ያቅርቡ! ከእግዚአብሔር ሌላ ማንም የለምና ለአምላክነቱ ብቻ አምልኮን ያቅርቡ!
-------------------------
(ይህን
ዕለታዊ
ዲቮሽን
ላይክና ሼር ያድርጉ፣ ወዳጅ ጓደኞችዎም
እንዲያገኙ
ያግዙ፡፡
ይህን አገልግሎት ለመደገፍ (Tesfahun Hatia Daka, Commercial
Bank of Ethiopia, Andinet Branch; A/C 1000036318949; Swift Code: CBETETAA) መላክ ትችላላችሁ፡፡ ለዘሪ ዘርን የሚሰጥ ጌታ ዘራችሁን ይባርክልኝ!)