Saturday, May 30, 2015

ጉዳት እስክታልፍ



ዲቮሽን 263/07 እሁድ፣ ግንቦት 23/07
(በዶ/ በቀለ ብርሃኑ)


ጉዳት እስክታልፍ



ይህ አጭር ጽሑፍ መዝሙር 57 ላይ የተመሠረተ ይሆናል፡፡ በግሌ እጅግ በጣም የምወደው ክፍል ነው፤ ሙሉውን በርጋታና በማስተዋል እንድታነቡት ጋብዤአችኋለሁ፡፡

 

ከሰዎች ጋር ስንኖር መቀራረብ ይኖራል፣ መራራቅም እንዲሁ፡፡ በመቀራረብ የሚመጣ በረከት አለ፡፡ ጉዳትም ይኖራል፡፡ በተጨማሪም ባልጠበቅነው መንገድ የሚመጡ ብዙ ጉዳቶችና ስብራቶች ይኖራሉ፡፡ ከቤት መውጣት እስኪያስጠላንና አፍረን አንገት እስክንደፋ ድረስ የሚያደርገን ፈተና ሊመጣብን ይችላል፡፡ መኖርን እስከመጥላት ልንደርስም እንችል ይሆናል፡፡ በግሌ በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታዎች ውስጥ ደጋግሜ ማለፌን አልደብቃችሁም፡፡ እነዚያ ገጠመኞች ግሩም የመሠሪያ ጊዜም እንደነበሩ አበስራችኋለሁ፡፡ ይህንን አስመልክቶ ሐዋርያው ያዕቆብ እንዲህ ብሏል፡-

ወንድሞቼ ሆይ፣ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፣ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት፡፡ ትዕግሥትም ምንም የሚጎድላችሁ ሳይኖር ፍጹማንና ምሉዓን ትሆኑ ዘንድ ሥራውን ይፈጽም።” (ያዕቆብ 12-4)


ንጉሥ ሳኦል ዳዊት በነበረው አስተዋይነት ድልና ስኬት ክፉኛ ቀንቶ ስለነበረ፣ ሊያጠፋው ያልሞከረው ነገር አልነበረም፡፡ ስለዚህ ዳዊት ለረጅም ጊዜ በስደትና በእንግልት አሳልፏል፡፡ ዳዊት ይህንን ቅኔ የተቀኘው ከሳኦል ሸሽቶ በዋሻ በነበረበት ጊዜ ነበር(1ሳሙኤል 221)፡፡ ይህ ጊዜ ለዳዊት ከባድ የመከራና የኅዘን ጊዜ ነበር፡፡ በእኔና በሞት መካከል አንድ ርምጃ ቀርቷልስ ብሎ የለ? ለዚህ ነውማረኝ አቤቱ ማረኝ” (.1) ብሎ አምላኩን የተማጸነው፤ አስመልጠኝ ማለቱ ነው፡፡ አዎ፣ ዳዊት ከባድ ጉዳት ላይ እንደ ነበር ምንም አያጠያይቅም፡፡

 

ታዲያ ዳዊት በአምላኩ ላይ የነበረውን መታመንና መሰጠትልቤ ጨካኝ አቤቱ ልቤ ጨካኝ ነው” (.7) በሚል ቋንቋ ገልጾታል፡፡ በእንግሊዝኛ መጽሐፍ ቅዱሶች my heart is fixed የሚል ትርጉምን የያዘ ሐሳብ ሲሆን፣ ዳዊትአልናወጥም አምላኬን እጠብቃለሁማለቱ ነው፡፡ ለመሆኑ በእንደዚህ ዓይነት ጊዜ የኛስ ምላሽ ምን ይሆን ?


ልብ ሊባል የሚገባው ነገር፣ በዚህች አጭር ሕይወት ውስጥ ‹‹ጉዳት›› አይቀሬ መሆኑ ሲሆን፣ መጠየቅ ያለበት ነገር ግንጉዳት እስኪያልፍ ምን ላድርግ?” የሚለው ይሆናል፡፡ ዳዊት በአምላኩ ላይ የሚደገፍና የጸሎት ሰው ስለነበርወደ ሚረዳኝ እግዚአብሔር ወደ ልዑል እግዚብሔር እጮኻለሁ” (.2) በማለት መደገፊያውና መታመኛው እግዚአብሔር እንደ ሆነ በግልጽ አብስሮናል::


እርግጥ ነው ጉዳት በተለያየ መንገድ ሊከሰት የሚችል ጉዳይ ነው፡፡ የሕይወታችን ዘይቤም ይመስላል፤ ከሱ የሚያመልጥ የለምና፡፡ያቀረብናቸው ሰዎች የልብ ቁስል ሊያመጡብን ይችላሉ፤ ሊከዱን ይችላሉ፡፡ ሊገፉንና ሊጥሉን ይችላሉ፡፡ ደስ የሚለውና ሊታወቅ የሚገባው ነገር ግን እግዚአብሔር በፍጹም ታምነው የተደገፉበትን ሰዎች አይጥልም፡፡ ስለዚህ ወገኖቼ ልጠይቃችሁ፡፡ የታመናችሁትና የተደገፋችሁት ማንን ነው?


ዳዊትጉዳት እስክታልፍ በክንፎችህ ጥላ እታመናለሁ” (.1) ብሎ ተናግሯል፡፡ እኛስ በጉዳት ውስጥ ስንሆን ምንድነው የምናደርገው? ዳዊት መከራም ውስጥ ሆኖ በእግዚአብሔር የክንፎች ጥላ በመታመኑከሰማይ ልኮ አዳነኝ ለረገጡኝም ውርደትን ሰጣቸው” (.3) ብሎ መስክሯል፡፡


በግሌ ያዘንኩባቸውና የተጐዳሁባቸው ብዙ ጉዳዮች ነበሩ፡፡ በነዚያ ጊዜያት ደጋግሞ ደርሶልኝ እርሱን የሚመስል አጽናኝና ደጋፊ እንደሌለ በማያሳስት መንገድ ተምሬአለሁ፤ ስለዚህ በድፍረትጌታ ለነፍሴ ደጋፊዋ ነውእላለሁ፡፡ እናንተስ



ጽሑፌን እንደ ገና በጥያቄ ልጨርስ፡፡ ወገኖቼ ጉዳት እስክታልፍ ምንድነው የሚታያችሁ፣ ደግሞስ ምንድነው የምታደርጉት?

የማይወሰድ ዕድል


ዲቮሽን 262/07 ቅዳሜ፣ ግንቦት 22/07
(በዶ/ በቀለ ብርሃኑ)


የማይወሰድ ዕድል

የጸጋው ዙፋን የምሕረት፣ የሕክምናና የፈውስ ቦታ ነው፡፡ የሚገርመው ነገር ግን ወደዚህ የፈውስ ማዕከል እንዳንመጣና እንዳንፈወስ፣ እንዳንለወጥና ለሌሎች በረከት እንድንሆን የማይመጣ የተግዳሮት ዓይነት የለም፡፡

ሁሌ የሚገርመኝ ነገር አለ፡፡ የጨለማው ዓለምና አጋንንቱ ሌሎችን ተግባራት ስናከናውን ምንም ግድ አይሰጣቸውም፡፡ ወደዚህ የፈውስ ቦታ ለመምጣት ስናስብ ግን አዚማቸውንና ተቃውሞአቸውን በተለያየ መንገድ ይገልጻሉ፡፡ ወስነን ለጸሎትና ከጌታ ጋር በተለያየ መንገድ ሕብረት ለማድረግ ስንነሣሣ፣ ስልቹ ሆነን እንድናቋርጥ፣ ቶሎ ጨርሰን ወደ ሌላ ጉዳዮች እንድንሄድ ጫናቸውን ይጨምራሉ፡፡ የጸሎትን ጥቅም ማሣነስም ትልቅ መዋጊያ መሣሪያቸው ነው፡፡

በግል ሕይወቴና ከጌታ ጋር በርከት ያለ ጊዜን ከሚያሳልፉ ሰዎች እንደተማርኩት፣ በጌታ እግር ሥር መሆን ብዙ ጥቅም አለው፡፡ ከሁሉ ሊተኮርበት የሚገባው ጥቅም ግን ውስጣችን መለወጡ ነው፡፡ ውስጣችን ዕለት ዕለት መታደሱ ነው (2ቆሮንቶስ 416)፡፡ ልባችን የመንፈስ ፍሬዎችን ማፍለቁና መንፈሳችን መጠንከሩ ነው፡፡

ከላይ እንደጠቀስኩት ከጌታ ጋር በቂ ሕብረት እንዳይኖረን የማይመጣ የጠላት ተጽዕኖ የለም፡፡ ቢሆንም እነዚህንጫናዎች ተቋቁመን በሱ ፊት በቂ ጊዜን ብናሳልፍ፣ ሕይወታች በሚገርም ሁኔታ ይለወጣል፡፡ ያኔ አቅም ባጣንባቸው ነገሮች ላይ ጉልበት እናገኛለን፡፡ ያኔእምቢማለት ባቃቱን ነገሮች ላይ የበላይ እንሆናለን፡፡

እውነተኛ መንፈሳዊ ለውጥና በረከት፣ የምር የሆነ መሻትን ይፈልጋል፤ ራብንና ጉጉትም ያስፈልገዋል፡፡ ይህንን ሐሳብ አስመልክቶ ኢየሱስጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው ይጠግባሉናብሎ ድንቅ መንፈሳዊ መርሕን አብስሮናል፡፡  እኔ ሁልጊዜይጠግባሉናየሚለው ተስፋ በኃይል የሚያስደንቀኝና ጉጉትን የሚፈጥርብኝ፡፡

አዎ መንፈሳዊ ራባችንና ጥማታችን እያየለ ሲሄድ፣ አስደናቂ ሕይወት ውስጥ ራሳችንን እናገኘዋለን፡፡ እናም መሻታችን እየጨመረ ሲሄድ፣ ሌሎች ብዙ ረብ የሌላቸውን ነገሮች የመጣል ድፍረትን እናገኛለን፤  ምክንያቱም ነፍሳችን በጌታ እያረፈች ትመጣለችና ነው፡፡ ምክንያቱም ነፍሳችን ከተተበተበችበት የማይታዩ ሰንሰለቶች ነጻ ትሆናለችና ነው፡፡

የእግዚአብሔር ቃልዕረፉ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ”(መዝሙር4610) ብሎ ይናገራል፡፡ ታዲያዕረፉማለቱ ጌታ አምነን፣ በፊቱ እየጸለይን፣ ቃሉን እየተመገብንና በእግሩ ሥር ሆነንና እሱን እየጠበቅን መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ ኢየሱስ ስለዚህ ዕረፍት ሲናገርማርያም መልካም ዕድልን መርጣለች፣ ከርሷም አይወሰድባትም” (ሉቃስ 1042) ብሎ ተናግሯል፡፡ በርግጥም በሚገባ ከተዘወተረ የማይወሰድ ዕድል!

ጌታ ሆይ የጸሎትን መንፈስ አፍስስልን! እባክህ በፊትህ የመሆንን ዕድል አብዝተህ ስጠን! የጋለ ፍላጎትና መንፈሳዊ መሻትን በልባችን ላይ አፍስስ!

ትምህርቱ ጠቅሞዎታል? እንግዲያውስ እባክዎ ላይክና ሼር ያድርጉ፣ ጌታ ይባርክዎ።