ዲቮሽን
ቁ.135/07 አርብ፣ ጥር 15/07 ዓ.ም.
(በመጋቢ ተስፋሁን ሐጢያ)
አይዞዎት!
እናንተ ሰዎች
ሆይ፥ አይዞአችሁ፤ እንደ ተናገረኝ እንዲሁ እንዲሆን አምናለሁና (የሐዋ
27፡25)።
በሕይወት ጉዞ ላይ ማዕበል ሊነሳብንና ወጀብ ሊያናውጠን ይችላል!
በሕይወታችን ላይ አውሎንፋስ ሊመጣና ወደማንፈልገው አቅጣጫ ሊገፈትረን ይችላል! በሕይወታችን ላይ ሐሩርና ውርጭ፣ ቁርና ትኩሳት
ሊያቃጥለን ይችላል!
ወዳጄ ሆይ፣ ማዕበል በርትቶብዎት እየተንገላቱ ይሆን? አይዞዎት፤ እንደተናገረዎ እንዲሁ እንዲሆን በእግዚአብሔር ይመኑ!
በቃሉ የታመነ፣ እንደተናገረው ሊያደርግ የሚችለውን እግዚአብሔርን ይመኑ!
ወዳጄ ሆይ፣ አይዞዎት!
ማዕበል ቢበረታም አይዞዎት! ወጀብ ቢያንገላታዎትም አይዞዎት! ችግር ቢፈራረቅብዎትም አይዞዎት! መከራ ቢያይልብዎትም አይዞዎት!
ቃሉ የማይታጠፍ፣ ታማኝ እግዚአብሔር የተናገረዎን እንዲሁ ሳያደርግ ማዕበሉም፣ ወጀቡም፣ መከራውም ችግሩም አያጠፋዎትምና አይዞዎት!
ወዳጄ ሆይ፣ ሐዋርያ
ጳውሎስን ያስቡ! ‹‹በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ›› በእስራቱ ላይ ተጨማሪ ማዕበል ተጨማሪ ወጀብ ተነሳና ባህሩ ተናጠ! የእግዚአብሔር
ሰው ጳውሎስ ከጣረ ሞት ጋር ፊትለፊት ተፋጠጠ!
ታውቃላችሁ፣ ተልዕኮ
ያለው ሰው፣ ቃል የተሰጠው ሰው፣ ጌታ የተናገረው ሰው ዝም ብሎ አይሞትም! የፈለገው ማዕበል፣ ተፈለገው ወጀብ፣ የፈለገው ስቃይ፣
የፈለገው እንግልት ቃል ያለውን ሰው ሊያጠፋው አይችልም!
ታውቃላችሁ፣ ቃል
የተሰጠው ሰው፣ መከራና ጭንቀት፥ ፍርሃትና ስደት፥ ረሀብ ራቁትነት፥ የእግዚአብሔር ቃል ያለውን የእግዚአብሔርን ሰው ሊያጠፋው አይችልም!
-----
ትምህርቱ ጠቅምዎታል? እንግዲያውስ ላይክ ያድርጉ፡፡ ጌታ ይባርክዎ!
ትምህርቱ ጠቅምዎታል? እንግዲያውስ ላይክ ያድርጉ፡፡ ጌታ ይባርክዎ!
--------------------------------
‹‹የወንጌላዊው እጮኛ›› አዲስ መጽሐፍ፣ በገበያ ላይ ውሏል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ
በ0911 678158 ወይም 0911 813092 ይደውሉ፡፡