ዲቮሽን ቁ.198/07፣ አርብ፥ መጋቢት 18/07 ዓ.ም.
(በፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)
(በፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)
በጥቂቱ
ታምነሃል – በብዙ
እሾምሃለሁ!
መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፤
ወደ ጌታህ ደስታ ግባ (ማቴ 25፡20-23)።
ብዙ ጊዜ እግዚአብሔር ለመንግሥቱ ሥራ በኃይል ቀብቶ እንዲያስነሳን፣ በሙላት
እንዲጠቀምብን እንፈልጋለንና በጾምና ጸሎት እንጠይቀዋለን፡፡ የእግዚአብሔርን መንግሥት በምድር ላይ ለመገንባት በውስጣችን ፍላጎት
ማደሩ ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡ ተቀብቶ ለመውጣት መጾምና መጸለይም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው፡፡
ወገኖች ሆይ፣ እግዚአብሔር አምላካችን ለመንግሥቱ ሥራ አገልጋዮችን በኃይል
ቀብቶ ማስነሳትና፣ በሙላትም መጠቀም የዕለት ተዕለት ፍላጎቱ ነው! ነገር ግን ይኼው አምላካችን እኛን በአገልግሎት ቅባት ቀብቶ
ለማውጣት – የእኛን ታማኝነት ይመለከታል!
ወገኖች ሆይ፣ በብዙ ለመሾም በጥቂቱ መታመን መለኮታዊ ሕግ ነው! በመለኮታዊ
አሠራር በጥቂት ነገር መታመን በብዙ ያሾማል! በተሰጠን በጥቂቱ ነገር ታምነን ያልተገኘን በብዙ ለመሾም የመጠበቅ ነገር
የማይታሰብ ነው!
ወገኖች ሆይ፣ በተሰጠን በጥቂቱ ነገር ታማኞች ሳንሆን በብዙ ለመሾም መጾም
መጸለዩ እንዲሁ ለድካም ነው! ታማኝነት ሳይኖር፣ ሺህ ጊዜ ሺህ ጸሎት፣ እልፍ ጊዜ እልፍ ጾም የእግዚአብሔርን ቅባት ሊያመጣው አይችልም!
ታውቃላችሁ፣ ማናችንም ብንሆን ሀብት ንብረታችንን ለማንታመነው ሰው አደራ
አንሰጥም! አመራር፣ አስተዳደር፣ ሹመት ሽልማት የሚመሠረተው በታማኝነት ነው!
ወገኖች ሆይ፣ ከጌታ ለተሰጠን ለጥቂቱ ነገር ታማኞች እንሁን! ይኼ ታማኝነታችን
በእግዚአብሔር ፊት ብድራት ያገኛል! ስለሆነም፣ ለተሰጠን ለጥቂቱ ነገር ታማኞች እንሁን!
ታውቃላችሁ፣ በጥቂት መታመን፥ ለብዙ ሹመት በር ይከፍታል፤ ይህ በር ሲከፈት
ወደ ጌታ ደስታ መግባት ያስከትላል! ሃሌሉያ!
------------------------------------------
(ትምህርቱ ጠቅምዎታል? እንግዲያውስ ላይክ ያድርጉ፣ ጌታ
ይባርክዎ!)
(1) ዕለታዊ ዲቮሽኖቹን በፌስቡክ ለመከታተል የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ፡፡ https://www.facebook.com/tesfahun.hatia
(2) ዲቮሽኖቹን በብሎግ ለመከታተል የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ፡፡
https://draft.blogger.com/blogger.g?blogID=7832170107481561272#allposts
(3) ኤግል የሬዲዮ አገልግሎት በአማርኛ ቋንቋ
መጀመሬን በደስታ አሳውቃለሁ፡፡ በየትኛውም ዓለም የሚገኙ አማርኛ አድማጮች
http://zenoradio.com/en/listeners/ET/Eagle+Amharic+Radio/
በመጫን ሊያዳምጡ ይችላሉ፡፡ Listeners in Canada and America can call free at (605) 562 4274 and enjoy some of my live sermons.