ዲቮሽን
229/07፣ ሰኞ፣
ሚያዚያ
19/07
(በፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)
እግዚአብሔር ይነሣ – ጠላቶቹም ይበተኑ!
እግዚአብሔር
ይነሣ፥ ጠላቶቹም ይበተኑ፥ የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ። ጢስ እንደሚበንን እንዲሁ ይብነኑ፤ ሰም በእሳት ፊት እንደሚቀልጥ፥ እንዲሁ
ኅጥኣን ከእግዚአብሔር ፊት ይጥፉ (መዝ 68፡1-2)።
ወገኖች
ሆይ፣ ሙሴ እስራኤላዊያንን ወደተስፋዪቱ ምድር ለማድረስ በምድረበዳ በሚንቀሳቀስበት ጊዜ ሁሉ ይዘምር የነበረው ዝማሬ፣ ይጮኽ የነበረው
ጩኸት ይኼ ነው! እግዚአብሔር ይነሣ! ጠላቶቹም ይበተኑ! ወገኖች ሆይ፣ ጌታ እንዲነሣ፣ ጠላቶቹም እንዲበተኑ – ወደ ጌታ እንጩኽ
!
ወገኖች
ሆይ፣ የኃጢአተኞች ክፋት በምድር ላይ ሲበዛ፣ ለጻድቃን መከራ ይበዛል! እግዚአብሔር ዝም ሲል፣ የጻድቃን መከራ የትየለለ ይሆናል!
ጌታ ካልተነሣ፣ እግዚአብሔር ዝም ሲል፣ ጠላት በሕዝቡ ላይ የፈለገውን ሥራ ሊሠራ ይችላል!
ወገኖች
ሆይ፣ ጌታ ካልተነሣ፣ ጠላት በጻድቃን ላይ ምላሱን አውጥቶ እኚኝያ ይሰጣል! ጌታ ካልተነሣ፣ ጠላት በጻድቃን ላይ ጦሩን ከነነቅነቅ፣
ሰይፉን ከመምዘዝ አልፎ፣ ጦሩን ይወረውራል፣ በጭካኔ ካራ አንገት ይሰይፋል፡፡
ወገኖች
ሆይ፣ ጌታ ካልተነሣ፣ ጠላት በጻድቃን ላይ ቀስቱን በመለጠጥ፣ ፍላጻ በመላክ፣ ድንጋይ በመወርወር፣ ሰላምን በማወክ ምድርን ያሸብራል!
ወገኖች ሆይ፣ እግዚአብሔር ዝም ሲል፣ ጠላት ይፈነጫል! ዳንኪራ ይረግጣል፣ የጻድቃንን ደም በማፍሰስ፣ ጠጥቶ ይሰክራል!
ወገኖች
ሆይ፣ እግዚአብሔር በኃይሉ ሲነሣ ግን ጠላቶቹ ይወድቃሉ! እግዚአብሔር በኃይሉ ሲነሣ ጠላቶቹ ከፊቱ ይሸሻሉ! እግዚአብሔር ሲነሣ፣
ጢስ በንኖ እንደሚጠፋ ሁሉ ጠላቶቹ በንነው ይጠፋሉ! ሰም በእሳት ፊት እንደሚቀልጥ ሁሉ እግዚአብሔር ሲነሣ ጠላቶቹ ይቀልጣሉ!
ወገኖች
ሆይ፣ የጠላት ብርታት፣ የጻድቃን መከራ መብዛት ምክንያቱ የእግዚአብሔር አለመነሣት ነው! በዓለም ዙሪያ ባሉ በጻድቃን ላይ መከራ
የበዛው፣ ደማቸው በከንቱ እየፈሰሰ በአፈርና ወንዝ ጋር የሚቀላቀለው፣ ጌታ ዝም ስላለ ነው!
ወገኖች
ሆይ፣ የእግዚአብሔር ዝምታ አደገኛ ነው! ጌታ ዝም ካለ፣ ለእኛ ችግር አለው! ጌታ ዝም የሚለው በሕዝቡ አዝኖ ነው! እግዚአብሔር
ካዘነ ለእኛ አደጋ ነው! ወገኖች ሆይ፣ ጻድቃን ሲታረዱ ጌታ ዝም ካለ፣ ጻድቃን ከነሕይወታቸው በእሳት ሲቃጠሉ ጌታ ዝም ካለ፣ የሕጻናት
ደም በመሬት ላይ እየጎረፈ ጌታ ዝም ካለ – ይኼ አደጋ ነው!
ወገኖች
ሆይ፣ ኃጢአን በጻድቃን ላይ፣ ያሻቸውን ሠርተው፣ ከልካይ ሰው ከሌለ – ይኼ አደጋ ነው! የጻድቃን ሚስቶች በባሎቻቸውና በልጆቻቸው
ፊት እርቃን ስትደፈር ከልካይ ሰው ከሌለ – ይኼ አደጋ ነው! የጻድቃን እጆች ወደኋላ ታስሮ፣ እንደ ቄራ ከብቶች በግፍ ሲታረዱ
ጌታ ዝም ካለ – ይኼ አደጋ ነው!
ወገኖች
ሆይ፣ ሌላ ሌላ ነገር ትተን፣ ሌላ ሌላ ሥራ ትተን፣ ንስሐ እንግባ! ወገኖች ሆይ፣ መነቋቆራችንን ትተን፣ መወጋገዛችንን ትተን፣
መካሰሳችንን ትተን፣ እግዚአብሔር እንዲነሣ ወደ እግዚአብሔር እንጩኽ! ወገኖች ሆይ፣ አሕዛብ፣ በእውነት ለጻድቅ ፍሬ እንዳለው እንዲያውቁ፣ በእውነት በምድር ላይ የሚፈርድ አምላክ አለ እንዲሉ – ጌታ እንዲነሣ፣
ወደ ጌታ እንጩኽ።
የሕዝቡ ጠላቶች እንዲደመሰሱ፣ የጻድቃን ጠላቶች ከምድር ገጽ ፍጹም እንዲጠፉ ወደ ጌታ እንጩኽ! በጻድቃን ሁሉ
ላይ ሰይፋቸውን የሚነቀነቁ፣ በሰይፍ እንዲጠፉ – ጌታ እንዲነሣ፣ ወደ ጌታ እንጩኽ።፣ በቆፈሩት ጉድጓድ
ራሳቸው እንዲገቡ –
ጌታ እንዲነሣ ወደ ጌታ እንጩኽ።
ትምህርቱ ጠቅምዎት
ከሆነ፣ ላይክ ያድርጉ! ጌታ ይባርክዎ!