ዲቮሽን ቁ.13/2007ማክሰኞ፥ መስከረም 13/2007 ዓ.ም.
(በፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)
(በፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)
እግዚአብሔርን እንፍራ፥ ትእዛዙንም እንጠብቅ!
የነገሩን
ሁሉ ፍጻሜ እንስማ፥ ይህ
የሰው ሁለንተናው ነውና፥ እግዚአብሔርን
ፍራ፥ ትእዛዙንም ጠብቅ፡፡ እግዚአብሔር
ስራን ሁሉ፥ የተሰወረውንም ነገር ሁሉ፥
መልካምም
ቢሆን ክፉም ቢሆን፥ ወደ
ፍርድ ያመጣዋልና ( መክብብ 12፡13-14)
ከላይ የቀረቡት ሁለት ጥቅሶች
የመጽሐፈ
መከብብ
የመጨረሻ
ድምዳሜ
ነው፡፡
ጸሐፊው
ከጸሐይ
በታች ያደረጋቸውን ጥልቅ ምርምሮችና
ጥናቶች
ሲያጠናቅቅ፥
ለሰው ልጆች ሁሉ የሰጠው
የመጨረሻ
ምክር ነው፡፡ እግዚአብሔር እንደ
ስራችን
የሚፈርድ
አምላክ
ነውና፥
የሰው ልጆች ሆይ፥ አካሄዳችሁን
መርምሩ፥
ስራችሁን
ፈትሹ እያለ ነው!
የመጽሐፈ
መክብብ
ጸሐፊ ንጉሱ ሰለሞን ነው፡፡
ሰለሞን
አባቱን
ዳዊትን
ተክቶ የእስራኤል ንጉስ የሆነው
ገና በወጣትነት ዕድሜው ነው፡፡
ሆኖም ጌታ ወጣት ነው
ሳይል፥
አልተማረም
፥ አልተመራመረም ሳይል፥ አለው
የለውም
ሳይል፥
የሚያስፈልገውንና
የተሟላ
እውቀትና
ጥበብ፥
ሀብትና
ዝና፥ ሰላምና ጤና ሰጥቶታል፡፡
እግዚአብሔር
ለሰለሞን
ሁለት ጊዜ ተገልጦለታል! በዚህ
መገለጥ
የእግዚአብሔርን
ማንነት
እንዲያውቅ፥
ክብሩንና
ሞገሱን
እንዲያውቅ፥
ቅድስናውንና
ጽድቁን፥
ምሕረትና
ፍርዱን
እንዲያይ
አድርጎታል፡፡
ሰለሞን
በተገለጠለት
እምነት
መሰረት
ጌታን እንደመከተል፥ በራሱ የምርምርና
ጥናት አዙሪት ውስጥ ገብቶ
መዳከር
ጀመረ፡፡
ከተገለጠለት
እምነትም
ሆነ ከተሰጠው መለኮታዊ ትእዛዝ
ወጣ፡፡
ሕይወቱን
በምርምርና
ጥናት ባህር ውስጥ ዘፍቆ
ያለ መቅዘፊያ ይዋኝ ጀመር፡፡
ሕይወት
ከተገለጠላት
ብርሃን
በተቃራኒ
ብትሄድ
ልትረካ
አትችልምና
ጨለመበት!
ሕይወት
ከተሰጣት
ምሪት መስመር ውጭ መሻገር
አትችልምና፥
ሰለሞን
በጥልቁ
ባህር ላይ ሰጠመ! ለዚህ
ነው የሚመክረን፡፡
የሰለሞን
ማስጠንቀቂያ
ግልጽ ነው! ሕይወትን በራሳችን
ምድራዊ
መስፈርቶች
አንምራ፥
ይጨልምብናልና!
ሕይወታችንን
በተገለጠልን
የእግዚአብሔርን
ቃልና ምሪት እንጠብቅ ሕይወት
አስደሳች
ትሆንልናለችና!
እግዚአብሔርን
እየፈራንና
ቃሉን እየጠበቅን እንኑር፡፡ እንዴት
እንደምንኖር
እንጠንቀቅ!
አንድ ቀን በእግዚአብሔር ፊት ለፍርድ
እንቀርባለንና!
(ይህን
ዲቮሽን
ላይክ ያድርጉ፥ ለወዳጅ ጓደኞችዎም
ያስተላልፉ፡፡
ጌታ ይባርክዎ!)
No comments:
Post a Comment