Tuesday, June 30, 2015

ግብረሰዶማዊነት – የማይረባ አዕምሮ ውጤት #1

ዲቮሽ 293/07፥ ማክሰኞ፥ ሰኔ 23/07 ዓ/ም
(በፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)
ግብረሰዶማዊነት – የማይረባ አዕምሮ ውጤት #1
እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው (ሮሜ 1፡28)
ከሣምንታት በፊት አየርላንድ 62% በሆነ ሕዝበ ውሳኔ ግብረሰዶማዊነት የሀገሯ ሕገመንግሥታዊ መብት በማድረግ ያጸደቀችውን ዜና አድምጠን ሳናበቃ፣ ሰሞኑን ደግሞ ታላቋ ሀገር አሜሪካ ግብረሰዶማዊነት በመላ ሀገሪቱ ውስጥ ሕገመንግሥታዊ እንዲሆን አጽድቃለች፡፡ ይህን ተከትሎ ከመላው ዓለም ዘንድ የድጋፍና ተቃውሞ አስተያየቶች እየተሰጡ ነው፡፡
ወገኖች ሆይ፣ ዓለማችን በትልቅ ትኩሳት ቀልጣ ልትጠፋ ደርሳለችና በዚህ ልንደነቅ አይገባም፡፡ ግብረሰዶማዊነት በሀገር ደረጃ ሕጋዊ ከሆነባቸው ሀገሮች አሁን አሜሪካ 15ኛዋ ሀገር ትሁን እንጂ፣ ሌሎችም በርካታ ሀገሮች ሕጉን በመወሰኛ ምክር ቤቱ ጠረጴዛ ላይ ወረፋ አስይዘው ቀን እየጠበቁ ያሉ በርካታ ናቸው፡፡ በሀገራችንም ኢትዮጵያ በመወሰኛ ምክር ቤቱ ጠረጴዛ ላይ ይኼ ጥያቄ ወረፋ ይዞ ይኑር አይኑር የማውቀው ነገር ባይኖርም፣ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች የግብረሰዶማዊያን ክለቦች የመኖራቸው እውነታ ከሐሜት ባለፈ ደረጃ ሲወራለት ቆይቷል፡፡
ይኼ ችግር በዓለም ደረጃ እያሳየ ከመጣው ፈጣን የሆነ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም አጋንንታዊ ጫና ሲታይ፣ በቅርብ ዓመታት በመላው የዓለም ሀገሮች ተቀባይነት የሚያገኝ ይመስላል፡፡ ስለሆነም፣ የዓመታት ጉዳይ ይሁን እንጂ ኢትዮጵያም ግብረሰዶማዊነትን በውዷ ሳይሆን በግዷ ተቀብላ በሕገመንግሥት የምታጸድቅበት ዘመን ሩቅ አይመስልም፡፡
ወገኖች ሆይ፣ ግብረሰዶማዊነት በመጽሐፍ ቅዱሳዊ እይታ ምንድነው? ግብረሰዶማነት ማለት ‹‹የማይገባውን ነገር እንዲያደርግ ተላልፎ የተሰጠ የማይረባ አእምሮ›› ማለት ነው፡፡ ይህ አእምሮ የሚፈጠረው እግዚአብሔር ለሰዎች ሊታወቅ እየፈለገና እየቀረበ ነገር ሰዎች እርሱን ለማወቅ ባለመውደድና ባለመፈለግ የሚከሰት አደጋ ነው፡፡ ይህን ሐሳብ በምሣሌ ላስረዳ፡፡
አንድ በሽተኛ ከታመመ ታክሞ መዳን ይገባዋል፡፡ ይህን ሕክምና ባልፈለገና ባልወደደ መጠን በሽታው ወደ ካንሰር ይቀየራል፡፡ ግብረሰዶማዊነት ከበሽታ ያለፈ የሰውን ስነልቦና ወደ እንስሳነት የሚቀይር ካንሰር ነው፡፡ የሰው ዓይነምድር መብላትን ጨምሮ ግብረሰዶማዊያን ሲያደርጓቸው የሚታዩት እጅግ ቀፋፊና ዘግናኝ የሆኑ ድርጊቶች ይህን እውነታ የሚያሳዩ ናቸው፡፡ ግብረሰዶማዊያን የተቃራኒ ጾታ ግንኙነት የሚጠሉ ቢሆንም፣ ነገር ግን በሚገርም ሁኔታ እናት ከወንድ ልጅዋ ጋር፣ አባት ከሴት ልጁ ጋር፣ ወንድም ከእህቱ ጋር የሚያደርገውን የግብረሥጋ ግንኙነት ያበረታታሉ፡፡ ሴቶቹ ከወንድ ውሾች ጋር፣ ከወንድ ፈረሶችና ከወንድ አህዮች ጋር የሚያደርጉትን የግብረሥጋ ግንኙነት ያበረታታሉ፡፡ ወንዶቹም ከሴት ውሾች ጋር፣ ከሴት ፈረሶችና አህዮች ጋር የሚያደርጉትን የግብረሥጋ ግንኙነት ያበረታታሉ፡፡ ይህም ከተፈጥሮ ሕግጋትና ሥርዓት ጋር ያላቸውን ጥላቻ ያሳያል፡፡
ወገኖች ሆይ፣ ግብረሰዶማዊያን፣ የተቃራኒ ጾታ ግንኙነት የሚጠሉ ቢሆንም፣ አንዲት ሴት በአንድ ጊዜ ከሶስትና አራት ወንዶች ጋር የምታደርገውን የግብረሥጋ ግንኙነት ያበረታታሉ፡፡ ግብረሰዶማዊያን፣ የተቃራኒ ጾታ ግንኙነት የሚጠሉ ቢሆንም፣ ነገር ግን በሕዝብ አደባባዮችና በየመንገዱ ወንዶች ከሴቶች ጋር የሚያደርጉትን ከባሕልና ሥርዓት ያፈነገጠ ዝሙት እንዲደረግ ያበረታታሉ፡፡ ይህም ከተፈጥሮ ሕግጋትና ሥርዓት ጋር ያላቸውን ጥላቻ ያሳያል፡፡
ወገኖች ሆይ፣ ግብረሰዶማዊያን፣ የተቃራኒ ጾታ ግንኙነት የሚጠሉ ቢሆንም፣ ነገር ግን ሁለት ወንዶች ሚስቶቻቸውን ተቀያይረው፣ አንድ ቤትና አንድ አልጋ ላይ መዘሞትን ያበረታታሉ፡፡ ግብረሰዶማዊያን፣ የተቃራኒ ጾታ ግንኙነት የሚጠሉ ቢሆንም፣ ነገር ግን ወንዶች ሚስቶቻቸውን አስይዘው ወይንም አከራይተው ቁማር እንዲጫወቱባቸው ያበረታታሉ፡፡ ግብረሰዶማዊያን፣ የተቃራኒ ጾታ ግንኙነት የሚጠሉ ቢሆንም፣ ነገር ግን ወንዶች ሴት ሕጻናትን አስገድደው እንዲደፍሩ ያበረታታሉ፡፡ ይህም ከተፈጥሮ ሕግጋትና ሥርዓት ጋር ያላቸውን ጥላቻ ያሳያል፡፡
ወገኖች ሆይ፣ እነዚህ ነገሮች በኢትዮጵያ ውስጥም በኅቡዕ እየሆኑ ናቸው፡፡ አስቡት እስቲ 
በምዕራቡ ዓለም ሴቶች ወንድ ውሾችን ለመግዛት የሚመርጡበትና ከሰው በላይ ከአቅም በላይ ሲንከባከቧቸውና ሲወዷቸው የምናይበት ምክንያት፣ ወንዶች ሴት ውሾችን ለመግዛት የሚመርጡበት ምክንያትና ሩቅ መንገድ ሲሄዱም ይዘዋቸው ለመሄድ የሙጥኝ የሚሉበት ምክንያት የጤና ነው?
ወገኖች ሆይ፣ እስኪ በዚህ ዲቮሽን ላይ የሚሰማችሁን አስተያየት ስጡበት? ከሰማችሁትና ካነበባችሁት አካፍሉ? ስለግብረሰዶማነት ያለዎትን አቋም ያንጸባርቁ?

አለጊዜውም ጽና!!!!

ዲቮሽን 292/07 ሰኞ፥ ሰኔ 22/07
(በእህት ማርታ ሲሳይነህ)
አለጊዜውም ጽና!!!!
እግዚአብሔርን ለምንፈራ ለእኛ፣ ሕይወት ሁልጊዜ አመቺ አይደለችምና፣ ያገኘነውን ያህል ስናጣ፣ ሰማይ ሲከደንብንና፣ መሔጃ መላወሻ ስናጣ፣ ቅድስናችንን ለመጣል፣ ብኩርናችንን ለማቃለል፣ ለጌታ ያለንን ነገር ለማዳፈንና፣ አማራጭ ያልነውን ነገር ለመያዝ እናስባለን። አንዳንዴም፣ በጽድቅና በሐጢያት መካከል ያለው ድንበር፣ ውሉ፣ ይጠፋብንና፣ ስሜታችንን ብቻ ወደ መታዘዝ እናደላለን። እግዚአብሔርን ከመፍራት የሚገኘው በረከትና ጥቅም ሁሉ ትርጉም የሚያጣብን ወቅት
ይኖራል።
የሚወዱን ከእኛ በራቁ ጊዜ፣ ብቸኝነት ሲሰማን፣ በቤተክርስትያንም፣ በሰፈርም፣ የምናየው ነገር አላምር ሲለን፣ ሲርበንና ሲጠማን፣ ስንራቆት፣ . . . ሕይወት ዳገት ሲሆንብን፣ ጸንቶ መገኘት እጅግ ፈታኝ ነገር ነው። ቢሆንም ግን፣ ከነገሮች ሁሉ በላይ የሆነውን፣ ኤልሻዳዩን እያሰብን፣ ጸንተን ልንኖር ይገባል። ለዚህም ነው፣ ጳውሎስ፣ አለጊዜውም ጽና በማለት፣ 2ኛ ጢሞ 4፡2 ጢሞቴዎስን የሚመክረው።
መንፈስ ቅዱስ ሆይ፣ ሁሉን ታደርግ ዘንድ በእርግጥ ቻይ ነህና፣ በዚህች ተለዋዋጭ ዓለም ውስጥ፣ ጸንተን እንድኖር እርዳን። ዓለምም በውስጧም ያሉ ገሮች ሁሉ አላፊና ቀሪ መሆናቸውን፣ ትሁት መንፈስ ቅዱስ ሆይ፣ አሁንም፣ አሁንም፣ ደግመህ ደጋግመህ፣ ሳትሰለችና ሳትታክት፣ እባክህ ለነፍሳችን
አስተምራት። እኛም መስማት እንዲሆንልን፣ መንፈሳዊ ዓይኖቻችንን አሁን አብራ። ሰምተህኛልና ተባረክ።
ትምሕርቱ ጠቅሞዎታል፣ እንግዲያውስ እባክዎ ላይክ፣ ሼር እና ኮሜንት ያድርጉ፣ ጌታ ይባርክዎ።

እንባህን እናፍቃለሁ

ዲቮሽን 291/07 እሁድ፥ ሰኔ 21/07
(በእህት ማርታ ሲሳይነህ)
እንባህን እናፍቃለሁ
እንባህን እያሰብሁ በደስታ እሞላ ዘንድ . . . ። 2ኛ ጢሞ 1፡4
አማኝ መሆን ማለት፣ ውጫዊ መረጋጋት፣ ሰላም ሳይሆን ሰላም ነው ማለት፣ በጌታ መንፈስ ሳይነኩ፣ እንደተነኩ መምሰል፣ መንፈሳዊ ጨዋነት፣ መንፈሳዊ ሰላምታ፣ መንፈሳዊ አንደበት፣ መንፈሳዊ አለባበስ፣ የማስመሰል ቁጥብነት፣ . . . . . . ብቻ ከልብ ያልሆነ፣ ለታይታ ብቻ የምናደርገው ተግባር አይደለም።
አማኝነት፣ እግዚአብሔርን በየእለቱ የማወቅና የመረዳት ሒደት ነው። አማኝ፣ ይወድቃል፣ ይነሳል፣ ያለቅሳል፣ ይስቃል፣ ይጠይቃል፣ ይከፋዋል፣ አምላኬ ወዴት ነህ? ይላል። በግል ጉዳዩም ሆነ፣ በሀገርና በቤተክርስትያን ጉዳዮችም ላይ፣ ያልገባው ነገር ካለ፣ አማኝ ያለቅሳል፤ ይጨንቀዋል፤ ይጠበዋል።
ለዚህም ነው፣ ጳውሎስ፣ “እንባህን እያሰብሁ በደስታ እሞላ ዘንድ ላይህ እናፍቃለሁ፣ በአንተ ያለውን ግብዝነት የሌለበትን እምነትህን አስባለሁ” በማለት ለጢሞቴዎስ የሚጽፍለት።
አባት ሆይ ከማስመሰል ህይወት አውጣንና፣ የቀደመውን እንባችንን እና ቅንነታችንን መልስልን። ግብዝነት እና አስመሳይነት የተሞላው ሕይወታችን ዛሬ ይለወጥ። ሰምተህኛልና ተባረክ።
ትምሕርቱ ጠቅሞዎታል፣ እንግዲያውስ እባክዎ ላይክ፣ ሼር እና ኮሜንት ያድርጉ፣ ጌታ ይባርክዎ።

እውነተኛ አምልኮ

ዲቮሽን 290/07 ቅዳሜ፥ ሰኔ 20/07
(በዶ/ር በቀለ ብርሃኑ)
እውነተኛ አምልኮ
እውነተኛ አምልኮ በእግዚአብሔር ጸጋ ከተለወጠ ልብ ይወጣል፡፡ እውነተኛ አምልኮ ግብዝነት የሌለበትና እግዚአብሔርን በእውነትና በመንፈስ በማወቅ የተመሠረተ ስግደት ነው፡፡ እውነተኛ አምልኮ ራስን መስጠት ነው(ሮሜ 12፡1)፡፡ እውነተኛ አምልኮ መድረክ ላይ ከምናደርጋቸው ስርዓቶች ያልፋል፡፡ እግዚአብሔርንም በሚገባ ማወቅ መሠረቱ ነው፡፡
እውነተኛ አምልኮ በኑሮ፣ በዕለት ዕለት በምንሠራው ሥራና ከሰዎች ጋር በምናደርገው ግንኙነት ወዘተ ይገለጻል፤ የእግዚአብሔር ቃል አንዲህ ይላልና፡- “ነጻ የሚያወጣውን ፍጹሙን ሕግ ተመልክቶ የሚጸናበት፣ ሥራንም የሚሠራ እንጂ ሰምቶ የሚረሳ ያልሆነው፣ በሥራው የተባረከ ይሆናል። አንደበቱን ሳይገታ ልቡን እያሳተ እግዚአብሔርን የሚያመልክ የሚመስለው ማንም ቢኖር የእርሱ አምልኮ ከንቱ ነው። ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ፣ በዓለምም ከሚገኝ እድፍ ሰውነቱን መጠበቅ ነው።” (ያዕቆብ 1፡25-25)
እውነተኛ አምልኮ በተግባር የተገለጠ ሕይወትንና ቅድስናን ይፈልጋል ማለቱ ነው፡፡ እነዚህ ሁለቱ ሳይሟሉ የሚደረጉ አምልኮ ተብዬዎች ግርግር ነው የሚሆኑት ማለቱ ነው፡፡ በእርግጥ ወደ ጎን አድናቆት ያተርፉ እንደ ሆነ ነው እንጂ፣ ወደ ላይ አያርጉም፡፡ ወደ ጎን ቲፎዞ ያስገኙ እንደ ሆነ ነው
እንጂ፣ በእሱ ዘንድ ተቀባይ አይኖራቸውም፡፡ የልብ አምላክ ስለሆነ፣ በምድራችን ቋንቋ ፍተሻውን(censorship) አያልፉም::
እውነተኛ አምልኮ ሐቀኝነትን፣ ጥልቅ ንስሐን፣ የተሰበረ መንፈስንና መታዘዝን ይፈልጋል፡፡ ነገር ግን በብዙዎቻችን ዘንድ ብዙ ነገሮች ነካ ነካ(superficial) እየሆኑ መጥተዋል፡፡ በኢሳይያስ ዘመን የነበሩ ሰዎች ከእኛ ዘመን ሰዎች ጋር እጅግ ይመሳሰላሉ፡፡ የጌታ መንፈስ አፋቸውና ልባቸው አልተገናኝቶ ስለሆነበት እንዲህ ብሏቸዋልና፡-
“ይህ ሕዝብ በአፉ ወደ እኔ ይቀርባል(ጸሎትና አምልኮ እንደ ልብ ነው)፣ በከንፈሮቹ ያከብረኛልና ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው”(ኢሳይያስ 29፡13፣ አጽንኦት በእኔ የተጨመረ)
ይህ ሁኔታ በዚህ ዘመን የባሰ አይመስላችሁም? በግሌ እንደዛ አስባለሁ፡: ስለዚህ የሚበጀን ላይ ትንሽ ልበል፡፡ በእውነተኛ መመለስና በተሰበረ ልብ እሱ የሚፈልገውን አምልኮ ለመሰዋት እንችል ዘንድ፣ “ከኔ ምንድነው የምትፈልገው?” እንበለው፡፡ በእርግጥ በፊቱ ከምር ከወደቅን ለእያንዳንዳችን ምን ማድረግ እንደሚገባንና የቱ ጋ መስተካከል እንደሚገባን ያሳየናል፡፡ ያኔ ማለትም ውስጣችን በጸጋው ኃይል ከተሠራ በኋላ፣ ድንቅ አምልኮ ከመንፈሳችን ወደ ላይ ይወጣና ያርጋል፡፡ አዎ፣ ንጉሥ ሰለሞን የሠራው ቤተ መቅደስ ተሠርቶ ከተጠናቀቀ በኋላ፣ የእግዚአብሔር ክብር መቅደሱን እንደሞላው፣ ከተሠራ ማንነት የሚወጣ አምልኮ ልዩ ነው የሚሆነው፡፡
“አቤቱ፥ በውዴታህ ጽዮንን አሰማምራት፤ የኢየሩሳሌምንም ቅጽሮች ሥራ። የጽድቁን መሥዋዕት መባውንም የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በወደድህ ጊዜ፣ያን ጊዜ በመሠዊያህ ላይ ፍሪዳዎችን ይሠዋሉ።” (መዝሙር 51፡
18-19)

ለጠላት - ፊት አይስጡ!

ዲቮሽን 289/07 አርብ፥ ሰኔ 19/07
(በፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)
ለጠላት - ፊት አይስጡ!
የምናመልከው አምላካችን ከሚነድደው ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል፥ ንጉሥ ሆይ! ነገር ግን፥ ንጉሥ ሆይ፥ እርሱ ባያድነን፥ አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድለት እወቅ አሉት (ዳንኤል 3 : 17-18)
ወዳጄ ሆይ፥ የሚያመልኩትን ጌታ ማንነቱን ያውቃሉ? ግርማና ሞገሱን፥ ኃይልና ሥልጣኑን፥ ችሎታ ብቃቱን ጉልበትና ክንዱን ያውቃሉ? እንግዲያውስ ለጠላትዎ ዛቻ፥ ስድብ ማስፈራሪያ አይንቀጠቀጡ! አምላክዎን ካወቁ፥ ለጠላት ፊት አይስጡ!
በባቢሎን አውራጃ በፖለቲካ ሥልጣን ላይ ተሿሚዎች የነበሩ ሲድራቅ ሚሳቅና ሲብደናጎ አምላካቸውን የሚያውቁ፥ አይሁዳዊያን ናቸው፡፡ የመንግሥታቸውን አዋጅ፥ አዋጅ መተላለፍ የሚያመጣውን ቅጣት ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ የንጉሡ ቁጣ፥ የባለሥልጣናቱ አድማ በሕይወታቸው ላይ የሚያስከፍላቸውን ዋጋ ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ ነገር ግን፥ ይህን ሁሉ እያወቁ፥ በነፍሳቸው ተወራርደው ለሐውልቱ ላይሰግዱ፥ ለባለሥልጣናቱ ለንጉሡም ላያጎበድዱ ውሳኔ አደረጉ!
ወገኖች ሆይ፥ ሲድራቅ ሚሳቅ አብደናጎ፥ ለንጉሡ ሐውልት ሰግደው በሕይወትና በምድራዊ ክብር ከመኖር ይልቅ፥ በሚነድደው እሳት መጣልን መረጡ፡፡ ለጣዖት በመስገድ ምድራዊ ሀብትና ሥልጣን ከሚያቆዩ፥ ለሚያመልኩት ጌታ መሰዋት መረጡ!
ወዳጄ ሆይ፥ የሚያመልኩትን ጌታ በእውነት ያውቁታል? ክብርና ሞገሱን፥ ኃይልና ሥልጣኑ ችሎታ ጉልበቱንስ ያውቃሉ? እንግዲያውስ ለጠላት ማስፈራሪያ ወድቀው አይስገዱ! ፈተና ቢነሳ፥ ማዕበል ቢበረታ ለወጀብ ለንውጥውጥታ ፊትዎትን አይስጡ!
ወገኖች ሆይ፥ ዳዊትን ያስቡ! በጎልያድ ፊት ሲቆም ለዛቻ ፉከራው አልተንቀጠቀጠም! ዳንኤልን ያስቡ! በአንበሶች ጉድጓድ ሲጣል የሚያመልከውን ያውቅ ነበርና አልተብረከረከም! ዮሴፍ ለጶጥፋር ሚስት አልተልፈሰፈሰም! ነህምያም ለሰንበላጥ ለጦቢያና ጌሳም የዛቻ፥ የንቀት፥ የመግደል ሙከራ አልተርበደበደም!
ወገኖች ሆይ፥ የሚያመልኩትን አምላክ ያውቃሉ? እንግዲያውስ፥ ለጠላት ፊት አይስጡ!

የማይሰማ ጩኸት !

ዲቮሽን 288/07 ሓሙስ ስኔ 18/07
( ጌታሁን ሓለፎም )
የማይሰማ ጩኸት !
“ጌታ ሆይ ማን ምስክርነታችንን አመነ? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገለጠ ?” (ዮሓ 12፡-38)
ወጭ አውጥቶ፥ ለፍቶበት እና ብዙ ተጨንቆ አስቦ አልሞ ሽር ጉድ ብሎ ያዘጋጀውን ግብዣ ታዳሚው በሰአቱ መጥቶ ሲበላ ሲጠጣ ሲያይ ጋባዥ ደስ ይለዋል ፡፡ ከደስታውም ብዛት “ብሉልኝ ጠጡልኝ ” እያለ አደግድጎ ያስተናግዳል፥ በተለይ እማ የምግቡ ጣእም እና መስተንግዶውን መልካም እንደነበረ እያደንቁ “ አቤት አቤት እንዲህ ነው እንጅ ግብዣ ማለት እጅ ይባረክ ብለናል” እያሉ ስለ ግብዣው ሲያመሰግኑ ሲመርቁ
ጋባዥ ጆሮ ውስጥ የገባ እንደሆነማ ፤ ይኮራል ፤ ሓሴት ያደርጋል ደስታው ወሰን ያጣል ፡፡ ልፋቱ ከንቱ እንዳልቀረ ያስባል ፡፡
ሰው የወለደውን ሲስሙለት ፤ ልጆቹ አድገው ለቁም ነገር ሲበቁለት ፤ ስራውን ሲያደንቁለት ፤ በርታ አይዞህ ሲሉት ይወዳል፡፡ ምክሩ ሲደመጥለት ፤በሸንጎ ለመፍትሄ ሲፈለግ ኩራት ይስማዋል
በአንጻሩ ግን ገንዘቡን አቅሙን አሟጦ ጉልበቱን ያፈሰሰበት ግብዣ ላይ ፤ ታዳሚው ሳይመጣ ቢቀር የተዘጋጀው ድግስ በይ ቢያጣ ፤ ሰው የመከረው ምክር በሰዎች ዘንድ ዋጋ ቢስ ቢሆን ፤ ባይደመጥ ፤ የመፍትሔ ሃሳብ እንዳለው ውስጡ እያወቀ ምክሩን ቢያጣጥሉበት ያ ሰው ይከፋል ያዝናል ፡፡
አዎ እንዲሁ ነው ነብዩ ኢሳያስም ስለ ክርስቶስ እየሱስ ያለውን መረዳት ስለ አምላክነቱ ስለ ጌትነቱ ስለሁሉን ቻይነቱ ስለአዳኝ እና ታዳጊነቱ የገባውን እውነት ቢሰብክ ቢመሰክር ሰዎች ስለአልተረዱት አዘነ ውስጡ ተሰበረ ፡፡ አሻግሮ የመሲሁን መምጣት ቢያይ ፤ በውስጡ የበራለትን ብርሃን ለሰዎች ሊያስረዳ ቢፈልግ ሰሚ ቢያጣ እንዲህ አለ “ ጌታ
ሆይ ማን ምስክርነታችንን አመነ የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገለጠ ?”
“ ጌታ ሆይ ለኛ የተገለጠልንን እውነት የዳንበትን ተስፋ በውስጣችን ያፈሰስከውን የማያሳፍር ፍቅር ለሰዎች ብንናገር ብንመሰክር አላመኑንም ምድር እና ሰማይን የፈጠርክበት ጥበብህ ለማን ተገለጠ ማን ተረዳው እኛም ብንናገር ሊሰሙን ፈቃደኞች አይደሉም ” አለ ፡፡
ዛሬም ቢሆን እንዲሁ ነው የነበያት ጩኸት ሰሚ አጥቷል ፤ የውንጌላዊያን ድምጽ አልተደመጠም የሰባኪዎች ምስክርነታቸው ጆሮ አላገኘም ስለ ጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት የሚነገረው የዛሬ 2000 አመት በፊት ጀምሮ የሚሰበከው ወንጌል በውስጡ ህይወት እያለበት ሰወችን ከሞት የሚታደግ ስልጣን ቢኖረውም ዛሬም ድረስ እየተገፋ ይኖራል
በምትኩ የሰው ልጅ ፡ እግዚአብሔር ለተጸየፈው እና ሓጢያት ነው ብሎ ለጠላው ለዘፈን እና ለዳንኪራ ለተለያየ ክፋት እንድሁም ለርክሰት ሲጋፋ እና አዳራሹን ሲሞላ ሲያጣብብ ፤ በየስፍራው የሰዎች ልጆች በጥፋት ወጥመድ ለመያዝ ሲቸኩሉ ህይወት መንገድ እና እውነት የሆነውን ክርስቶስ እየሱስን ሲገፉ ስለ መሲሁ ሲነገር ሳያደምጡ እና ጆሮ
ሳይሰጡ ዛረም ድረስ አሉ ፡፡
ምናለ ጌታ ሆይ ሰው ሁሉ አንተን አምኖ የዘላለምን ህይወት ቢወርስ ?
ምናለ ጌታ ሆይ በተለያየ እስራት ውስጥ ያለ ወደ አንተ መጥቶ ነጻነትን ፤ መፈታትን ቢያገኝ ?
ምናለ ጌታ ሆይ እንዲያው ይሔ ቃል ለሁሉ ሰው ቢበራለት ? “መዳን በሌላ በማንም የለም ልንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና ” ሓዋ 4፡-12
ምናለ ጌታ ሆይ ይህ የርህራሄ ቃልህ ለሁሉ ቢገለጥ ? “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ህይወት እንዲኖረው እንጅ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ አለሙን እንዲሁ ወዷል እና ” ዮሓ 3፡-16