ዲቮሽን ቁ.20/2007 ማክሰኞ፣ መስከረም 20/2007 ዓ.ም.
(በመጋቢ ተስፋሁን ሐጢያ)
(በመጋቢ ተስፋሁን ሐጢያ)
ነገራችን ሲሰራ!
ነገርን
ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ
ሠራው (መክ 3፡11)
የዓለም
ሕዝብ እነፒካሶን፣ እነማይክል አንጀሎን፣
ለምንድነው
የሚያደንቃቸው?
በቀረጿቸው
እጅግ ውብ የጥበብ ስራዎች
አይደለምን?
መላው ኢትዮጵያዊያንስ እነሜትር አርትስት
አፈወርቅ
ተክሌን
ለምንድነው
የሚያደንቁት?
በሰራቸው
እጅግ ረቂቅ የስነስዕል ስራዎች
አይደለምን?
ለምንድነው
አጼ ላሊበላን የምናደንቀው? በሰራቸው
ፍልፍል
አብያተክርስቲያናት
አይደለምን?
እነዚህ
ሰዎች ስራቸውን እንደ ነገሩ
እንደ ነገሩ አድርገው ሰርተው
ቢሆን ኖሮ ይህን ያህል
አድናቆት
ያገኙ ነበር? በጭራሽ! ይመሰገኑስ
ነበር? በፍጹም!
ሐውልቶች
የመጨረሻውን
ቅርጽ ከመያዛቸው በፊት ይጠረባሉ፣
ይፈለጣሉ!
ድንጋዮቹ
ይቆረቆራሉ፣
ይወቀራሉ፣
ይቀወራሉ፣
ይነረታሉ፣
ይደቆሳሉ!
እንጨቶቹ
ይቆረጣሉ፣
ይመገዛሉ፣
ይገዘገዛሉ!
ድንጋዮቹም
ሆኑ እንጨቶቹ ማራኪ ቅርጽና
ውበት እንዲሰጡ ቀራጺው በሚፈልገው
መንገድ
ያሻቸዋል፣
ይልጋቸዋል፣
ይሞርዳቸዋል፣
ይቀርጻቸዋል!
ቅርጻ ቅርጾቹ የቀራጺውን ችሎታና
ጥበብ የሚገልጹ በመሆናቸው በውበታቸው
እርሱን
በመልካም
እስኪገልጡት
ድረስ ይለፋባቸዋል፡፡ በመጨረሻም ውብ
አድርጎ
በሰራቸውና
በሚኮራባቸው
ቅርጻ ቅርጾች ላይ የስሙን
ፊርማ ያሳርፍባቸዋል፡፡ ዋጋቸውንም እጅግ
ውድ አድርጎ ለሕዝብ እይታ፥
ለገበያም
ያቀርባቸዋል!
ወርቅ የወርቅነት ውበት እንዲኖረው
አንጣሪው
በእሳት
ይፈትነዋል!
በእሳት
አልፎ ያልተፈተነ ወርቅ የወርቅ
ውበት የለውም! የብረት ውበቱም
ያለው በእሳት አልፎ ሲሰራ
ነው፡፡
ሸክላ ሰሪውም ሸክላውን በእሳት
ይፈትነዋል!
የቡና ጀበና እንኳ በእሳት
ይሟሻል!
ያልተሟሸ
ጀበና ዋጋ የለውም!
ታውቃላችሁ፣
እግዚአብሔር
የተመሰከረለት
ቀራጺ ነው! ስለዚህም ልጆቹን
በሚወድደው
መልክ ይቀርጻቸዋል! ያልተሰራ ነገራችንን
እየሰራ፣
ያልተነካ
ቦታችንን
እየነካ፣
ያልቆረጠውን
ቆርጦ እየጣለ፣ ወጣ ገባውን
እያስተካከለ፣
ሸካራውን
እየሞረደ፣
የማይጠቅመው እያስወገደ…ይቀርጸናል!
ታውቃላችሁ፣
በኑሮ ይሁን በማናቸውም ነገራችን
እየቆረቆረንና
እየጎረበጠን
የማይመች
ስሜት እየተሰማን ከሆነ ነገሮቻችን
እየተሰሩ
ነው ማለት ነው! ያሰብነውን
ባለማግኘት፣
ያቀድንበት
ባለመድረስ
እያመመን
ከሆነ እየተሰራን ነው ማለት
ነው!
ወገኖች
ሆይ፣ ስራ ባለማግኘት እየተጨነቅን
እንደሆነ፣
አፍቃሪ
የትዳር
ጓደኛ አላገኘን እንደሆነ፣ ቤት
ንብረት
አላፈራን
እንደሆነ፣
ሁሉ ነገር በጊዜው ውብ
ሆኖ ይሰራልና፣ አይዞን!
በልዩ ልዩ ፈተና ውስጥ
ሆነን እያለቀስን ላለን፣ በሕመም
አልጋ ላይ ላለን፣ በንግድ
ኪሳራ ላይ ላለን፣ በማረሚያ
ቤት ላለን፣ ሁሉ ነገር
በጊዜው
ውብ ሆኖ ይሰራልና፣ አይዞን!
እርሱ በእኛ ሊከብር ነገሮቻችን
እየሰራ
ነው! ሁኔታው ቢያምም፣ ጊዜው
ቢዘገይም፣
ሁሉ ለበጎ ነውና እንቀበለው!
ያየልንን
ለመሆን፥
ፈቅደንና
ታዝዘን፣
እርሱ በሚፈልገው ቅርጽ ተሰርቶ
ለማውጣት
እጃችንን
እንስጥ!
ውድ የሆነ ስራ ጊዜ
ይወስዳልና
በስራ ላይ ቆይቶብንም እንደሆነ፣
የወደፊት
ዋጋችንን
እያሰብን
በትዕግስት
እንሰራ
!
(ይህን
ዕለታዊ
ዲቮሽን
ላይክ እና ሼር ያድርጉ፣
ወዳጅ ጓደኞችዎም እንዲያገኙ ያግዙ፡፡
ዲቮሽኑ
ሳይቋረጥ
ዓመቱን
ሙሉ እንዲቀጥል በጸሎትዎና ጌታ
በልብዎ
በሚያስቀምጥ
ማናቸውም
ነገር ሁሉ ይደግፉ፡፡ ጌታ
ይባርክዎ፡፡)
No comments:
Post a Comment