ዲቮሽን ቁ.19/2007 ሰኞ፣ መስከረም 19/2007 ዓ.ም.
(በመጋቢ ተስፋሁን ሐጢያ)
(በመጋቢ ተስፋሁን ሐጢያ)
የምታየውን ትወርሳለህ!
…ካለህበት
ስፍራ ቀና ብለህ ወደ
ሰሜንና
ወደ ደቡብ ወደ ምሥራቅና
ወደ ምዕራብ ተመልከት፣ ዐይንህ
የሚያየውን
ምድር ሁሉ ለአንተና ለዘርህ
ለዘላለም
እሰጣለሁ።…እንግዲህ ምድሪቱን ስለምሰጥህ
ተነሳ፣
በርዝመቷም፣
በስፋቷም
ተመላለስባት
(ዘፍ 13፡14-17)
በአገራችን
ዐውድ፣
ወርሃ መስከረም በርካታ ሰዎች
ለአዲስ
ነገር ራሳቸውን የሚያዘጋጁበት ነው፡፡ ከእነዚህ
መካከል
ነጋዴዎች፣
ተማሪዎች፣
የቤተክርስቲያን
መሪዎችና
አገልጋዮች
ይገኙበታል፡፡
ሁሉም ሰው በሚሰማራበት መስክ
ስኬታማ
መሆን ይፈልጋል፡፡ ይሁንና የሰው
ልጅ ስለወደፊቱ ሁኔታ እርግጠኛ
መሆን ስለማይችል በፍርሃትና በስጋት
ታጅቦ ወደ ስራ ይገባል፡፡
ታውቃላችሁ፣
ውጤታችን
የሚወሰነው
በራዕያችን
ነው! ራዕያችን ስለ ምግብ፣
ስለ ልብስና ስለ መኖሪያ
ከሆነ፣
እህልና
ውሃ፣ ጨርቅና ታዛ እናገኛለን!
ታውቃላችሁ፣
ውጤታችን
የራዕያችንን
ያህል ብቻ ነው! ዕድገታችን
የራዕያችን
ያህል ነው! ራዕያችን አነስተኛ
ከሆነ አነስተኛ ውጤት፣ መካከለኛ
ከሆነ መካከለኛ ውጤት፣ ከፍተኛ
ከሆነም
ከፍተኛ
ውጤት እናስመዘግባለን!
ታውቃላችሁ፣
ስኬታችን
የራዕያችንን
ያህል ብቻ ነው! ራዕያችን
ትንሽ ከሆነ ትንሽ ስኬት፣
ትልቅ ከሆነ ደግሞ ትልቅ
ውጤት እንጎናጸፋለን፡፡ ራዕያችን የሰፈር
አካባቢ
ብቻ ከሆነ ሰፈራችንን ብቻ፣
ቀበሌያዊ
ከሆነ ቀበሌያችንን፣ ክልላዊ ከሆነ
ክልላችንን፣
አገር አቀፋዊ ከሆነ መላው
አገርን፣
ዓለማቀፋዊ
ከሆነ ደግሞ መላው ዓለምን
እንወርሳለን!
ታውቃላችሁ፣
ማየት የመንፈሳዊ ሰው መሰረታዊ
ብቃት ነው! የእግዚአብሔርን ሰው የእግዚአብሔርን
ሰው ከሚያደርጉ መሰረታዊ መስፈርቶች
አንዱ ራዕይ ነው! ራዕይ
የሌለው
መንፈሳዊ
ሰው በጭለማ እንደሚሄድ ሰው
ነው፡፡
ራዕይ የሌለው ሰው በእውር
ድንብር
እንደሚራመድ
ሰው ነው፡፡ ራዕይ የሌለው
ሰው ተራራ ሸለቆ፣ ወንዙን፣
ውቅያኖሱን፣
ባህሩን
ወጀቡን
መሻገር
አይችልም፡፡
እነዚህን
ካልተሻገረ
ደግሞ መውረስ አይችልም፡፡
በዓለማችን
የተነሱ
‹‹ታላላቅ››
ሰዎች ወደነዚያ ‹‹ታላቅነት›› የደረሱት
በነበራቸው
ራዕይ ነው፡፡ ቶማስ ኤዲሰን
የኤክትሪክ
መብራት
ለመፍጠር
ራዕይ ነበረው፡፡ ከብዙ አድካሚ
ጥረቶች
በኋላ ተሳክቶለታል፡፡ ጆን ኤፍ
ኬኔዲ የሰው ልጅ በጨረቃ
ላይ የማሳረፍ ራዕይ ነበረው፡፡
ዛሬ ጨረቃ የቱሪስቶች መዝናኛ
ሆናለች፡፡
ኮለምበስ
የዓለም
አህጉራት
በንግድ
እንዲተሳሰሩ
ለማድረግ
ብርቱ ራዕይ ነበረው፡፡ ያ
ራዕይ እጅግ ከባድ ፈተናዎችን
በማለፍ
ተሳክቶለታል፡፡
የራይትስ
ብራዘርስ
ሰውን በአየር ላይ የማብረር
ራዕይ ተሳክቷል!
በጦርነት
ዓለምን
ያንበረከኩ
ሰዎች፣
በፍልስፍናቸው
ዓለምን
ያማለሉ
ግለሰቦች፣
በርዕዮተዓለማቸው
ዓለምን
የገዙ የፖለቲካ ሰዎች፣ በበጎ
ስራቸው
የዓለምን
ሕዝብ ልብ ያሸነፉ ሰዎች፣
በእውቀታቸው
የዓለምን
ሕዝብ የረዱ ሳይንቲስቶች፣ ሁሉም ራዕይ
ያላቸው
ናቸው፡፡
ራዕይ ያለው ሰው እይታው
ሰፊ ነው፡፡ ባለራዕይ አሁን
ከሚታየው
ነገር በስተጀርባ ያለውን ተስፋ
ለመያዝ
ይዘረጋል፡፡
ከዛሬው
መከራ ይልቅ ወደፊት የሚጠብቀው
ደስታና
ሐሴት ይታየዋል፡፡ ከአሁኑ ጊዜያዊ
ችግር ይልቅ የወደፊቱ ዘላቂ
መፍትሔ
ይታየዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲ
ተማሪዎች
አብዛኞቹ
ከሚያውቁት
አካባቢ
ወደማያውቁት
ክልሎች
ይሄዳሉ፡፡
ከተወለዱበትና
ካደጉበት
አካባቢ፣
ወደማያውቁት
ክልልና
ወዳልለመዱት
የአየር
ጠባይ ይገባሉ፡፡ ከሞቀ ቤታቸው
ወጥተው
ወደሚደብት
ዶርም ይገባሉ፡፡ ‹‹ከፍትፍቱ ፊቱ››
ከሆነበት
ቤት ወጥተው፣ ‹‹ከፊቱ ፍትፍቱ››
ወደሆነ
ካምፓስ
ይመጣሉ፡፡
እናት በእንጀራ እናት ወደሚተካበት፣
ቤተሰብ
በመጻሕፍት
ወደሚለወጥበት፣
እንቅልፍና
ምቾት በንባብና ውጥረት ወደሚቀየርበት
ዓለም ይገባሉ፡፡
ሆኖም፣
ከዛሬው
ጭንቀትና
መከራና
ውጥረት
ነገ ወዳለው ውጤት ለመድረስ
የስኬት
ራዕይ ሊይዙ ይገባል፡፡ የስኬት
ራዕይ እስከያዙ ድረስ፣ የወደፊት
ስኬታቸው
በተረጋገጠ
ሁኔታ የታወቀ እስከሆነ ድረስ፣
ዛሬ የሚያጋሟቸውን ማናቸውንም ፈተናዎች
በድል ለመሻገር ተግተው ሊሰሩ
ይገባል፡፡
አየሩ፣
አካባቢው
ምግቡ ባይመች፤ ጥናቱ፣ ውጥረቱ፣
ድካሙ ቢያሰለች… እነዚህ ችግሮች
ጊዜያዊ
መሆናቸውን
ማወቅ ይገባል! ፍላጎት ባይሞላ፣
መኝታው
ባይደላ፣
እነዚህ
ችግሮች
ጊዜያዊ
ናቸው! ሁሉም ያልፋል፣ ነገ
ሌላ ቀን ነውና ታሪክ
ይለወጣል!
ስለሆነም
የወደፊት
ራዕይ ሊኖረንና ለዚህም ራዕይ
ልንኖር፣
ተግተንና
ጨክነን
ለራዕያችን
መሳካት
የሚረዳ
ስራ ልንሰራ ይገባል!
(ይህን
ዕለታዊ
ዲቮሽን
ላይክ እና ሼር ያድርጉ፣
ወዳጅ ጓደኞችዎም እንዲያገኙ ያግዙ፡፡
ዲቮሽኑ
ሳይቋረጥ
ዓመቱን
ሙሉ እንዲቀጥል በጸሎትዎና ጌታ
በልብዎ
በሚያስቀምጥ
ማናቸውም
ነገር ሁሉ ይደግፉ፡፡ ጌታ
ይባርክዎ፡፡)
No comments:
Post a Comment