ዲቮሽን ቁ.16/2007 አርብ፣ መስከረም 16/2007 ዓ.ም.
(በፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)
(በፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)
መጀን ለእግዚአብሔር ! መጀን ለእግዚአብሔር ሕዝብ ! !
(በለአም) እንዲህም አለ፦
ባላቅ ከአራም አመጣኝ፥ የሞዓብ
ንጉሥ ከምሥራቅ ተራሮች፤ ና፥
ያዕቆብን
ርገምልኝ፤
ና፥ እስራኤልን ተጣላልኝ ብሎ።
እግዚአብሔር
ያልረገመውን
እንዴት
እረግማለሁ?...እነሆ፥ ለመባረክ ትእዛዝን
ተቀብያለሁ
እርሱ ባርኮአል፥ እመልሰውም ዘንድ
አልችልም።...
በያዕቆብ
ላይ ክፋትን አልተመለከተም፥ በእስራኤልም ጠማምነትን
አላየም፤
አምላኩ
እግዚአብሔር
ከእርሱ
ጋር ነው፥ የንጉሥም እልልታ
በመካከላቸው
አለ። ...በያዕቆብ ላይ አስማት
የለም፥
በእስራኤልም
ላይ ምዋርት የለም፤ በጊዜው
ስለ ያዕቆብና ስለ እስራኤል፥
እግዚአብሔር
ምን አደረገ! ይባላል። (ዘሁልቁ
23)
የምድር
ወገኖች
ሰማያዊ
ወገኖችን
ሁሌም እንደጠሉ፣ እንደተቃወሙና የሚችሉትን ክፉ
ነገር ሁሉ ለማድረግ እንደሞከሩ
ነው! የእግዚአብሔርን ሕዝብ የሚጠሉ
እነዚህ
የአጋንንት
ማህበርተኞች
ሰማያዊ
ወገኖችን
ለማጥቃት
ከሚጠቀሙባቸው
መሳሪያዎች
አንዱ መርገም ነው! አስማተኞችን፣
ጠንቋዮችን፣
መተተኞችና
ሟርተኞችን
በመጠቀም
ሊያጠቁን
ይሞክራሉ፡፡
በመድኃኒት
ቀማሚ፣
በቅጠል
በጣሹ፣
በአፍዝ
አደንግዙም
ሊመቱን
ይፈልጋሉ፡፡
ሆኖም፣
በእኛ ላይ እነዚህ ሁሉ
አይሰሩምና፣
ሙከራቸው
እንደ ከሸፈ፣ እንደ ተሸነፈ
እና እንደከሰረ ነው! ሕዝቡን
የሚጠብቅ
ጌታ አይተኛም፣ አያንቀላፋምና ጠላት ሁሌም
እንደተረታና
በብርቱ
የጌታ እጅ እንደተመታ ነው!
የእግዚአብሔር
ሕዝብ ሆይ፣ በሚበላ ምግብ፣
በሚጠጣ
ውሃ፣ በልብስ በቁሳቁስ ባንተ
ላይ ቢመተት፣ ቢሟረት፣ ቢሰለት፣
በአንተ
ላይ አይሰራምና ደስ ይበልህ!
በልጆች
ቸኮላት፣
ማስቲካና
ብስኩት፣
ደብተር
ስክሪብቶ፣
ከለርና
እርሳስ
ክፉ አይሰራም! የልጆቻችን ውሎ፥
ዴስኩ፣
ጠረጴዛው፣
የምሳ ዕቃና ኮዳው፣ የተጠበቀ
ነው! ታጥቦ በተሰጣ፣ ከላውንደሪ
በወጣ፣
ከሆቴልም
ይሁን ከማርኬት በመጣ ነገር
ላይ ክፉ ሊሰራ አይችልም!
የእግዚአብሔር
ሕዝብ ሆይ፣ ብቻ ክፋት
አይገኝብን
እንጂ፣
ጠማምነት
አይታይብን
እንጂ ለጠላት አትስጋ! ብቻ
አምላክህ
እግዚአብሔር
ከአንተ
ጋር ይሁን እንጂ፣ ለሌላው
አትስጋ!
እግዚአብሔር
ከእኛ ጋር ከሆነ፣ ጠላት
ይነሳል፣
ነገር ግን ተመትቶ ይወድቃል!
ይታገላል
እንጂ አይረታም፣ ይደክማል እንጂ
አይበረታም!
ይሞክራል
እንጂ አያሸንፍም!
የእግዚአብሔር
ሕዝብ ሲያሸንፍ ሁሌም በድንኳናቸው
ምስጋናና
እልልታ፣
ሐሴትና
ደስታ፣
ድግስና
ፌሽታ ይሆናል፡፡ የጠላት ሙከራ
እየተመታ
ሲወድቅ፣
ዝማሬና
እልልታ
በአማኞች
ቤት ሲደምቅ፣ ጠላት ራሱ
ይገረማል፣
ይደነቃል!
ታውቃላችሁ፣
የጠላትን
ስራ ጌታ የሚያፈርሰው፣ ፍላጻውን አምክኖ
ቀስቱን
የሚቀማው፣
ወጥመድን
ሰባብሮ
ሕዝቡን
የሚያስመልጠው
ክብሩን
ለራሱ ሊወስድ ነው! የድል
አጥቢያ
አምልኮ
ከእኛ ፈልጎ ነው! የምስጋና
መስዋዕት
መቀበል
ፈልጎ ነው!
ታውቃላችሁ፣
‹‹ጅራፍ ራሱ ገርፎ፣ ራሱ
ይጮኻል››
እንዲሉ፣
ጠላት ከሙከራው ሽንፈት፣ ከትግሉ
ውርደት
ይቀምስና
ይገረማል፣
ይደነቃል!
ጌታ ለሕዝቡ ባለው ጥበቃ
ሁሌም ይገረማል፣ ሁሌም ይደነቃል!
መልካሙ
እረኛ ሕዝቡን እንዴት እንደሚጠብቅ
ያይና ጠላት ይገረማል! እንደ
አይን ብሌን እንዴት እንደሚጠነቀቅላቸው
ይመለከትና
ይደነቃል!
መርገማቸውን
ወደ በረከት፣ ሞታቸውን ወደ
ሕይወት
እንዴት
እንደሚቀይር
አይቶ ዲያብሎስ ይገረማል፣ ይደነቃል!
መጀን ለእግዚአብሔር ሕዝብ! ሲገፉት
ለማይወድቅ፣
ሲጠሉት
ለሚደምቅ፣
ሲያጠፉት
የሚሰድድ!
መጀን ለእግዚአብሔር፣ ለሕዝቡ ጠባቂ፣
ለምሽግ
ነቅናቂ፣
ጠላትን
አዋርዶ
ምስጋናን
አድማቂ!
(ይህንን
ዕለታዊ
ዲቮሽን
ላይክ ያድርጉ፥ ለወዳጅ ጓደኞችዎም
ያስተላልፉ፡፡
ጌታ ይባርክዎ!)
No comments:
Post a Comment