ዲቮሽን ቁ.7/2007 ረቡዕ፥ መስከረም 7/2007 ዓ.ም.
(በፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)
(በፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)
አቤቱ ሌሊቱን ሁሉ አድረን
ስንደክም
ምንም አልያዝንም፥ ነገር ግን
በቃልህ
መረቦቹን
እጥላለሁ፡፡
ይህንም
ባደረጉ
ጊዜ እጅግ ብዙ ዓሳ
ያዙ፥ መረቦቻቸውም ተቀደዱ (ሉቃ
5፡5-6)
ከጌታ ደቀመዛሙርት መካከል እነ
ስምዓን
ጴጥሮስ፥
ወንድሙም
እንድሪያስ፥
የዘብዴዎስ
ልጆች ያዕቆብና ወንድሙ ዮሐንስ
የአሳ ማስገር ስራ ልሂቃን
(ኤክስፐርቶች)
ነበሩ፡፡
ሌሎቹም
በገሊላ
ባህር አካባቢ ተወልደው ያደጉ
ጥሩ የስራ ልምድ ያላቸው
ነበሩ፡፡
ነገር ግን ሌሊቱን ሙሉ
አንድም
ዓሳ ሳያገኙ አነጉ፡፡ ድካማቸው
ከባድ ነበር፡፡ ወይ ከእንቅልፋቸው
ወይ ከዓሳቸው ሳይሆኑ በኪሳራ
ያደሩ አጥማጆችን ነው ጌታችን
ኢየሱስ
ክርስቶስ
ያገኛቸው፡፡
ሌሊቱን
ሲለፉ ባደሩበት በዚያው ባህር
ላይ "መረባችሁን ጣሉ" ሲላቸው፥
እንደ ባለአዕምሮና በሙያውም ላይ
እውቀትና
ልዩ ችሎታ እንዳላቸው ሰዎች
"አይ፥ እኛ እናውቃለን፥ አይሆንም፡፡"
በማለት
መቃወም
ይችሉ ነበር፡፡
ነገር ግን ተናጋሪው ጌታ
ነውና የራሳቸውን ሰዋዊ "ሎጂክ"
ትተው፥
ለጌታ ወቅታዊ የምሪት ቃል
ታዘዙ፡፡
የእነርሱ
እውቀትና
ልምድ ይህንን መንገድ እንዲከተሉ
ባይፈቅድም፥
የሰሙት
ቃል ሞኝነት ቢመስልም፥ ነገር
ግን ጌታ ቃል ተናግሯልና
እንዳላቸው
አደረጉ፡፡
ያ ሌሊቱን ሙሉ ሲያለፋቸው
ያደረው
ባህር ታዲያ ጌታ ቃል
ተናግሯልና
ታዘዘ፡፡
የዓሳ ክምርም ተፋ! መረባቸው
እስኪቀደድ
ድረስና
የሌሎች
ሰዎችን
እርዳታ
እስኪጠይቁ
ድረስ የአሳ ምርት ተትረፈረፈ፡፡
ታውቃላችሁ፥
ወቅታዊ
የምሪት
ቃል ከድካም ያድነናል፡፡ እውቀታችን፥
ልምዳችን፥
ሎጂካችን
…ሁሉ ሊሰጠን የማይችለውን በረከት
ያጎናጽፈናል፡፡
መንፈሳዊ
ሰው በራሱ ችሎታ ከመደገፍ
ይልቅ በጌታ የምሪት ቃል
መደገፍ
የተሻለ
መሆኑን
ያውቃል፡፡
"ልፋ ያለው አንድ እንጨት
ያስራል"
እንዲሉ፥
የጌታን
ወቅታዊ
ምሪት ከመቀበል ይልቅ በራስ
ችሎታ መደገፍ ከትርፉ ድካሙ
ያመዝናል፡፡
ይህ እንዳይሆን፥ ድምጹን መስማት
ይሁንልን፡፡
መንፈሳዊ
ሰው ወቅታዊ መለኮታዊ የምሪት
ቃል (ካይሮስ-ሬማ) ያስፈልገዋል!
ከእግዚአብሔር
የሆነ ወቅታዊ ቃል ከብዙ
ድካምና
ኪሳራ ያድናል፡፡ እግዚአብሔር ሕያው
መሆኑን
ካመንን፥
ጊዜ የማይለውጠው አምላክ መሆኑን
ካመንን፥
መንፈስ
ቅዱስ ዛሬም ስራ ላይ
መሆኑን
ካመንን፥
ወቅታዊ
ምሪት ሊሰጠን እንደሚችል ደግሞ
ማመን ይገባናል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ
ትናንትና
ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው
ነው፡፡
(ይህን
ዕለታዊ
ዲቮሽን
ላይክ ያድርጉ፥ ለወዳጅ ጓደኞችዎም
ያስተላልፉ)
No comments:
Post a Comment