ዲቮሽን ቁ.1/2007 ሐሙስ፥ መስከረም 1/2007 ዓ.ም.
(በፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)
እግዚአብሔርን እንወቀው፤ የበለጠ እናውቀውም ዘንድ እንትጋ፤ እንደ ንጋት ብርሃን፤ በእርግጥ ይገለጣል፤ ምድርን እንደሚያረሰርስ የበልግ ዝናብ፣ እንደ ክረምትም ዝናብ ወደ እኛ ይመጣል(ሆሴ 6፡3)፡፡
‹‹የእግዚአብሔር ሕዝብ የሚያደርገው እውነተኛ ንስሐ አዲስ የሆነ መንፈሳዊ ሕይወትን ያመጣል፡፡ ከዚያም ሕዝቡ እግዚአብሔርን በሚገባ ማወቅ ሲጀምሩ፣ እርሱ የበለጠ መንፈሳዊ ሕይወትንና በረከትን ለማምጣት እንደ ዝናብ ይመጣል፡፡››
(ምሉዕ ሕይወት መጽሐፍ ቅዱስ፣ ገጽ 1298 የተወሰደ) (ይህን ዲቮሽን ለወዳጅ ዘመድዎ ያስተላልፉ)
No comments:
Post a Comment