Friday, October 3, 2014

የእግዚአብሔርን ልክ አታውቀውም!


ዲቮሽን .4/2007 እሁድ፥ መስከረም 4/2007 ..
(
በፓ/ ተስፋሁን ሐጢያ)

 

ንጉሱ ዖዝያን በሞተበት ዓመት እግዚአብሔርን በረጅምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት ... (ኢሳ 61)

ሰው እግዚአብሔርን ካላየ በስተቀር የእግዚአብሔን ልክ አያውቀውም፡፡ የእግዚአብሔን ልክ የማያውቅ ሰው ደግሞ እግዚአብሔርን በሰው መለኪያ ሊወስነው ይችላል፡፡

እግዚአብሔር በሰው መለኪያ አይወሰንም፡፡ እግዚአብሔር "ትልቅ" ነው! የእግዚአብሔርን ልክ መላእክትም አያውቁትም፡፡ ምክንያቱም ከክብሩ ታላቅነት የተነሳ ፊትለፊት ሊመለከቱት አይችሉምና! ነቢዩ ኢሳያስ ያየው እውነታ ይህ ነው፡፡

የእግዚአብሔር ልክ ከመታወቅ ያልፋል፡፡ ርዝመቱ፥ ስፋቱ፥ ከፍታውና ጥልቀቱ ከመታወቅ ያልፋል! እንደዚህ ያለ አምላክ ማገልገል ትልቅ ዕድል ነው፡፡ በሰው አእምሮ የማይገመተውን ይህን አምላክ ስናመልከው ታዲያ ማንነቱን እያሰብን እንድናመልከው፥ ስናገለግለውም ማንነቱን እያሰብን ልናገለግለው ይገባል፡፡ ይህ ሲሆን ነው የራሳችን ውስንነትና ልኬት በግልጽ የሚገባን፡፡
 (ይህን ዲቮሽን ለወዳጅ ጓደኞችዎ ያስተላልፉ)

No comments:

Post a Comment