ዲቮሽን ቁ.2/2007 አርብ፥ መስከረም 2/2007 ዓ.ም.
(በፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)
(በፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)
ሔኖክ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር አደረገ...ሔኖክም አካሄዱን ከእግዚአብሔር
ጋር ስላደረገ አልተገኘም፥ እግዚአብሔር
ወስዶታልና፡፡
(ዘፍ 5፡22፥24)
እውነተኛ
መንፈሳዊነት
የሚቀዳበት
ምንጩ እግዚአብሔር ራሱ ነው፡፡
ለመንፈሳዊ
ሰው መንፈሳዊነትን ከእግዚአብሔር መቅዳት ምትክ
የሌለው
ምርጫ ነው፡፡ ሔኖክ በዘመኑ
ከነበሩ
ሰዎች ይልቅ፥ ከራሱ ቤተዘመድና
የዘር ሐረግ ይልቅ ተለይቶ
ታወቀ፡፡
ይህም አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ማድረጉ
ነው፡፡
ከዚህም
የተነሳ
በእግዚአብሔር
ራዳር ውስጥ ገባ፡፡ በእግዚአብሔር
ራዳር ውስጥ በመግባቱም ከሰዎች
ራዳር ውጭ ሆነ፡፡ መንፈሳዊ
ሰው ከሰው ራዳር (ወግና
ልማድ፥
ደንብና
አሰራር፥
ፍልስፍናና
ጥበብ፥
ወዘተ ...) ይወጣል፡፡ አካሄዱን ከእግዚአብሔር
ጋር የሚያደርግ ሰው በእግዚአብሔር
መንፈስ
ሉዓላዊ
አሰራር
ውስጥ ይገባል፡፡
(ይህን ዲቮሽን
ለወዳጅ
ዘመድዎ
ያስተላልፉ)
No comments:
Post a Comment