ዲቮሽን 292/07 ሰኞ፥ ሰኔ 22/07
(በእህት ማርታ ሲሳይነህ)
(በእህት ማርታ ሲሳይነህ)
አለጊዜውም ጽና!!!!
እግዚአብሔርን ለምንፈራ ለእኛ፣ ሕይወት ሁልጊዜ አመቺ አይደለችምና፣ ያገኘነውን ያህል ስናጣ፣ ሰማይ ሲከደንብንና፣ መሔጃ መላወሻ ስናጣ፣ ቅድስናችንን ለመጣል፣ ብኩርናችንን ለማቃለል፣ ለጌታ ያለንን ነገር ለማዳፈንና፣ አማራጭ ያልነውን ነገር ለመያዝ እናስባለን። አንዳንዴም፣ በጽድቅና በሐጢያት መካከል ያለው ድንበር፣ ውሉ፣ ይጠፋብንና፣ ስሜታችንን ብቻ ወደ መታዘዝ እናደላለን። እግዚአብሔርን ከመፍራት የሚገኘው በረከትና ጥቅም ሁሉ ትርጉም የሚያጣብን ወቅት
ይኖራል።
ይኖራል።
የሚወዱን ከእኛ በራቁ ጊዜ፣ ብቸኝነት ሲሰማን፣ በቤተክርስትያንም፣ በሰፈርም፣ የምናየው ነገር አላምር ሲለን፣ ሲርበንና ሲጠማን፣ ስንራቆት፣ . . . ሕይወት ዳገት ሲሆንብን፣ ጸንቶ መገኘት እጅግ ፈታኝ ነገር ነው። ቢሆንም ግን፣ ከነገሮች ሁሉ በላይ የሆነውን፣ ኤልሻዳዩን እያሰብን፣ ጸንተን ልንኖር ይገባል። ለዚህም ነው፣ ጳውሎስ፣ አለጊዜውም ጽና በማለት፣ 2ኛ ጢሞ 4፡2 ጢሞቴዎስን የሚመክረው።
መንፈስ ቅዱስ ሆይ፣ ሁሉን ታደርግ ዘንድ በእርግጥ ቻይ ነህና፣ በዚህች ተለዋዋጭ ዓለም ውስጥ፣ ጸንተን እንድኖር እርዳን። ዓለምም በውስጧም ያሉ ገሮች ሁሉ አላፊና ቀሪ መሆናቸውን፣ ትሁት መንፈስ ቅዱስ ሆይ፣ አሁንም፣ አሁንም፣ ደግመህ ደጋግመህ፣ ሳትሰለችና ሳትታክት፣ እባክህ ለነፍሳችን
አስተምራት። እኛም መስማት እንዲሆንልን፣ መንፈሳዊ ዓይኖቻችንን አሁን አብራ። ሰምተህኛልና ተባረክ።
አስተምራት። እኛም መስማት እንዲሆንልን፣ መንፈሳዊ ዓይኖቻችንን አሁን አብራ። ሰምተህኛልና ተባረክ።
ትምሕርቱ ጠቅሞዎታል፣ እንግዲያውስ እባክዎ ላይክ፣ ሼር እና ኮሜንት ያድርጉ፣ ጌታ ይባርክዎ።
No comments:
Post a Comment