Tuesday, June 30, 2015

እንባህን እናፍቃለሁ

ዲቮሽን 291/07 እሁድ፥ ሰኔ 21/07
(በእህት ማርታ ሲሳይነህ)
እንባህን እናፍቃለሁ
እንባህን እያሰብሁ በደስታ እሞላ ዘንድ . . . ። 2ኛ ጢሞ 1፡4
አማኝ መሆን ማለት፣ ውጫዊ መረጋጋት፣ ሰላም ሳይሆን ሰላም ነው ማለት፣ በጌታ መንፈስ ሳይነኩ፣ እንደተነኩ መምሰል፣ መንፈሳዊ ጨዋነት፣ መንፈሳዊ ሰላምታ፣ መንፈሳዊ አንደበት፣ መንፈሳዊ አለባበስ፣ የማስመሰል ቁጥብነት፣ . . . . . . ብቻ ከልብ ያልሆነ፣ ለታይታ ብቻ የምናደርገው ተግባር አይደለም።
አማኝነት፣ እግዚአብሔርን በየእለቱ የማወቅና የመረዳት ሒደት ነው። አማኝ፣ ይወድቃል፣ ይነሳል፣ ያለቅሳል፣ ይስቃል፣ ይጠይቃል፣ ይከፋዋል፣ አምላኬ ወዴት ነህ? ይላል። በግል ጉዳዩም ሆነ፣ በሀገርና በቤተክርስትያን ጉዳዮችም ላይ፣ ያልገባው ነገር ካለ፣ አማኝ ያለቅሳል፤ ይጨንቀዋል፤ ይጠበዋል።
ለዚህም ነው፣ ጳውሎስ፣ “እንባህን እያሰብሁ በደስታ እሞላ ዘንድ ላይህ እናፍቃለሁ፣ በአንተ ያለውን ግብዝነት የሌለበትን እምነትህን አስባለሁ” በማለት ለጢሞቴዎስ የሚጽፍለት።
አባት ሆይ ከማስመሰል ህይወት አውጣንና፣ የቀደመውን እንባችንን እና ቅንነታችንን መልስልን። ግብዝነት እና አስመሳይነት የተሞላው ሕይወታችን ዛሬ ይለወጥ። ሰምተህኛልና ተባረክ።
ትምሕርቱ ጠቅሞዎታል፣ እንግዲያውስ እባክዎ ላይክ፣ ሼር እና ኮሜንት ያድርጉ፣ ጌታ ይባርክዎ።

No comments:

Post a Comment