ዲቮሽን 290/07 ቅዳሜ፥ ሰኔ 20/07
(በዶ/ር በቀለ ብርሃኑ)
(በዶ/ር በቀለ ብርሃኑ)
እውነተኛ አምልኮ
እውነተኛ አምልኮ በእግዚአብሔር ጸጋ ከተለወጠ ልብ ይወጣል፡፡ እውነተኛ አምልኮ ግብዝነት የሌለበትና እግዚአብሔርን በእውነትና በመንፈስ በማወቅ የተመሠረተ ስግደት ነው፡፡ እውነተኛ አምልኮ ራስን መስጠት ነው(ሮሜ 12፡1)፡፡ እውነተኛ አምልኮ መድረክ ላይ ከምናደርጋቸው ስርዓቶች ያልፋል፡፡ እግዚአብሔርንም በሚገባ ማወቅ መሠረቱ ነው፡፡
እውነተኛ አምልኮ በኑሮ፣ በዕለት ዕለት በምንሠራው ሥራና ከሰዎች ጋር በምናደርገው ግንኙነት ወዘተ ይገለጻል፤ የእግዚአብሔር ቃል አንዲህ ይላልና፡- “ነጻ የሚያወጣውን ፍጹሙን ሕግ ተመልክቶ የሚጸናበት፣ ሥራንም የሚሠራ እንጂ ሰምቶ የሚረሳ ያልሆነው፣ በሥራው የተባረከ ይሆናል። አንደበቱን ሳይገታ ልቡን እያሳተ እግዚአብሔርን የሚያመልክ የሚመስለው ማንም ቢኖር የእርሱ አምልኮ ከንቱ ነው። ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ፣ በዓለምም ከሚገኝ እድፍ ሰውነቱን መጠበቅ ነው።” (ያዕቆብ 1፡25-25)
እውነተኛ አምልኮ በተግባር የተገለጠ ሕይወትንና ቅድስናን ይፈልጋል ማለቱ ነው፡፡ እነዚህ ሁለቱ ሳይሟሉ የሚደረጉ አምልኮ ተብዬዎች ግርግር ነው የሚሆኑት ማለቱ ነው፡፡ በእርግጥ ወደ ጎን አድናቆት ያተርፉ እንደ ሆነ ነው እንጂ፣ ወደ ላይ አያርጉም፡፡ ወደ ጎን ቲፎዞ ያስገኙ እንደ ሆነ ነው
እንጂ፣ በእሱ ዘንድ ተቀባይ አይኖራቸውም፡፡ የልብ አምላክ ስለሆነ፣ በምድራችን ቋንቋ ፍተሻውን(censorship) አያልፉም::
እንጂ፣ በእሱ ዘንድ ተቀባይ አይኖራቸውም፡፡ የልብ አምላክ ስለሆነ፣ በምድራችን ቋንቋ ፍተሻውን(censorship) አያልፉም::
እውነተኛ አምልኮ ሐቀኝነትን፣ ጥልቅ ንስሐን፣ የተሰበረ መንፈስንና መታዘዝን ይፈልጋል፡፡ ነገር ግን በብዙዎቻችን ዘንድ ብዙ ነገሮች ነካ ነካ(superficial) እየሆኑ መጥተዋል፡፡ በኢሳይያስ ዘመን የነበሩ ሰዎች ከእኛ ዘመን ሰዎች ጋር እጅግ ይመሳሰላሉ፡፡ የጌታ መንፈስ አፋቸውና ልባቸው አልተገናኝቶ ስለሆነበት እንዲህ ብሏቸዋልና፡-
“ይህ ሕዝብ በአፉ ወደ እኔ ይቀርባል(ጸሎትና አምልኮ እንደ ልብ ነው)፣ በከንፈሮቹ ያከብረኛልና ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው”(ኢሳይያስ 29፡13፣ አጽንኦት በእኔ የተጨመረ)
ይህ ሁኔታ በዚህ ዘመን የባሰ አይመስላችሁም? በግሌ እንደዛ አስባለሁ፡: ስለዚህ የሚበጀን ላይ ትንሽ ልበል፡፡ በእውነተኛ መመለስና በተሰበረ ልብ እሱ የሚፈልገውን አምልኮ ለመሰዋት እንችል ዘንድ፣ “ከኔ ምንድነው የምትፈልገው?” እንበለው፡፡ በእርግጥ በፊቱ ከምር ከወደቅን ለእያንዳንዳችን ምን ማድረግ እንደሚገባንና የቱ ጋ መስተካከል እንደሚገባን ያሳየናል፡፡ ያኔ ማለትም ውስጣችን በጸጋው ኃይል ከተሠራ በኋላ፣ ድንቅ አምልኮ ከመንፈሳችን ወደ ላይ ይወጣና ያርጋል፡፡ አዎ፣ ንጉሥ ሰለሞን የሠራው ቤተ መቅደስ ተሠርቶ ከተጠናቀቀ በኋላ፣ የእግዚአብሔር ክብር መቅደሱን እንደሞላው፣ ከተሠራ ማንነት የሚወጣ አምልኮ ልዩ ነው የሚሆነው፡፡
“አቤቱ፥ በውዴታህ ጽዮንን አሰማምራት፤ የኢየሩሳሌምንም ቅጽሮች ሥራ። የጽድቁን መሥዋዕት መባውንም የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በወደድህ ጊዜ፣ያን ጊዜ በመሠዊያህ ላይ ፍሪዳዎችን ይሠዋሉ።” (መዝሙር 51፡
18-19)
18-19)
No comments:
Post a Comment