ዲቮሽን 307/07፥ ማክሰኞ፥ ሐምሌ 7/07 ዓ/ም
(በእህት ማርታ ሲሳይነህ)
ቆም ብለህ አስብ!!!!
ቆም ብለህ የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ ዐስብ። ኢዮ 37፡ 14
በሕይወታችን ላይ ማዕበል እና ወጀብ ሲበዛ፣ ከቀናነት ይልቅ ጠማማ ነገሮች በከበቡን ጊዜ፣ በድቅድቅ ጭለማና ግራ መጋባት ውስጥ ስንሆን፣ አሰልቺ የሆኑ ነገሮች ሲበዙብን፣ ከንቱ ድግግሞሽ ሕይወት ሲሆንብን፣ ወደ ማን እንሔዳለን? በማያምኑት መሀል ስንከበብ፣ የጨለማው ሥራ የእግዚአብሔርን ብርሐን የደፈነው ሲመስለን፣ በእጃችን የያዝነው ነገር ሁሉ ሲፈርስብን፣ ብቻችንን የሆንን ሲመስለን ወደማን እንሄዳለን? የማንፈልገውን እንጅ የምንፈልገውን ማድረግ ሲሳነን፣ ሥጋችን አርነት ፈልጎ ሲያምጽብን፣ ነፍሳችን የሌለች ሲመስለን ወደማን እንሄዳለን?
በዚህ ጊዜ፣ ማድረግ የሚገባን፣ እስከ ዛሬ ድረስ እግዚአብሔር በእኛም ሆነ በወገኖቻችን ላይ ያደረገውን መልካም ሥራ እያሰብን፣ መጽናናት ነው።
ለዚህም ነው፣ ኤሊሁ፣ ኢዮብን፣ ቆም ብለህ የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ ዐስብ። ኢዮ 37፡ 14 በማለት የሚመክረው።
የእግዚአብሔር ሥራ ድንቅ ነው፤ በተጠበቀው ጊዜና ሁኔታ ሳይሆን፣ በእኔና በእናንተ እይታ እና እቅድ ሳይሆን፣ ኤልሻዳዩ፣ በራሱ ጊዜ እንደቀድመው ዘመን ሁሉ በእያንዳንዳችን ላይ በእርግጥ በድንቅ ስራው ይመጣል።
አባት ሆይ፣ ከከበበን ነገር ይልቅ፣ ከሆንነውም ነገር ይልቅ፣ ካለንበት ሁኔታም ይልቅ አንተ ድንቅ ነህና፣ ተረጋግተን በቦታችን ሆነን እንድናስብህ፣ እንድናከብርህ እና አንተን ብቻ እንድንጨዋወትህ ዛሬ ጸጋህ ይደግፈን ሰምተህኛልና ተባረክ።
------
ዕለታዊ ዲቮሽኑ ጳጉሜ 6/07 ዓ/ም ይጠናቀቃል፡፡ አሁን 59 ቀን ቀርቶታል፡፡

No comments:
Post a Comment