ዲቮሽን 360/07፥ ቅዳሜ፥ ነሐሴ 30/07 ዓ/ም
(በእህት ማርታ ሲሳይነህ)
(በእህት ማርታ ሲሳይነህ)
መታወቅ አለባቸው!!!!!!!
የእኔንም የእናንተንም መንፈስ አሳርፈዋልና፣ እንደዚህ ያሉ ሰዎች መታወቅ አለባቸው። 1ኛ ቆሮ 16፡18
የዚህ ዲቮሽን አጀማመር ትንግርታዊ ነበር፣ ምናልባት አፈጻጸሙም። እኔ ይህን ዲቮሽን መከታተል ከጀመርኩበት ጊዜ አንስቶ፣ አስተያየት ወደ መስጠት እስከተሸጋገርኩበት፣ ከዚያም ዲቮሽን መጻፍ እስከ ጀመርኩበት ጊዜ ያሉት በሙሉ ተዓምራዊ ነበሩ ብላችሁ ምንም ማጋነን አይሆንብኝም። እያንዳንዱ የሚቀርቡትን ጹሁፎች እንደ እግዚአብሔር እለታዊ ቃል በጉጉት ሳነባቸው፣ ስጠቀምባቸው እንዲሁም በተግባር ሲለውጡኝ አስተውያለሁ። እግዚአብሔር በአንድም በሌላም ይናገራል ተብሎ እንደተጻፈ በየእለቱ እግዚአብሔር የሚናገረኝ ነገር ነበረው። ክብር ለመንፈስ ቅዱስ ይሁን።
ጳውሎስ “የእኔንም የእናንተንም መንፈስ አሳርፈዋልና፣ እንደዚህ ያሉ ሰዎች መታወቅ አለባቸው” ብሎ ለቆሮንቶሳዊያኑ እንደሚነግራቸው፣ እኔም በዚህ ዲቮሽን ላይ አስተዋጽኦ ያደርጉ ለነበሩ ሰዎች ይፋዊ ምስጋና እንዳቀርብ ፍቀዱልኝ፣ ወገኖቼ!!!
የመጀመሪያዎቹ ተመስጋኞች እናንተ አንባቢዎች እና አስተያየት ሰጭዎች ቅዱሳን ሁላችሁ ተባረኩ። ምክንያቱም ቃሎቹን እንደ ሰው ቃል ሳይሆን እንደ መለኮት ቃል ተቀብላችኋልና፣ ደግሜ እላለሁ ጌታ ኢየሱስ ይባርካችሁ።
በመቀጠል ወንድሜ ፓስተር ተስፋሁን ሐጢያ፣ ዓመቱን ሙሉ የእግዚአብሔርን ቃል በጹሑፍ ስታቀርብልን የሚያስከፍለው ዋጋ ቀላል እንዳልነበር ለማናችንም ግልጽ ነው። ካለህ ተደራራቢ ሥራዎች፣ አገልግሎቶች፣ እንዲሁም ቤተሰባዊ ኃላፊነቶች ቆርሰህ፣ “ለእግዚአብሔር ሕዝብ ይህን ማድረግ አለብኝ” ብለህ ስለተነሳህ፣ ስላደረግኸውም ኢየሱስ ዘመንህን ይባርክ። ለኔ ደግሞ እንደ ደጉ ሳምራዊ ነህና፣ ደጉ ጌታ ኢየሱስ ከጠበቅኸውም ካሰብከውም በላይ ደግነቱን በዘመንህ፣ በሚመጣው ትውልድህ ሁሉ ይግለጽልህ። “እግዚአብሔር አመጸኛ አይደለም። እርሱ ስራችሁን እንዲሁም በፊትም ሆነ አሁን ቅዱሳንን ለመርዳት ስለስሙ ያሳያችሁትን ፍቅር አይረሳም” ተብሎ በዕብ 6፡10 ላይ እንደተጻፈ፣ ወንድሜ ሆይ! መንፈስ ቅዱስ ካስለመደህ ነገር በበለጠ በአዲስ መገለጥና ክብር ወደ አንተ ይምጣ!!!!
ወንድሜ ጌታሁን ኃለፎም (ጌትሾ)፣ ታቀርብልን ከነበሩ ትምህርቶች በተጨማሪ፣ የዋህነትህን፣ ቅንነትህን፣ ሰው ለማሳደግ ያለህን ብቃትና ጥሪ ሳስብ በእውነት በስርህ ያሉ እህቶችና ወንድሞች ምንኛ የታደሉ ናቸው ብዬ አስባለሁ። ሁልጊዜ የምትሰጠኝ ማበረታቻ ይኼው ለዛሬ ቀን አድርሰውኛል። ወንድሜ ተባረክልኝ። አንተንም ቤትህንም እንግዳ በሆነ ጉብኝት መንፈስ ቅዱስ ይገናኛችሁ!!!!
ወንድም በቀለ በላቸው (ዶር)፣ እንዲሁም ወንድም አበባዬ ቢተው (ጆሲ)፣ ታቀርቡልን የነበረ ትምህርት ትሰጡን የነበረ አስተያየት በእውነት ያለ ዋጋ የሚቀር አይደለምና፣ ጌታ መውጣት መግባታችሁን ሁሉ፣ ቀሪ ዘመናችሁን ሁሉ ይባርክ።
እነዚህን የመሳሰሉ ብዙ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፣ ሸክም የሚሆንብንን ነገር ሁሉ፣ በቀላሉም ተብትቦ የሚከበንን ኃጢያት አስወግደን የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን በፊታችን ያለውን ሩጫ በትእግስት እንሩጥ። እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሶ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና። ዕብ 1፡12
ኢየሱስ ጌታ ነው!!!!!!!
(ከነገ ከጳጉሜ 1 ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 6 ፓስተር ተስፋሁን የሚያቀርብልንን ምክርና ትምህርት እንዲሁም መልእክት አብረን እንከታተል። እወዳችኋለሁ።)
---------
ዕለታዊ ዲቮሽኑ ጳጉሜ 6/07 ዓ/ም ይጠናቀቃል፡፡ አሁን 6 ቀን ቀርቶታል
ዕለታዊ ዲቮሽኑ ጳጉሜ 6/07 ዓ/ም ይጠናቀቃል፡፡ አሁን 6 ቀን ቀርቶታል
No comments:
Post a Comment