Friday, September 11, 2015

አመሰግናለሁ፡፡



አመሰግናለሁ፡፡




የተወደዳችሁ የ2007 ዓ.ም. የፌስቡክ፣ የብሎግ፣ የጎግል ፕላስና የኢሜይል ዕለታዊ ዲቮሽን ተከታታዮች፡፡ ሰላም ለእናንተ ይሁን፡፡

እንኳን ለ2008 ዓ.ም. አደረሰን፡፡

ለድፍን አንድ ዓመት አብራችሁን ስለቆያችሁ ለሁላችሁም ከፍ ያለ ምስጋናዬን እያቀረብኩ፣  በዲቮሽኑ ተጠቃሚ ስለሆኑት፣ ከሐዘናቸው ስለተጽናኑት፣ ጌታን ስለተቀበሉትና፣ ለልዩ ልዩ መንፈሳዊ ጥያቄዎቻቸው ምላሽ ስላገኙት ሁሉ፣ ጌታዬን እጅግ አድርጌ አመሰግናለሁ፡፡  

በዚህ ዓመት ከ50ሺ በላይ ሰዎች ዲቮሽኑን ሲከታተሉ ነበር፡፡ ጌታ ከሞት አስመልጦ ከ2006 ዓ.ም. ወደ 2007 ዓ.ም. ለምን እንዳሳለፈኝ በዚህ ዓመት በጣም ግልጽ ሆኖልኝ ነበር ያሳለፍኩት፡፡


ዕለታዊ ዲቮሽኑ የየዕለት ጫና እየሆነብኝ ሲመጣ፣ ክንዴ እንዳይዝልና የቃሉ አገልግሎት እንይቋረጥ፣ ጌታ እንደ አሮንና ሖር ያሉ ወንድሞችና እህት አስነስቶልኛል፡፡ እነርሱ ልቤን በጣም አሳርፈውታል፡፡


በዚህ አጋጣሚ እናንተን ለማገልግል አብረውኝ ተሰልፈው ለነበሩት፣ ለእጅግ ተወዳጇና ብርቅዬ እህታችን ማርታ ሲሳይነህ፣ የተጣበበ ጊዜውን መስዋዕት በማድረግ ወደ ዙፋኑ ሥር እንድንቀርብ የሚያደሩ መልዕክቶችን በመላክ ላገለገለን አሜሪካዊው ዶ/ር በቀለ ብርሃኑ፣ መንፈሳዊ ጉልበቱና ወንድማዊ ፍቅሩ እንዲሁም እምነቱ ሁሌ መጽናኛዬና ትዝታዬ ለሆነው ጌታሁን ሐለፎም፣ ጽሁፎቹን ስናነብ በወቅታዊነቱና በአርቆ ተመልካችነቱ ሁልጊዜ ከመቀመጫችን ብድግ ብለን ‹‹ኖር›› እንድንለው ያደርገን ለነበረው አበባዬ ቢተው፣ ደግሞም ለእናንተም በንቃት በመሳተፍና ላይክና ሼር በማድረግ እንዲሁም ውይይት በማድረግ ዲቮሽኑ በየዕለቱ ትኩስ፣ በየዕለቱ ተናፋቂ እንዲሆን አስተዋጽኦ ላደረጋችሁ ሁሉ ጌታ ይባርካችሁ ማለት እወዳለሁ፡፡ ለሁላችሁም ሞቅ ያለ ጭብጨባ ይገባችኋል፡፡


ይህን ዲቮሽን ከተከታታዮቻችንም ሆነ ከሌሎች አምስት ሳንቲም ድጋፍ አልተደረገልንም፡፡ በዚህ አጋጣሚ ዓመቱን ሙሉ በንጹህ ገንዘባችን ብቻ ስናገለግላችሁ እንደነበረ ሪፖርቱን ማቅረብ ሁላችንም ንጹህ አዕምሮ እንዲኖረን ይረዳናል፡፡ ለዲቮሽን መጽሐፍ ሕትመት የሚሆን ድጋፍ እንዲደረግ በተደጋጋሚ ጥያቄ ብናቀርብም፣ ማንም ምላሽ አልሰጠም፡፡


ለረዥም ሳምንታት ስንናገር እንደነበረው፣ ዕለታዊ ዲቮሽኑ ዛሬ ጳጉሜ 6 ቀን 2007 ዓ.ም. ዛሬ መጠናቀቁን ይፋ እያደረግሁ፣ ዘንድሮ ጌታ ባስተማረን መንገድ ተከትለን፣ ፌስቡካችንን ለቀልድና ቧልት ሳይሆን፣ ለቁም ነገርና ለብዙዎች መጽናናትና መዳን እንድንጠቀምበት ወንድማዊ ምክሬን እለግሳለሁ፡፡


አሁን፣ ዲቮሽኖቹ ተሰብስበው በመጽሐፍ መልክ እንዲታተሙ ጥረት እየተደረገ ነው፡፡ በገንዘብ አቅም ምክንያት፣ ይህ መጽሐፍ ሳይታተም እንዳይቀር ልባችሁ የተነሣሣና፣ በዚህ ዓመት እናንተ ስታገኙ የነበረውን ወቅታዊ መልዕክት ሌሎቹም በመጽሐፍ ታትሞ እንዲያገኙት የፍቅር ስጦታችሁን እንድትለግሱ፣ በድጋሚ ዕድሉን እሰጣችኋለሁ፡፡ ሕትመቱን ለመደገፍ የምትወዱ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር፣ (ተስፋሁን ሐጢያ ዳካ፣ 1000103090745 ካዛንቺስ ቅርንጫፍ) ገቢ ልታደርጉ ትችላላችሁ፡፡

ጌታ አብዝቶ ይባርካችሁ፡፡

መልካም አዲስ ዓመት፡፡

No comments:

Post a Comment