ዲቮሽን 329/07፥ ረቡዕ፥ ሐምሌ 29/07 ዓ/ም
(በእህት ማርታ ሲሳይነህ)
አንጠመድ!!!!!!!
ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ። 2ኛ ቆሮ 6፡ 14
እንግዲህ ልዩነት መታየት አለበት። አማኝ ነን ካልን፣ የክርስቶስ ተከታዮች ነን ካልን፣ በቃ ያንን በዘመናችን ሁሉ ማሳየት እና ማስመስከር አለብን። እየወደቅንም እየተነሳንም ቢሆን ማሳየት አለብን።
አንዳንዴ እኮ፣ አልፎ ተርፎ ወንጌልን ማድረስ በጥበብ ነው በሚል ሰበብ አጓጉል ፈተናዎች ላይ ራሳችንን ጥለን እንገኛለን። አስተምረን እንለውጣቸዋለን ያልናቸው ሰዎች፣ እነሱ ሳይለወጡ እኛ ወደ እነሱ ተለውጠን፣ የነሱን ጥበብ እና እውቀት የሙጥኝ ብለን የቀረን ስንቶች ነን?
መንፈሳዊ በሚመስል ርህርሄ ውስጥ እንኳን ገብተን ሰጥመን የቀረን ስንቶች ነን? ጓደኞቻችንን፣ ዘመዶቻችንን መስክረን እናመጣለን ብለን ደስ በማይሉ ስፍራዎች እና ቦታዎች ላይ ተነክረን የቀረነውን ቤታችን ይቁጥረው። ለስንት አገልግሎት ስንጠበቅስ ባለህበት ሂድ የምንረግጥ የለንም ብላችሁ ነው? ለስንት ቁም ነገር ስንጠበቅ፣ አልታወቀንም እንጅ ብዙዎቻችን ቀጭጨን ቀርተናል።
እንግዲህ ይበቃል። ዳዊት ሲናገር፣ "ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር የማይሔድ፣ በኃጢአተኞች መንገድ የማይቆም፣ በፌዘኞችም ወንበር የማይቀመጥ" ብሎ (መዝ 1፡1) መክሮናል።
ስለዚህ፣ ቃሉ ራሱ አትጠመዱ ካለን፣ በቃ አንጠመድ!!!!! እንዴት አለመጠመድ ይቻላል? ካልን ወይም ደግሞ ከተጠመድንበት እንዴት መውጣት ይቻላል? ካልን፣ መልሱ አንድና አንድ ነው፣ “ለሚያምን ሁሉ ይቻላል” የተባለው ለእኔና ለእናንተ ነው።
ብሩክ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፣ ታስችለናለህና ተባረክልኝ!!!!
--------
ዕለታዊ ዲቮሽኑ ጳጉሜ 6/07 ዓ/ም ይጠናቀቃል፡፡ አሁን 37 ቀን ቀርቶታል

No comments:
Post a Comment