ዲቮሽን 328/07፥ ማክሰኞ፥ ሐምሌ 28/07 ዓ/ም
(በእህት ማርታ ሲሳይነህ)
(በእህት ማርታ ሲሳይነህ)
ይገስጸኝ!!!!!!!
ጻድቅ በምሕረትህ ይገስጸኝ፣ ይዝለፈኝም። መዝ 141፡5
መቼም ቅምጥልነት የለመድን ሰዎች አለን እንደሆነ፣ ወይም ደግሞ አቢሲኒያዊ ጀግንነት የሚያጠቃን ሰዎች፣ ከምንሰደብ ሞትን እንመርጣለን። አንድ የእግዚአብሔር ሰው መጥቶ፣ ሁልጊዜ ቢያባብለን እንጂ፣ "ከዚህ ጠማማ አካሔድህ እረፍ/እረፊ" ከሚለን፣ ራሳችንን ብናጠፋ የምንመርጥ ብዙዎች አለን። ያው የመጨረሻው ዘመን ስለሆነ በእርግጥ የመንፈሱ አሠራራም በጣም ውስብስብ ስለሆነ አይፈረድብን ይሆናል።
ግን እንዲያው አልፎ አልፎ የሚቆጣን ሰው አያስፈልገንም ትላላችሁ። መቼም ዓለም እና ሰይጣን እያባበሉ እና እያሞካሹ ሲኦል ከሚከቱን፣ አንድ እግዚአብሔር መንፈስ ያለበት ሰው መጥቶ ቢዘልፈን ትርፉ ለእኛ ነው። ግን የእኛም ውሳኔ ያስፈልጋል። እንደ ዳዊት ያለ ልብም ይጠይቃል። ጻድቅ በምሕረትህ ይገስጸኝ፣ ይዝለፈኝም። የኃጢአተኛ ዘይት ግን ራሴን አይቅባ። መዝ 141፡5 ሲል ተናግሯል።
በእርግጥ ወገኖች ሲገስጹን ያማል፣ ግን ለእኛው ፈውስ ነው። የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት ሰው ሲወቅሰን የሚገርማችሁ ነገር፣ እንነቃለን እንጅ፣ እንጠፋም። “በመልእክቴ ባሳዝናችሁም በዚህ አልጸጸትም፤ ብጸጸትም እንኳ መልእክቴ ያሳዘናችሁ ለጥቂት ጊዜ እንደሆነ ተረድቻለሁ። አሁን ግን ደስ ብሎኛል፣ ደስታየም ስላዘናችሁ ሳይሆን፣ ሐዘናችሁ ንስሐ ለመግባት ስላበቃችሁ ነው።” በማለት 2ኛ ቆሮ 7፡8 ላይ ጳውሎስ የሚናገረው።
ስለዚህ እንደ ጳውሎስ ያሉ የሚገስጹ ሰዎች፣ እንደ ዳዊት እና እንደቆሮንቶሳዎያኑ ደግሞ ተግሳጽን የሚሰሙ ሰዎች፣ በዘመናችም ቢበዙ መልካም አይደለም ትላላችሁ? ግን እንዲያው አልፎ አልፎ የሚቆጣን ሰው አያስፈልገንም ትላላችሁ?
ጌታ ኢየሱስ ሆይ፣ ሁለቱንም አይነት ሰወች እባክህ አብዛልን?ወዳጄ ሆይ ተባረክልኝ።
--------
ዕለታዊ ዲቮሽኑ ጳጉሜ 6/07 ዓ/ም ይጠናቀቃል፡፡ አሁን 38 ቀን ቀርቶታል
ዕለታዊ ዲቮሽኑ ጳጉሜ 6/07 ዓ/ም ይጠናቀቃል፡፡ አሁን 38 ቀን ቀርቶታል
No comments:
Post a Comment