Monday, August 3, 2015

እዘረጋለሁ!!!!!

ዲቮሽን 327/07፥ ሰኞ፥ ሐምሌ 27/07 ዓ/ም
(በእህት ማርታ ሲሳይነህ)

እዘረጋለሁ!!!!!

ከኋላየ ያለውን እየረሳሁ ከፊቴ ወዳለው እዘረጋለሁ። ኤፌሶን 2፡19

እንግዲህ አንድ ነገር ልብ በሉ። ኢየሱስ ጌታ ነው። ኢየሱስ በድካማች የሚራራ ሊቀ ካህን ነው። ኢየሱስ ከወንድም ይልቅ የሚጠጋጋ ነው። አየሱስ ታከተኝ ደከመኝ ብሎ ጥሎ የማይሔድ ባልንጀራ ነው። ስለዚህ ምን እናድርግ?

በከፋ ሐጢያት ውስጥ ወድቀን ይሆናል፣ ኢየሱስን እንደሚገባው ሳናስከብረው እስከዛሬ ኖረን ይሆናል፣ በጸያፍ ሕይወት ውስጥ እስካሁኑ ደቂቃ ውስጥ ተዘፍቀን ይሆናል፣ የሆነው ሁሉ ሆነ! የፈሰሰ ውሃ አይታፈስም! ጌታም ይህን እያየ ዝም ብሎናል አይደል? ታዲያ ለምን በንሐ አንመለስም? በሐጢያት እየቆሸሽን እስከመቼ? አንድ ቀን ውጥቅንጡ ሲጠፋን ራሳችንን እየወቀስን፣ ለምን ራሴን አላጠፋም? እኔ ለማን እጠቅመዋለሁ? እያልን ሐጢያታችንን እያስታወስን ለምን የዲያብሎስ ራት እንሆናለን? እንደዚያች ውርጭላ፣ ለጌታ እናስፈልገዋለን!!!!!!!!!!!

ስለዚህ ዛሬ ንስሐ ገብተን፣ በአዲስ ማንነት ለምን አንገለጠም? ለዚያም እኮ ነው፣ ጳውሎስ፣ ከኋላየ ያለውን እየረሳሁ ከፊቴ ወዳለው እዘረጋለሁ። ኤፌሶን 2፡19 የሚለው።

አይዞን! አይዟችሁ!!! እንዲያ ባዋረደን ጠላት ላይ፣ ገና ሳናዋርደው መሞት የለም! ላዋረደን ጠላትማ በበቀል እንወጣበታለን። ተነሱ፣ ጌታ ሰንሰለቱን በጥሶላችኋል።

ጌታ በእርግጥ የሚከብደው አንዳችም ነገር እንደሌለ የምናይበት ዘመን ነው። ይህን የተደበላለቀውን ሕይወታችንን በሰከንድ ውስጥ ሊያጠራው ብቁ ነው!!!!! ይችላል!!!!!!!!!!! የጌታ ፍቅር፣ ስፋቱ፣ ርዝመቱ፣ ከፍታውንና፣ ጥልቀቱን፣ ምን ያህል መሆኑን የምናውቅበት ዘመን ነው! ጌታን ከበፊት ይልቅ እናውቀዋለን፣ እናየዋለን፣ እንዳስሰዋለን! ኢየሱስ እውነተኛ ወዳጅ ነው። አሁን ተነሱ! እንነሳ! ንስሐ እንግባ፣ ሐይላችንን ያድስልናል፣ ጉልበታችንን ያለመልምልናል! እውነቴን ነው የምላችሁ እኮ! ጌታ እውነተኛ አፍቃሪ ነው!!!!

ኢየሱስየ ሆይ፣ እወድሃለሁ። ስለወደድከኝ እወድሃለሁ። ይቅር ስላልከኝ እወድሃለሁ። ሐጢያቴን አይተህ እንዳላየ እያለፍክ፣በብዙ ባስከፋህ እንኳ ስለዛሬዋ እለት ብለህ ዳግመኛ እድል ስለሰጠሕኝ፣ ኢየሱስየ ሆይ፣ ዘመኔን ሁሉ ላንተ አስገዛለሁ። አዎ!!! ላንተ አስፈልግሃለሁ!!!!!! ሰምተህኛልና ተባረክልኝ!!!!
--------
ዕለታዊ ዲቮሽኑ ጳጉሜ 6/07 ዓ/ም ይጠናቀቃል፡፡ አሁን 39 ቀን ቀርቶታል

No comments:

Post a Comment