ዲቮሽን 326/07፥ እሁድ፥ ሐምሌ 26/07 ዓ/ም
(በእህት ማርታ ሲሳይነህ)
(በእህት ማርታ ሲሳይነህ)
ሰይጣን ደስ አይበልህ!!!!!!!
እግዚአብሔርን ለሚወዱትና እንደ ሐሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ተያይዞ ለበጎ እንደሚያደርግላቸው እናውቃለን። ሮሜ 8፡28
ያለነው በመጨረሻው ዘመን ነው። ሰይጣን ጨክኖ ወጥቶአል። ክብራችንን እንድንጥል፣ እንድንዋረድ የማይፈለፍለው ድንጋይ፣ የማይቆፍረው ጉድጉዋድ የለም።
ለአንዳንዶቻችን በተለያየ መልኩ የብርሐን መልዓክ መስሎ፣ ወዳጅ መስሎ፣ አባብሎ፣ የራሱ ሊያደርገን ከዚያም በሲኦል ሊያከማቸን የጨከነበት ሰዓት ስለሆነ ነው በአሳፋሪ ሕይወት ውስጥ የገባነው።
አይግረማችሁ! መጽሐፍ ቅዱሳችሁን ብትጥሉትና ፊታችሁን ወደ ዓለም ዘወር ብታደርጉት ምንም አይግረማችሁ። እናንተ የሚመስላችሁ ራሳችሁ በፈቃዳችሁ እያደረጋችሁት ነው አይደል? አጅሬ ዲያብሎስ ከጀርባው አለ! ተነቅቶበታል!!!!!!
የዘገየ ተስፋችሁን እንደ ትልቅ ነገር እያሳየ፣ ያልተመለሰ ጸሎታችሁን እያሳየ፣ "ኑ ወደ እኔ" እያለ፣ ቤተክርስትያንን በሞራል ትምሕርት ቤትነት ሊተካ እኮ ነው!
የሰይጣን አላማ እኮ፣ ቤተክርስትያንን በዘፋኝ፣ በሰካራም፣ በአመንዝራ ሊሞላ እኮ ነው! ተነቅቶበታል!!!!!!
ዘመናችንን ሊበላ፣ ሊያኝክ፣ ከዚያም ሊውጠን እኮ ነው ለሐጩን እያዝረበረበ ያሰፈሰፈው። አ---ን--ገ---ኝ---ም!!!!! አምልጠናል።
ዛሬ ምን ሁኔታ ላይ ነው ያላችሁት! በምን አይነት ሐጢያት ውስጥ ነው ያለነው? የሆነው ነገር ሁሉ የሆነብን ለበጎ ነው!
ለሰይጣን እንዲህ እንለዋለን። እኔ ግን ወደ እግዚአብሔር እመለከታለሁ። የመድኃኒቴንም አምላክ ተስፋ አደርገዋለሁ። አምላኬም ይሰማኛል። ጠላቴ ሆይ ብወድቅ እነሳለሁና በእኔ ደስ አይበልህ። በጨለማም ብቀመጥ እግዚአብሔር ብርሐን ይሆንልኛልና በእኔ ደስ አይበልህ። በእግዚአብሔር ላይ ኃጢያት ሰርቻለሁና፣ እስኪምዋገትልኝ ድረስ፣፣ ፍርድን ለእኔ እስኪያደርግ ድረስ፣ ቁጣውን እታገሳለሁ። ወደ ብርሐን ያወጣኛል፣ ፅድቅንም አያለሁ። ጠላቴም ታያለህ። እኔንም፣ አምላክህ ወዴት ነው ያለ ሁሉ፣ በእፍረት ይከደናል፣ እንደ መንገድ ጭቃ ይረገጣል።
ኢየሱስ ጌታ ነው! ኢየሱስ ያድናል!!!!!! ሃሌ ሉያ!!!!!! እፎይ!!!!
--------
ዕለታዊ ዲቮሽኑ ጳጉሜ 6/07 ዓ/ም ይጠናቀቃል፡፡ አሁን 40 ቀን ቀርቶታል
ዕለታዊ ዲቮሽኑ ጳጉሜ 6/07 ዓ/ም ይጠናቀቃል፡፡ አሁን 40 ቀን ቀርቶታል
No comments:
Post a Comment