ዲቮሽን
301/07፥
ረቡዕ፥
ሐምሌ
1/07 ዓ/ም
(በፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)
(በፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)
ሁሉ – በክርስቶስ ሲጠቀለል!
በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል
ነው (ኤፌ 1፡10)።
ወገኖች ሆይ፣ የዘመኑ ፍጻሜ ደርሷል! ዘመኑ ሲፈጸም፣ ማለትም፣ በጣም በቅርቡ በሰማይና
በምድር የሚገኙ መንፈሳዊና ቁሳዊ ፍጥረቶች ሁሉ በክርስቶስ ይጠቀለላሉ! ይህ ምን ማለት ነው? ‹‹ይጠቀለላሉ›› ማለት
በክርስቶስ ጠቅላይ አገዛዝ ሥር፣ በመንግሥቱ አስተዳደር ሥር፣ በግዛቱ ሥር፣ በቁጥጥሩ ሥር ይወድቃሉ ማለት ነው!
ወገኖች ሆይ፣ የዘመኑ ፍጻሜ ደርሷል! በጣም በቅርቡ፣ በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት
ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ ጊዜው (ካይሮስ) ደርሷል! ምላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ
ሆነ ይመሰክር ዘንድ ግድ የሚሆንበት ጊዜ (ካይሮስ) ደርሷል (ፊልጵ 2፡10-11) !
ወገኖች ሆይ፣ የዘመኑ ፍጻሜ ደርሷል! የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት
የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደዚህች ዓለም ልኳል(ገላ 4፡4)፡፡ በዚህ የፍጻሜው ዘመን ጊዜ
ውስጥ (ክሮኖስ) የድኅነት ወንጌል ለሰው ልጆች ሁሉ ተገልጧል፡፡ ሆኖም፣ አሁን ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአል
(ሮሜ 13፡11)። እስከዛሬ ከተገለጠው ድኅነት ይልቅ ፍጹም የሆነ ድኅነት በቅርቡ ሊሆን ነው፡፡
ወገኖች ሆይ፣ የዘመኑ ፍጻሜ ደርሷል! ስለሆነም፣ በጣም በቅርቡ፣ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር
ይመጣል፤ የአሁኑ ሰማይና የአሁኑ ምድር ያልፋሉ፤ ሚዲትራኒያን ባሕሩ፣ አትላንቲክ ውቅያኖሱ ለወደፊት አይኖሩም! ሁሉ በክርስቶስ ሲጠቀለል የየአህጉራቱም ይሁን
የመንግሥታቱ ድርጅት አያስፈልጉንም!
ወገኖች ሆይ፣ የዘመኑ ፍጻሜ ደርሷል! ስለሆነም፣ ክርስቶስ በሚመለስበት በጣም በቅርብ ጊዜ፣
ያለ ሰባኪና ያለ አስተማሪ ሁሉ በእርሱ ፊት በግምባራቸው ተደፍተው ይሰግዱለታልና፣ በአንደበታቸው ደግሞ ለእግዚአብሔር አብ ክብር
ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክራሉና፣ የሐይማኖት ተቋማቱ አያስፈልጉንም!
-------------------
ዕለታዊ ዲቮሽኑ ጳጉሜ 6 ቀን 2007 ላይ ይጠናቀቃል፡፡ በዚህ ዓመት ብቻ ዲቮሽኑን የሚከታተሉ ከ15000 በላይ ሰዎች ከመላው ዓለም ማፍራት ተችሏል፡፡ ዲቮሽኖቹ፣ ሰዎች ወደጌታ እንዲመጡ፣ በርካታዎቹም ከውድቀታቸው
እንዲነሱና ከስብራታቸው እንዲጠገኑ፣ በርካታዎቹም እንዲታነጹ … ምክንያት ሆነዋል፡፡ ክብሩን ሁሉ ጌታ ይውሰድ፡፡
እነዚህን ዲቮሽኖች ሰብስቦ በአንድ መጽሐፍ ላይ ለማሳተምና መስከረም 2008 ዓ.ም. ላይ ለአንባቢዎች ለማድረስ እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡ በሀገራችን ታሪክ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነውንና አንድም ቀን
ሳይቋረጥ ዓመቱን ሙሉ ለአንባቢዎች ይቀርብ የነበረውንና በርካታ ነጻ አስተያየቶች ሲሰጡበትና በርካታ ቅዱሳን ሲጸልዩለት ቆይተዋል፡፡
ይህን ታሪካዊ መጽሐፍ፣ የማሳተሚያ ወጭ በገንዘብ ለመደገፍ የምትፈልጉ፣
ወይም ገፆች በመግዛት በመጽሐፉ ላይ የድርጅታችሁንና የአገልግሎታችሁን ዓላማዎች ለአንባቢያን ማስተዋወቅ
የምትፈልጉ፣ ምርቶቻችሁንና ማናቸውንም አገልግሎታችሁን በማስታወቂያ
ማስተላለፍ የምትፈልጉ በሀገር ውስጥና ውጭ የምትገኙ ወገኖች ሁሉ ባሉን ውስን ገጾች ውስጥ አስቀድሞ በመያዝ ራዕዩን መደገፍ ትችላላችሁ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፣ በሞባይል 911-678-158 መደወል ይቻላል፡፡
ዓመቱን ሙሉ አብራችሁን ለነበራችሁ ወገኖች ሁሉ ከፍ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ፡፡ በዲቮሽኑ መቆም ልባችሁ ለሚያዝንብን ወገኖች ደግሞ ከፍ ያለ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ ጌታ ይባርካችሁ፡፡ ፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ
No comments:
Post a Comment