Monday, July 6, 2015

አላወቅህምን? አልሰማህምን ?

ዲቮሽን 299/07፥ ሰኞ፥ ሰኔ 29/07 ዓ/ም
(በፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)

አላወቅህምን? አልሰማህምን ?

አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም (ኢሳ 40:28)

አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ ለደካማ ኃይል ሰጭ፥ ጕልበት ለሌለውም ብርታት ጨማሪ እንደሆነ?

ወዳጄ ሆይ፥ አላወቅህምን? አልሰማህምን? ጎቦዞች ሲደክሙ፥ ደግሞም ሲታክቱ፥ ኃያላንም ሁሉ ፈጽሞ ሲወድቁ - እርሱ ጸንቶ እንዲኖር?

አላወቅህምን? አልሰማህምን? ሰውን የሚያምኑ፥ በሰው ልጆች ላይም የሚተማመኑ ክንዳቸው ሲሰበር ትምክህታቸው ሲፈርስ ፈጽመው ሲወድቁ? አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር አምላክን በመተማመን የሚጠባበቁ ጉልበት ኃይላቸውን እንደሚያድሱ፤ እንደ ንስር ሁሉ ወደ ከፍታቸው በክንፍ እንዲወጡ፤ ሮጠው እንደማይታክቱ፤ ሄደው እንደማይደክሙ?
---------
ዕለታዊ ዲቮሽኑ ጳጉሜ 6 ቀን 2007 ላይ ይጠናቀቃል፡፡ በዚህ ዓመት ብቻ ዲቮሽኑን የሚከታተሉ ከ15000 በላይ ሰዎች ከመላው ዓለም ማፍራት ተችሏል፡፡ ዲቮሽኖቹ፣ ሰዎች ወደጌታ እንዲመጡ፣ በርካታዎቹም ከውድቀታቸው እንዲነሱና ከስብራታቸው እንዲጠገኑ፣ በርካታዎቹም እንዲታነጹ …ምክንያት ሆነዋል፡፡ ክብሩን ሁሉ ጌታ ይውሰድ፡፡
እነዚህን ዲቮሽኖች ሰብስቦ በአንድ መጽሐፍ ላይ ለማሳተምና መስከረም 2008 ዓ.ም. ላይ ለአንባቢዎች ለማድረስ እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡
በሀገራችን ታሪክ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነውንና አንድም ቀን ሳይቋረጥ ዓመቱን ሙሉ ለአንባቢዎች ይቀርብ የነበረውን፥ እንዲሁም በርካታ ነጻ አስተያየቶች ሲሰጡበትና በርካታ ቅዱሳን ሲጸልዩለት የቆዩትን ይህን የጥሞና መጽሐፍ ሁሉም የዲቮሽኑ ተከታታዮችና ሌሎችም ሊያገኙት ይገባል የሚል ራዕይ ተይዟል፡፡
ይህን ታሪካዊ መጽሐፍ፣ የማሳተሚያ ወጭ በገንዘብ ለመደገፍ የምትፈልጉ፣ ወይም ገፆች በመግዛት በመጽሐፉ ላይ የድርጅታችሁንና የአገልግሎታችሁን ዓላማዎች ለአንባቢያን ማስተዋወቅ የምትፈልጉ፣ ምርቶቻችሁንና ማናቸውንም አገልግሎታችሁን በማስታወቂያ ማስተላለፍ የምትፈልጉ በሀገር ውስጥና ውጭ የምትገኙ ወገኖች ሁሉ ባሉን ውስን ገጾች ውስጥ ቦታ አስቀድሞ በመያዝ ራዕዩን መደገፍ ትችላላችሁ፡፡
ሁሉም የዲቮሽኑ ተገልጋይ የነበራችሁ አነሰ በዛ ሳትሉ በዲቮሽኑ የተባረካችሁ መሆኑን የሚያሳይ የፍቅራችሁን ስጦታ ልታበረክቱ ትችላላችሁ፡፡ ለዚህ ጥሪ የምትመልሱት የፍቅራችሁ ምላሽ፥ ለቀጣዩና ጌታ በልቤ ያስቀመጠውን ለየት ያለ አገልግሎት ወደእናንተ ይዤ እንድመጣ የበለጠ የሚያነሳሳኝ መሆኑንም አትርሱ፡፡ ዓመቱን ሙሉ በዲቮሽኑ ስትባረኩበት ነበር፥ አሁን ደግሞ እኔን ለመባረክ ተራውና ዕድሉ ወደእናንተ ቀርቧልና ተጠቀሙበት፡፡ ጌታ ይባርካችሁ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፣ በሞባይል 0911-678-158 መደወል ይቻላል፡፡ ዓመቱን ሙሉ አብራችሁን ለነበራችሁ ወገኖች ሁሉ ከፍ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ፡፡ በዲቮሽኑ መቆም ልባችሁ ለሚያዝንብን ወገኖች ደግሞ ከፍ ያለ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ ጌታ ይባርካችሁ፡፡ የናንተው አገልጋይ፥ ፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ

No comments:

Post a Comment