
( ወንድም ጌታሁን ሓለፎም )
የመጨረሻው
እይታ !!
“ የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደሰጠን እዩ እንዲሁም ነን ፡፡ ” 1ኛ ዮሓ 3፡-1
ክርስቲያን መባላችን ፡- ጉዳዩ መንግስተ ሰማያትን መውረስ እና የዘላለም ህይወትን ማግኘት ፤ የእግዚአብሔር ልጆች ተብሎ የመጠራት እንዲሁም በግዚአብሔር እውቅናን የማግኜት እና ከሀሳቡ ጋር የመስማማት እውነት እስከሆነ ድረስ ፤ የመጨረሻውን እና ውድ የሆነውን ስጦታ መቀበልን የመሰለ ሌላ ወሳኝ እና አስፈላጊ አማራጭ አይኖርም ! እሱም ክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ ነው !
ለምን ቢባል ፡- ወደ እግዚአብሐር አብ ለምምጣትና ለመጠጋት ፤ አባ አባት ብለን በልጅነት ስልጣን እንድንጠራው እና እንድንመላለስ በፊቱም እንደ ልጅ እንድንገባ እና እንድንወጣ የሚያስችለንን ድፍረት ለማግኘት ፤ ከመሲሁ በስተቀር ሌላ መንገድ እግዚአብሔር አብ አላዘጋጀልንም እና ነው !
ይህ ደግሞ የራሱ የእግዚአብሔር ምርጫ እና ሃሳብ እንዲሁም የተቀደሰ ቸርነቱ ነው ፡፡
እግዚአብሔር እኛን እንደ ልጆች ሊቀበለን ፤ ሊያቀርበን ሲፈልግ እንደ መንገድ እና ድልድይ አድርጎ ሊጠቀም የወደደው አንድያ ልጁን ስጦታ አድርጎ ለኛ በመስጠት ነው ፡፡
ለዚህም ነው ሓዋርያው ዮሃንስ ፡- እንዴት ያለ የላቀ ፤ እንዴት ያለ የተመረጠ እንዴት ያለ የተለየ ስጦታ እንደተሰጣችሁ እና እንደተቀበላችሁ እዩ የሚለን ፡፡
ስጦታ ከሌላው ፤ ከተመረጠው ፤ ከብር ከእንቁ ይበልጣል ! ይህ። ስጦታ ከመላእክት ከቅዱሳን ፤ ከፍጥረታት ክብር ይበልጣል !
ስለዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር ምን ያህል የላቀ እንደሆነ አስተውሉ ፤ እዩ ተረዱ !
ስጦታው የመጣው በናንተ ልክ ፤ እናንተ በምትመጥኑት መለኪያ መጠን ሳይሆን በራሱ በእግዚአብሔር መለኮታዊ ሚዛን እና ፈቃድ የመጣ ነው ፡፡
ስለዚህ መንፈሳዊ አይንህ ይገለጥ እና የእግዚአብሔርን እቅድ እይ አንተን ስለወደደህ መለኮት የሆነውን ክርስቶስ ኢየሱስን ሰጠህ ፡፡
ስለዚህ መንፈሳዊ አይንህ ተገልጦ የተሰጠህን ስጦታ አስትውል
እውነት ነው ወገኖቼ ሰው ክርስቶስ እየሱስን ብቼኛ ጌታ እና ብቸኛው አዳኝ አድርጎ በህይወቱ ላይ ለመሾም እና ለመከተል ፡- መንፈሳዊ አይን እና መረዳትን ይጠይቃል ፡፡ በእግዚአብሔር የተወደደ እና የተመረጠው ሃሳብ የትኛው ነው ? ብሎ እራስን መጠየቅን እና እውነቱን የመቀበል ጀግንነትን ይጠይቃል፡፡ ከምንም አይነት ትጽእኖ ነጻ የሆነ እንዲሁም በቃሉ ላይ የተመሰረተ እይታን ድፍረትን ይጠይቃል !
እንግዲህ እኛም ይህ እውነት ገብቶናል ብለን የጌታን መንገድ የምንሮጥ ቅዱሳኖች ፤ ይህን የከበረውን ስጦታና የእግዛብሔር ታላቅ ፍቅር የተገለጠበትን እውነት እንደሚገባ እንድንኖር ጸጋው እንዲያግዘን እንድንጸልይ እና በጽድቅ ለመኖር እራሳችንን እንድናዘጋጅ በጌታ ፍቅር እያሳሰብኩ ፤
ሌሎች ደግሞ ይህ እውነት እንዲበራላቸው እና የእግዚአብሔርን ሃሳብ እንዲረዱ ከመናገር እና ከማሳሰብ ቸል አንበል እላለሁ፡፡
እየሱስ ጌታ ነው !
No comments:
Post a Comment