ዲቮሽን
279/07 ማክሰኞ፣
ሰኔ
9/07
(በፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)
(በፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)
ያደረግነውን
ሁሉ – ብናይ!
እግዚአብሔርም
ያደረገውን ሁሉ አየ፥ እነሆም እጅግ መልካም ነበረ…(ዘፍ 1፡31)።
እግዚአብሔር
አምላክ የመፍጠር ሥራው ሒደት በእያንዳንዱ ዕለት ያደረገውን ሁሉ መለስ ብሎ ያይ ነበር፡፡ የስድስት ቀናቱን የመፍጠር ሥራውን ሁሉ
ሲያጠናቅቅም፣ በአጠቃላይ ያደረገውን ሁሉ እንደ አየ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚመሰክርም፣ ‹‹እግዚአብሔር አምላክ ያደረገው ሁሉ
እነሆ እጅግ መልካም ነበረ›› ይላል!
ወዳጆች ሆይ፣
የምናደርገውን ነገር ሁሉ መለስ ብለን እናያለን? በቀናት ውስጥ ያደረግነውን ሁሉ፣ በሣምንታት ውስጥ ያደረግነውን ሁሉ፣ በወራት
ውስጥ ያደረግነውን ሁሉ፣ በዓመታት ውስጥ ያደረግነውን ሁሉ ወደኋላ ዞረን እንመለከታለን?
ወገኖች ሆይ፣
ያደረግነውን ነገር ሁሉ ወደኋላ መለስ ብለን ብንቃኝ፣ እንዴት እናገኘው ይሆን? ሥራችን ሲታይ፣ ክፉ ሆኖ ይገኝ ወይስ መልካም?
ሁሉ ቻይ የሆነው አምላክ እንኳን ያደረገውን ሁሉ ካየ፥ እኛስ ይልቁንም እንዴት አብልጠን ሥራችንን አንገመግም?
ወገኖች ሆይ፣
እግዚአብሔር አምላክ ያደረገውን ነገር በእያንዳንዲቱ ቀን መለስ ብሎ ካየ፣ እንዲሁም በሥራው ማጠናቀቂያ ላይ አጠቃላይ ግምገማ ካደረገ፣
እኛስ ደካሞችና ልዩ ልዩ ሸክም የከበደብን የሰው ልጆች ሁሉ፣ በየዕለቱና በየጊዜው ያደረግነውን ነገር ሁሉ ወደኋላ መለስ ብለን
ብንቃኝ፣ ሥራችንንና ራሳችንን መመርመር ምንኛ ያስፈልገን ይሆን?
No comments:
Post a Comment