Sunday, June 14, 2015

አዋቂ!!!!

ዲቮሽን 278/07 ሰኞ፣ ሰኔ 8/07
(
በእህት ማርታ ሲሳይነህ)

አዋቂ!!!!

እግዚአብሔር አዋቂ ነውና” 1 ሳሙ 23

እውቀት ያለ ገደብ፣ በሰኮንዶች ሽርፍራፊ ዓለምን እያደረሰበት ያለበት ጊዜ ቢኖር ይህ የኛ ዘመን ነው። በአንድ መንገድ እንገድበው፣ ብንል እንኳን በሌላ መንገድ ይፈሳል። እውቀት እንደ ጅረት ወንዝ የሚፈስበት ዘመን ማለት ይህ ነው። እያንዳንዳችንም ብንጠየቅ፣ አዋቂወች ነን የምንልበት ዘመን ነው-አሁን። ሰው ህይወቱን በእቅድ ለመምራት፣ ዘመናዊ አካሄዶችን ወደ ተግባር የሚለውጥበት ዘመን ነው- አሁን። ከእያንዳንዱ ደቂቃ እስከ ዓመታት ድረስ ለህይወታችን እቅድ እናወጣለን- በዚህ ዘመን። እንደ ካሌንደራችን ካልሔድን ደግሞ፣ እንከፋለን፣ ወይም ሁሉም ነገር የተበላሸ ይመስለናል።

የእግዚአብሔር እውቀት ግን ግሩም ነው። ለኔ እና ለእናንተ ያለው የዘላለም እቅዱና እውቀቱ አንዳንዴ፣ እኛ ምን ያህል ሞኞች እንደሆንን እና የጌታን የእውቀት ፍጽምና ልንመረምረው አለመቻላችን ህይወታችንን ምን ያህል፣ እንደሚያውከው ስንረዳ፣ ወየው! የእግዚአብሔርን ሀሳብ ቀድሜ ባወቅሁኝ ኖሮ እኮ እንዲህ አልኳትንም ነበር እንላለን።

እግዚአብሔር፣ ገና ሳንወለድ ጀምሮ ያለውን ነገር ያውቃል፤ ነገ ምን እንደሚገጥመንም ያውቃል፣ ከዓመታት በኋላም ምን ላይ እንደምንደርስ ያውቃል። ያውቃል። በእርግጥ ያውቃል!!!!

ከእሱ እውቀት ውጭ የሆነ አንዳችም ነገር የለምና፣ ወገኖቼ ሆይ ዛሬ፣ ለኔም ለእናንተም፣ ለሁላችንም ማረፍ ይሁንልን። ብቻ በእግሩ ሥር የሚያስጨንቀንን ሁሉ እየጣልን እንሂድ። እርሱ አዋቂ ነውና፣ ሀሳቡም አይመረመርምና!

አባትዬ፣ እረፉ እኔም አምላክ እንደሆንኩ እወቁ ያልከን ወዳጃችን ሆይ፣ ለዘላለም በክንፎችህ ጥላ ሥር ማረፍ ይሁንልን። ወደ እረፍትህ አስገባን። አዋቂ ነህና፣ ከመቅበዝበዝ ህይወት አውጣን። ውድየ፣ ሰምተህኛልና ተባረክ። እፎይ!!!!
ትምህርቱ ጠቅሞዎታል? እንግዲያውስ እባክዎ፣ ላይክ እና ሼር፣ ኮሜንትም ያድርጉ።

No comments:

Post a Comment