ዲቮሽን 267/07 ሓሙስ ግንቦት 27/07
( በ ወንድም ጌታሁን ሓለፎም )
አሁንም በስራ ላይ ያለ ፀጋ
“ ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና ” ቲቶ 2፡-11
ድሮ ልጆች ሆነን ከሰፈር ጓደኞቼ ጋር ቅዳሜ ፤ ቅዳሜ ለተወሰኑ ወራቶች በየሳምንቱ በነፃ በግ አርደን እንበላ ነበር ፡፡ ይህም አጋጣሚ ያኔ ለኔ እና ለጓደኞቼ ልዩ የሆነን ደስታን
ይፈጥርልን ነበር፡፡
ነገሩ እንዲህ ነው እኛ ከምንኖርባት አስፋቸው ውጫሌ ከምትባል የወረዳ ከተማ ቅዳሜ ቅዳሜ ከተለያየ አቅጣጫ ለመገበያየት ከየገጠሩ የሚመጡትን ሰዎች መንገድ ላይ እንጠብቅ እና ወደ ከተማ አምጥተው ሊሸጡት ያሉትን በግ በ 5 ብር እንገዛቸዋለን፤ ከዚያም በጉን አርደን ሥጋውን ጠባብሰን እንበላና ቆዳውን ለነጋዴ በ 7 ብር እንሸጠዋለን ፡፡
ከዚያም ተበድረን ያመጣናትን 5 ብር ላበደረን ሰው ከፍለን በ 2ቷ ብር ደግሞ ያለ እድሜያችን ለተለማመድነው የተለያየ ሱስ እናውለው ነበር ፡፡
ታዲያ ለተወሰኑ ወራቶች እንዲህ እንደዘለቅን በአንድ ቅዳሜ ቀን 5 ብራችንን ቋጥረን እንደወትሮአችን የተለመደው ቦታ ከገጠሬው በግ ልንገዛ ስንጠብቅ ለካ የበግ ቆዳ 7 ብር እንደሚያወጣ ገጠሬዎቹ ተረድተው ኖሮ “ አንች ኮረኮር (ዱርዪ) ሁላ ቆዲያሽን በ 7 ብር እየሸጥሽ ተኛ በግ በ 5 ብር ትገዣለሽ ? ማንን ነው የምታጃጅይው አሁን አከጅም ወይ ተይህ ” ብለው አስደነገጡን ፤ አባረሩን ፡፡እኛም ከዚያች ጊዜ በሁዋላ ወደዛች ስፍራ ብቅ አላልንም ፡፡
ይገርማል ዛሬም ቢሆን ታዲያ የክርስቶስን ማዳን ፤ የተገለጠውን ሰውን ሁሉ የሚያድነውን የእግዚአብሔርን ፀጋ የውድነቱን ነገር ፤ በጋቸውን በ 5 ብር ገዝተን ቆዳውን በ 7 ብር እንደምንሸጥው ለተውሰነ ወራት እንዳላወቁት ገጠሬዎች ሁሉ ፤ ይህንን ሰውን ሁሉ ሊያድን ከ 2000 አመት በፊት
የተገለጠውን የክርስቶስን የማዳን ፀጋ የዋጋውን ልቀት ተፈላጊነቱን አለም እስከአሁን አላወቀችም ፡፡
ገና በብዙ እስራት እና ቀንበር እንዲሁም በተለያየ ችግር ውስጥ ብዙ ህዝብ ይገኛል ፡፡ ሊገድለው በሚያደባበት የሃጥያት እስራት ውስጥ ዛሬም ድረስ ብዙ ህዝብ ተይዞአል ፡፡ ወደዚህ ዋጋው እጅግ የላቀ ከዘላለም ሞት የሚታደግ ፀጋ መጥቶ ተጠቃሚ አልሆነም ፡፡ ወደ እግዚአብሔር እረፍት ገና አልገባም ፡፡ አስተውሉ የእግዚአብሔር ቃል የሚለን “ ሰውን ሁሉ ፤ አለምን ሁሉ የሚያድን ውድ የሆነ ፀጋ የሚባል የእግዚአብሔር ስጦታ ተገልጧል ፤ የተትረፈረፈ ሃብት ያልጎደለ !እስከአሁንም ብዙዎችን ከሞት ፍርድ ሊያስጥል የሚችል ፤ ለሁሉ የሚበቃ ፤የተጥለቀለቀ በረከት ! ለነፍስ ለስጋ የሚሆን ፈውስ ብዙዎች ከህመማቸው ከችግራቸው ሊላቀቁበት ያላወቁት ያልተገነዘቡት መድሃኒት ! ለሰው ሁሉ የተለቀቀ ቸርነት ! ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ፀጋ ተገልጧል ” የተገለጠው አለሙን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ፀጋ ነፃ ስጦታ ነው ፡፡ ግን ውድ ነው ፡፡
ይህ ወደዚህ ምድር የተገለጠ ፀጋ ሃጢያትን ፤ ጠፊ እና ጊዚያዊ የሆነውን አለማዊውን ምኞት የሚያስክድ ነው ፡፡ ይህ የተገለጠው ፀጋ ፅድቅን ፤ ተስፋን የሚያስተምር የዘላለምን ሂይወት የሚሰጥ ነው ፡፡
ጌታን እንደግል አዳኛችሁ ያልተቀበላችሁ እና ይህንን ዲቮሽን የማንበብ እድል ያገኛችሁ ወገኖች ከዚህ ሰውን ሁሉ ሊያድን ከተገለጠው ከእግዚአብሔር ፀጋ ጋር ተገናኙ እላለሁ እኛም ጌታን እንደግል አዳኝ የተቀበልን ወገኖች ይህን የተገለጠውን ፀጋ እንደሚገባ ማክበር እና መያዝ
እንዲሆንልን ጌታ ይርዳን እላለሁ
ይህ ዲቮሽን ሰው ቢያነበው ይጠቅማል ያስተምራል ብለው ካሰቡ እባክዎ ላይክ እና ሼር በማድረግ ጌታን ያገልግሉ ፡፡ ጌታ ይባርካችሁ ,

No comments:
Post a Comment