Monday, May 4, 2015

ከነሕይወትዎ – እንዳይቀበሩ!

ዲቮሽን 236/07፣ ሰኞ ሚያዚያ 26/07
(
በፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)

ከነሕይወትዎ – እንዳይቀበሩ!
ባለቤትነቱ የአንድ አርሶ አደር የሆነች አህያ፣ ጉድጓድ ውስጥ ወደቀች፡፡ አህያዋ ለሰዓታት የጣር ጩኸት ታሰማ በነበረ በዚያ የጭንቅ ጊዜ፣ አርሶ አደሩ ከጉድጓዱ አፋፍ ላይ ቆሞ የሚያደርገውን ያሰላስል ነበር፡፡ አህያዋ ማርጀቷን፣ ጉድጓዱም መደፈን ያለበት መሆኑን፣ አህያዋን ከጉድጓዱ ማውጣትም የማይጠቅም መሆኑን ይወስናል፡፡
በመሆኑም፣ የመንደሩ ሰዎች ሁሉ መጥተው እንዲረዱት ይጠራቸዋል፡፡ እንደደረሱም በነፍስ ወከፍ፣ ሁላቸውም አካፋ በመያዝ ጉድጓዱን በአፈር መሙላት ጀመሩ፡፡ ጅማሬው ላይ አህያዋ እየሆነ ያለውን ነገር በመረዳቷ የመረረ ጩኸት ታሰማ ነበር፡፡ ከዚያም፣ ሰው ሁሉ እስኪገረም ድረስ መጮዃን አቋረጠች፡፡
ጥቂት አፈር ወደ ጉድጓዱ ከተመለሰ በኋላ፣ አርሶ አደሩ ወደ ጉድጓዱ ተመለከተ፡፡ ባየው ነገርም ተደነቀ፡፡ አህያዋ፣ በጀርባዋ ላይ በሚጣልባት እያንዳንዱ አፈር ላይ የሚያስገርም ነገር ታደርግ ነበር፡፡ አህያዋ አፈሩን ከላይዋ በማራገፍ አንድ ደረጃ ወደ ላይ ከፍ ብላ ትቆም ነበር፡፡
የአርሶ አደሩ ጎረቤቶች በአህያዋ ላይ አፈር መጨመራቸውን በቀጠሉ ቁጥር፣ አህያዋ አፈሩን ከላይዋ ማረገፏንና አንድ ደረጃ ወደ ላይ ከፍ ብላ መቆሟን ቀጠለችበት፡፡ ወዲያውም፣ ሰው ሁሉ እስኪገረም ድረስ አህያዋ ከጉድጓዱ አፋፍ ብቅ በማለትና በፍጥነትም ከጉድጓዱ ወጥታ ልታመልጥ ችላለች፡፡
ኑሮ በእኛ ላይ አፈርና ማናቸውም ዓይነት ቆሻሻዎች ይደፋብናል፡፡ ከጉድጓዱ ማምለጫ ዘዴ ታዲያ፣ የሚደፋብንን ቆሻሻ ከራሳችን ላይ በማራገፍ አንድ እርምጃ ወደላይ መውጣት ይገባል፡፡ እያንዳንዱ ችግራችን መሰላላችን ነው፡፡ ተስፋ ካልቆረጥንና ካልቆምን በስተቀር ከጥልቅ ጉድጓል ውስጥ መውጣት እንችላለን፡፡ እንደ አህያዋ ብልህ እንሁን፡፡ ችግራችንን ከላያችን እያራገፍን፣ ወደ ላይም ከፍ ማለታችንን አንዘንጋ፡፡ አለበለዚያ፣ ከነሕይወታችን ልንቀበር እንችላለን፡፡
ደስተኛ ለመሆን አምስት ቀላል ደንቦች ያስታውሱ፡፡
1.  ልብዎትን ከጥላቻ ነጻ ያድርጉ - ይቅርታ ያድርጉ፡፡
2.  ዓዕምሮዎን ከጭንቀት ነጻ ያድርጉ - ብዙ ጊዜ ይኼ አይሆንም
3.  ቀለል ያለ ኑሮ ይኑ፣ ያለዎትን ያድንቁ
4.  አብዝተው ይስጡ፣
5.  ከሰው ጥቂት ይጠብቁ፣ ግን ከራስዎ ብዙ ይጠብቁ፡፡

(ካነበብኩት)

No comments:

Post a Comment