Friday, May 29, 2015

"ሦስት መንገድ የለም"



ዲቮሽን 261/07 አርብ፣ ግንቦት 21/07
(
በወ/ም አበባዬ ቢተው)


"ሦስት መንገድ የለም"

"በራድ ወይም ትኩስ እንዳይደለህ ሥራህን አውቃለሁ። በራድ ወይም ትኩስ ብትሆንስ መልካም በሆነ ነበር። እንዲሁ ለብ ስላልህ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆንህ ከአፌ ልተፋህ ነው።" (የዮሐንስ ራእይ 3:15-16)

በጽድቅ እና በአመፅ፡ በብርሃን እና ጨለማ፡ በክርስቶስ እና በሰይጣን፡ በእግዚያብሄር ቤተ መቅደስ እና በጣኦት፡ መካከል ምንም ሕብረት የለም። ( 2ቆሮ 14-16)


ወይ ከእግዚአብሄር ጋር ነን ወይ ከሰይጣን። ወይ በኢየሰስ ነነ ወይ በአለም። ሌላ አማራጭ የለም። ተካፋይነታችን ወይ ከጽድቅ ጋር አልያም ከአመፅ ጋር ይሆናል። ወይ ድነናል ወይ ጠፍተናል። በከፊል ልንድን፡ በከፊል ደግሞ ልንጠፋ አንችልም። በከፊል ልናምን በከፊል ልንክድ አንችልም። ወይ በራድ ወይ ትኩስ፡፡

ዘማሪው እንዳለው "ሦስት መንገድ የለም!"

ወገኖቼ ጊዜው አካሄዳችንን ቆም ብለን እንድንመረምር ያስገድዳል። ብዙ ነገሮች መለኪያ አጥተዋል፡፡ ሁሉ ልክ መስሏል። ስህተት ፀንታ ምትኖርበት ምቹ ሁኔታ ይታያል። ሰው ሁሉ በአይኑ ፊት መልካም የመሰለውን ያደርጋል፡ይናገራል።

እኛ እንደ እግዚአብሄር ሰው፡ የጌታ ደቀ መዛሙርት በትክክላኛው ጎዳና ለመጓዝ መጨከን አለብን። ከኃጢያት ጋር መደራደር የለብንም። ከአለማዊ አስተሳሰብ ጋር ልንዳበል አይገባም። እዚህም እዚያም እየረገጥን ቅይጥ ሕይወት በመኖር ጌታን አናከብርም። በአቋማችን፡ በአኗኗራችን በአንደበታችን ሁሉ ጌታን ልንመስል ይገባል።


አትራፊው እና በፍፃሜው የምንሸለምበት ሕይወት ይህ ነው። ጌታ በነገር ሁሉ ማስተዋል ይስጠን!


ትምህርቱ ጠቅሞዎታል? እንግዲያውስ እባክዎ ላይክና ሼር ያድርጉ፣ ጌታ ይባርክዎ።

No comments:

Post a Comment