ዲቮሽን 256/07፥ እሁድ፣ ግንቦት 16/07
(በፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)
(በፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)
ሻሎም
ኤፒስኪያዞ – ለኢትዮጵያ !
ሰላም በምድራችን
እንደ ደመና ግርዶሽ የጸለለ ይሁን! ሻሎም ኤፒስኪያዞ! በመላው ኢትዮጵያ የእግዚአብሔር ሰላም ምድራችንን ይጋርድ! በሰሜን፣ በደቡብ፣
በምዕራብና ምሥራቅ በዋና ከተማው ሻሎም ኤፒስኪያዞ!
በጌታ በኢየሱስ
ስም የእግዚአብሔር ሰላም ለኢትዮጵያዊያን ሁሉ በያሉበት ይሁን! በቆላና ደጋው፣ ደግሞም በወይና ደጋው የእግዚአብሔር ሰላም ምድራችንን
ይጋርድ!
ሻሎም ኤፒስኪያዞ
ለሀገራችን የፖለቲካ ሰዎችና ሻሎም ኤፒስኪያዞ ለፖለቲካቸው! ሻሎም ኤፒስኪያዞ ለከተሞቻችን! ሻሎም ኤፒስኪያዞ ለገጠሮቻችን! ሻሎም ኤፒስኪያዞ ለሲቪሉ ሁሉ!
በጌታ በኢየሱስ
ስም፣ ደመና ምድርን እንደሚጋርድ፣ አቤቱ የእግዚአብሔር ሰላም ኢትዮጵያን ይጋርድ፡፡ ከዚህ የተነሣ የአመጻ መንፈስ፣ የአመጻ ሥራ
የተከለከለ ይሁን! በመላ ሀገሪቱ የእግዚአብሔር ሰላም እንደ ደመና ግርዶሽ የጸለለ ይሁን! ሻሎም ኤፒስኪያዞ!
ሻሎም በአዲስ
አበባ፣ ሻሎም በአዳማ፣ ሻሎም በድሬዳዋ፣ ሻሎም በጋምቤላ፣ ሻሎም በሐዋሣ፣ ሻሎም በአሶሣ፣ ሻሎም በባህር ዳር፣ ሻሎም በመቀሌ፣
ሻሎም በሰመራ፣ ሻሎም በጅግጅጋ፣ ሻሎም በሁሉም ሥፍራ!
No comments:
Post a Comment