ዲቮሽን 239/07 ሚያዚያ 29/07
( በወንድም ጌታሁን ሓለፎም )
እንደ ያቤጽ !
( በወንድም ጌታሁን ሓለፎም )
እንደ ያቤጽ !
"ያቤጽም ከወንድሞቹ ይልቅ የተከበረ ነበረ፡፡ እናቱም በጣር ወልጄዋለሁ እና ብላ ስሙን ያቤጽ ብላ ጠራችው ፡፡
ያቤጽም፡- እባክህ መባረክን ባርክርኝ አገሬንም አስፋው እጅህም ከእኔ ጋር ትሁን፤ እንዳያሳዝነኝም ከክፋት ጠብቀኝ
ብሎ የእስራኤልን አምላክ ጠራ እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው ፡፡" (1ኛ ዜና 4 ፡-9-10)
ለስራ ወደ አንድ እሩቅ ሃገር የሔደ ሰው ፤ በከተማው ውስጥ የሚገኘውን እጅግ የተዋበ የመቃብር ስፍራ እየጎበኜ እያለ ፤ ድንገት በሟቾቹ መቃብር ላይ በእምነ በረድ የተጻፈውን የህይወት ታሪክ እያነበበ መደነቅ ያዘ ፡፡
"አቶ እገሌ በተወለዱ በ 4 አመተቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ ፤ ወይዘሮ እገሊት በተወለዱ በ 6 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ" ይላል፡፡ የመጨረሻው ትልቅ እድሜ "በ10 አመት እድሜአችው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ" የሚል ነበር ፡፡
ጎብኝው በሁኔታው እየተገረመ እያለ ድንገት ዘወር ሲል የመቃብሩን ጠባቂ አየው ጠጋ አለናም ይቅርታ ጠይቆ እንዲህ አለው "ይቅርታ አንድ ነገር ልጠይቅህ በዚህ በሟቾች መቃብር ላይ የተጻፈውን ሳይ የሁሉም ሰው እድሜ የኖሩበት ዘመን ጥቂት ነው እንዲያውም የመጨረሻው ትልቅ ከ 10 አመት አይበልጥም ፎቶአቸው ሲታይ ደግሞ ትልልቆች ናቸው፡፡ ሽማግሌወችም አሉበት ነገሩ ምንድን ነው?" ብሎ ጠየቀው፡፡
የመቃብሩም ጠባቂ እንዲህ ሲል መለሰ "አዎ ልክ ነዎት ጌታው ! እነኝህ የምታያቸው የዚህ አገር ሙታኖች በምድር ላይ አመታት የቆጠሩበት ሳይሆን ተሳክቶላቸው፤ ሃገር ወገን ጠቅመው የኖሩበት ዘመን ነው የተጻፈላቸው ፡፡ እዚህ ሓገር ስርአቱ እንዲሁ ነው ፡፡ ሰው እድሜው የሚቆጠረው ፤ ተሳክቶለት የኖረበት ዘመን ነው እንጂ እድሜ የቆጠረበት አይደለም ፡፡
ጎብኝውም የመቃብሩን ጠባቂ በመገረም እያየ "አሁን እኔ ብሞት ምን ተብሎ ነው ታዲያ የሚጻፍልኝ ? ብሎ ጠየቀው የመቃብር ጠባቂውም "ለመሆኑ ምንድን ነው ስራዎ ጌታው" ሲል ጎብኝውን ጠየቀ ጎብኝውም ስራውን ነገረው የመቃብር ጠባቂውም " አይ ጌታው እርሶወማ ገና ከናታቸው መህጸን እንደወጡ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ ነው የሚባልሎት" ብሎት አረፈ፡፡ ነገሩ ፈገግ ቢያሰኝም ትንሽ ቁም ነገር ቢጤ አይጠፋውም፡፡
መጥሃፍ ቅዱሳችን ውስጥ ስናይ "እገሌ እገሌን ወለደ ፤ ሞተም እገሌ እገሌን ወለደ ሞተም የሚል የብዙ ሰዎች ስም ዝርዝር ተጽፎ እናገኛለን ፡፡
በዚህች ምድር በቅ ብለው የጠፉ፤በልተው ጠጥተው ትዳር ይዘው ልጅ ወልደው ከብደው ዘር የተኩ፤በዘመናቸው ነግደው ያተረፉ፤ አርሰው ያመረቱ ግን ኖረው ኖረው ሞቱ የተባሉ ከምድር ያለፈ ታሪክ የሌላቸው መጽሃፍ ቅዱሳችን ውስጥ ብዙ አሉ፡፡
ደግሞም የጊዜያዊውን ከዘላለሙ የከበረውን ከተዋረደው የሚረባውን ከማይረባው የለዩ ለእግዚአብሔር መንግስት ደፋ ቀና ብለው ያገለግሉ ታላላቅ መንፈሳዊ ገድልን ያስመዘገቡ እንደነ ያቤጽ ያሉ ጸሎቶቻቸው በላይ በአርያም የተሰማ ለትውልድ መባረክ ምክኒያት የሆኑ ጌታ ሰምቶ የልባቸውን መሻት የሰጣችው ስማቸው በወርቅ መዝገብ የተጻፈ ሞልተዋል፡፡
ያቤጽ በውንድሞቹ መካከል የተከበረ በእግዚአብሔር ዘንድ ጸሎቱ የተሰማለት ሰው ነበር፡፡ ያቤጽ የሚለው የስሙ ትርጉም ሲታይ የጭንቅ ሰው፤የጣር ሰው ማለት ነው ነገር ግን ለራሱ የነበረው ግምት ከስሙ ትርጉም ለየት ያለና የራቀ ነበር፡፡ እኔ የበረከት ሰው ነኝ አለ፤ እጸልያለሁ እግዚኣብሔር ይሰማኛል እኔን ቤተሰቤን ብቻ አይደለም ይሄ የታመንኩት ጌታ ትውልድንም የሚለውጥ ብቃት አለው ጸሎቴንም ይሰማል አለ ጸለየ እግዚአብሔርም ሰማው ፡፡
ለመሆኑ እኔና እርስዎ በዚህ ምድር ይሁን በሚመጣው የእግዚአብሔር መንግስት ምን የሚነገር የሚጻፍ ታሪክ አለን ? አይገርምወትም ዛሬም እንደ ያቤፅ ያሉ ለትውልድ ለውጥ የሚያመጣ ጸሎት የሚጸልዩ የእምነት ሰዎችን እግዚብሔር ይፈልጋል፡፡
አይገርሞትም እኔና እርስዎ በውነት ለምድራችን ለወጎኖቻችን መባረክ ምክኒያት ልንሆን እንችላለን፡፡ እስኪ የከበረን ነገር እናስብ ፤ እስኪ ፍቅር ያለበትን ደህንነት ያለበትን እንፈልግ ይቅርታ ያለበትን እናሰላስል በውነት ጌታ ይሰማናል ፡፡
ትምህርቱ ይጠቅም ከሆነ ላይክ እና ሼር ያድርጉ ጌታ ይባርክዎ !

Today I was thinking about this word,thanks to Holy spirit,and to you too.
ReplyDeleteIt is an amazing preaching. Thanks a lot May God impart you more wisdom's.
ReplyDelete