Monday, May 18, 2015

እንበልጣለን!!!

ዲቮሽን 249/07፥ እሁድ፥ ግንቦት 9/07
(በእህት ማርታ ሲሳይነህ)

እንበልጣለን!!!

በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን (ሮሜ 8፡ 37)።

በህይወታችን ላይ አሸናፊዎች መስለው ወይም ሆነው የሚታዩን፣ እጅግ በርካታ ነገሮች አሉ። ምናልባትም፣ ራሳቸውን አሸናፊ ብለው የጠሩ፣ እኛም ተሸንፈንላቸው ያሉ ነገሮች ይኖራሉ።

አንዳንዶቹ የሐጢያት አይነቶች ይሆናሉ። የሚመላለሱብን ሐጢያቶች ይኖሩብንና፣ ተሸንፈንላቸው ተቀምጠን ይሆናል። ወይም ደግሞ ያልተመለሱ ጸሎቶቻችን ይሆናሉ፤ ወይም ደግሞ በሥራ ቦታችንም ሆነ በቤታችን፣ በፋይናንሳችንም ሆነ በአገልግሎታችን ላይ፣ ገናና ሆነው የተቀመጡ እጀግ ብዙ ነገሮች ይኖራሉ። እኛም፣ እጅ ወደላይ ብለን የተማረክንላቸው ብዙ ጉዳዮች ይኖራሉ።

ስለዚህ ዛሬ፣ እንዲህ እንላቸዋለን። “በወደደን በኢየሱስ እንበልጣችኋለን!!!!”
 
እኛ፣ በከበረ ስሙ የተጠራን፣ ክርስቲያኖች ከኢየሱስ ድንቅ ኃይል የተነሳ፣ ከመስቀሉ ሥራ የተነሳ፣ ድል ነሽነዎች እንጂ ድል ተነሽዎች አይደለንም። ማራኪዎች እንጅ፣ ተማራኪዎች አይደለንም። ብርቱዎች እንጅ ደካሞች አይደለንም። ጠንካሮች እንጅ ሰነፎች አይደለንም። የሚገዳደሩንን ሁሉ ዛሬ በወደደን በእርሱ እንበልጣቸዋለን። ያዛሉንን፣ ያለፉንን፣ ያደከሙን እነሱን፣ ዛሬ ቃል እናወጣባቸዋለን። ተገዳዳሪዎቻንን ሁሉ፣ በኢየሱስ ስም ዛሬ እንበልጣቸዋለን።

ኢየሱስ ሆይ፣ ብርቱ የሆኑብንን ሁሉ በከበረ ደምህ ስላሸነፍክልን፣ እጅግ አድርጌ አመሰግንሃለሁ። ከስምህ ስልጣን በላይ የሆነ አንዳችም ነገር ስለሌለ፣ ክብር ምስጋና፣ አምልኮና፣ ስግደት ላንተ ብቻ እናቀርባለን። ሰምተህኛልና ተባረክ።

No comments:

Post a Comment