Friday, April 17, 2015

ለመዳን ብቸኛው መንገድ!




ዲቮሽን 218/07 ሐሙስ፣ ሚያዝያ 8/07 /
(በወንድም ጌታሁን ሓለፎም)


ለመዳን ብቸኛው መንገድ!
" እኔ መንገድ እና እውነት ህይወትም ነኝ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም "ዮሓ 14-6
ለተራበ ማብላት ፤ለታረዘው ማልበስ ፤ለጠማው ማጠጣት የተጨነቀን አይቶ አይዞህ ብሎ ማጽናናት ይህ ሁሉ መልካም ተግባር እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኙ፡ለመንፈስም ሰላም እናን እርካታን የሚሰጡ ተግባሮች ናቸው ፡፡
ሰው ልቡ ቅን ቢሆን፡ አይምሮው፡ ፍቅር ያለበትን ቸርነትን እና በጎ ነገር የበዛበትን ቢያስብ፡ ይህ በእግዚአብሔር የተወደደ እና በሰዎችም ዘንድ የሚያስመሰግን ነው፡፡
ሰው መንፈሱን እና ሥጋውን አስገዝቶ በፆም በፀሎት ቢያደክም አንደበቱን ከክፋት ተቆጣጥሮ እግሩን ከጥፋት ቢመልስ ፡እርግጥ ነው ህይወቱ ይለመልማል ክፉ ዘመንን ይሻገራል ጌታም ደስ ይለዋል፡፡
ነገር ግን ይሄ ሁሉ መልካም ተግባር ወደ መንግስተ ሰማያት በር አያቀርብም ወደ መግቢያው አያደርስም ወደ ውስጥም አያስገባም፡፡ባጠቃላይ ከንቱ ልፋት ነው ፡፡
በሓ 10 ላይ የምናገኘው ተወዳጁ ሰው ቆርኖሊዮስ ከቤተሰቦቹ ጋር እግዚአብሔርን የሚያመልክ፤ለህዝብ ሁሉ ምጽዋትን የሚሰጥ ፤ወደ እግዚአብሔር ዘወትር የሚጸልይ ሰው ነበረ፡፡ይህም ተግባሩ እግዚአብሔርን ደስ አሰኝቶት ነበር ፡፡በዚህም ምክኒያት እግዚአሔር መላኩን ልኮ እንዲህ አለው " መላእኩም አለው ጸሎትህና ምጽዋትህ በእግዚአብሔር ፊት ለመታሰቢያ እንዲሆን አረገ ፡፡
አሁንም ወደ እዮጴ ሰወችን ልከህ ጴጥሮስ የሚባለውን ስምኦንን አስመጣ ፤እርሱ ቤቱ በባህር አጠገብ ባለው በቁርበት ፋቂው በስምኦን ቤት እንግድነት ተቀምጦአል ፡፡ ልታደርገው የሚገባህን እሱ ይነግርሃል፡፡" ጴጥሮስም መጥቶ ስለጌታ አዳኝነት ሰበከው ቆርኖሊዮስም ከነ ቤተሰቡ አምኖ ተጠመቀ፡፡

አያችሁ ምንም እንኩዋን ፤ቆርኖሊዮስ በጸሎት እጅግ የተጋ ፤ምጽዋትን የሚያደርግ እግዚአብሔርንም የሚፈራ ሰው ቢሆንም ቅሉ ፤ሌላ አስረግጦ ሊያውቀው የሚገባ ጉዳይ ነበረው ፡፡እሱም መንገድ እውነት ህይወት የሆነውን የመንግስተ ሰማይ መግቢያ ቁልፍ የያዘውን ክርስቶስ እየሱስን ነው፡፡
የዛሬ 2ሽህ አመት በፊት በሓዋ 2 ላይ እንደምናነበው በባእለ ሃምሳ እለት ሁለት አይነት ጉባኤዎች በእየሩሳሌም ተሰብስበው ነበር፡፡ሃይማኖትን ሊፈጽሙ ከሰማይ በታች ያሉ በጸሎት የተጉ ብዙ ህዝብ ግን የዘመኑን የእግዚአብሔርን ፕሮግራም ያላወቁ ፤የአለም ቤዛ የሆነውን የክርስቶስ እየሱስን አዳኝነት ያልተገነዘቡ ፤ግን እግዚአብሔርን የሚወዱ አጥብቀው የሚጸልዩ ሃይማነተኞች ፤በሌላ ወገን ደግሞ የክርስቶ እየሱስን ትእዛዝ ተቀብለው በተስፋ የመንፈስ ቅዱስን መገለጥ የሚጠብቁ 120 የማይበልጡ ጥቂት ሰወች ታዲያ የጌታ መንፈስ በነብዩ እዩኤል የተነገረውን የተስፋ ቃል ሊፈጽም ሰማያትን ሰንጥቆ የመጣው እና መንፈስ ቅዱስ ተገልጦ ጸጋን የሰጠው ለነዚሁ ዳግም ለተወለዱ መንገድ እውነት እና ህይወት የሆነውን ክርስቶስ ኢየሱስን ለተቀበሉ 120 ብቻ ነበር ፡፡
ዛሬም ብዙዎች መንግስተ ሰማያትን ለመውረስ ልዩ ልዩ ተግባሮችን ይፈጽማሉ፤ገንዘባቸውን ለድሃ ያካፍላሉ፤በጾም እና በጾሎት ይተጋሉ ጽድቅ ነው ብለው ባሰቡት መንገድ ይሄዳሉ ይሄ ሁሉ መልካም ቢሆንም ጌታም ደስ ቢስኝበትም ጉዳዩ መንግስተ ሰማያትን የመውረስ እስከሆነ ድረስ አለም ሁሉ ይድንበት ዘንድ አሳልፎ በመስቀል ላይ ከሰጠው በአንድያ ልጁ በክርስቶስ ኢየሱስ በስተቀር መንግስተ ሰማይ የሚያስገባ ሌላ አማራጭ የለም፡፡
" የዘላለም ሕይዎት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ ይህንን ጽፌላችሁ አለሁ ፡፡ " 1 ዮሓ 5-13
አዎ በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ብቻ ለሚያምን የዘላለም ህይወት አለው !!
በዚህ የጌታ ቃል ካመኑበት እባክዎ ላይክ እና ሼር በማድረግ ጌታን ያገልግሉ ! ጌታ ይባርክዎ !

No comments:

Post a Comment