ዲቮሽን ቁ. 208/07፣ ሰኞ፥ መጋቢት 28/07 ዓ.ም.
(በፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)
(በፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)
ፍለጋውን – እንከተል !
የተጠራችሁለት
ለዚህ ነውና፤ ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና። እርሱም ኃጢአት አላደረገም፥
ተንኰልም በአፉ አልተገኘበትም፤ ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም መከራንም ሲቀበል አልዛተም፥ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ
ሰጠ፤ (1 ጴጥ 2፡21-23)
ከደርግ ውድቀት ወዲህ በኢትዮጵያ አብያተክርስቲያናት መካከል አለመግባባቶች እየጨመሩ መጥተዋል! በማናቸውም
ኅብረቶች መካከል አለመግባባቶች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን በሀገራችን የሚታዩ አለመግባባቶች በአብዛኛው አንዱ ሌላውን
ለማዋረድ፣ ለማጥቃት፣ ለማጥፋትና ለማፍረስ ታሳቢ የሚያደርጉ ናቸው! አንዱ ሌላውን ለማሸነፍ በጠቅላላ ጉባኤዎችና በመገናኛ ብዙሐን ከሚያስተላልፈው
ውግዘት በተጨማሪ፣ በአሕዛብ ፍርድ ቤቶች ጠበቃ አቁሞ በመከራከር አሕዛብ የጌታን ስም እንዲሰድቡ በር ይከፍታል!
ወገኖች ሆይ፣ ክርስቶስ በግፍ መከራ በምንቀበልበት ጊዜ ልንከተላቸው ስለሚገቡ መርሆዎች ከራሱ
ሕይወት ምሣሌ ትቶልናል! ይህም ማለት፣ በግፍ መከራ በምንቀበልበት ጊዜ የእርሱን ምሣሌ እንድንከተል ተጠርተናል ማለት ነው!
ወገኖች ሆይ፣ በግፍ መከራ በምንቀበልበት ጊዜ ብዙ ኃጢአት እንሠራለን! ክፉ በሚሠሩብን ላይ
ክፉ፣ ተንኮል በሚያደርጉብን ላይ ተንኮል፣ በሚሳደቡን ላይ ስድብ፣ በሚዝቱብን ላይ ዛቻ እንመልሳለን!
ታውቃላችሁ፣ በግፍ መከራ በምንቀበልበት ጊዜ ልንከተላቸው ስለሚገቡ መርሆዎች ክርስቶስ ከራሱ
ሕይወት ምሣሌ ትቶልናል! ክርስቶስ በግፍ መከራ በተቀበለ ጊዜ በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ!
ታውቃላችሁ፣ ክርስቶስ በግፍ መከራ በተቀበለ ጊዜ ራሱን አልተከላከለም! ሲሰድቡት፣ ሲደበድቡት፣ ሲያዋርዱትና
ተንኮል ሲያደርጉበት እንደ ከሳሾቹ፣ እንደ ተንኮለኞቹ፣ አጸፋ አልሰጠም! ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው
ለጻድቅ ፈራጁ ራሱን አሳልፎ ሰጠ!
ወገኖች ሆይ፣ ከኢየሱስ እንማር! በግፍ መከራ በምንቀበል ጊዜ የእኛን ነገር፣ የእኛን ጉዳይ፣ ከፍ
ባለ ዙፋኑ ተቀምጦ ላለው፣ ለጻድቅ ፈራጁ ለሕያው እግዚአብሔር አሳልፈን እንስጠው!
------------------------------------------
(ትምህርቱ ጠቅምዎታል? እንግዲያውስ ላይክ ያድርጉ፣ ጌታ
ይባርክዎ!)
No comments:
Post a Comment