ዲቮሽን 220/07፥ ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 10/07 ዓ/ም
(በዶ/ር በቀለ ብርሃኑ)
የውስጡ መንፈሳችን እንዲጠነክር!
(በዶ/ር በቀለ ብርሃኑ)
የውስጡ መንፈሳችን እንዲጠነክር!
የክርስትናን ተግዳሮት ጥሶ ለመቀጠል፣ የመንፈሳችን መጠንከር እጅግ ወሳኝ እንደ ሆነ የታመነ ነው፡፡ መንፈሳችን
በተገቢው ሁኔታ ካልጠነከረ፣ ጫናዎችን መቋቋም ስለሚያቅተን በቀላሉ ተልፈስፍሰን እንወድቃለን፡፡ መነሣቱም ሌላ የቤት
ሥራ ይሆናል፡፡
ሐዋርያው ጳውሎስ በኤፌሶን 3፡16-19 በእርሱ ዘመን በብዙ ተግዳሮትና መከራ ያልፉ ለነበሩ ክርስቲያኖች እንዲህ ብሎ ጸልዮላቸዋል (ዘርዝሬ እንድጽፋቸው ይፈቀድልኝ)፡-
(1ኛ) በመንፈሱ በውስጥ ሰውነታችሁ በኃይል እንድትጠነክሩ፣ (2ኛ) ክርስቶስም በልባችሁ በእምነት እንዲኖር፣ (3ኛ) የእናንተ ሥርና መሠረት በፍቅር ይጸና ዘንድ፣ (4ኛ) ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ስፋቱና ርዝመቱ ከፍታውም ጥልቅነቱም ምን ያህል መሆኑን ለማስተዋል፣ (5ኛ) ከመታወቅም የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ ትበረቱ ዘንድ፣ (6ኛ) እስከ እግዚአብሔርም ፍጹም ሙላት ደርሳችሁ ትሞሉ ዘንድ እጅግ አስደናቂ ጸሎት ነው፡፡
በግሌ ባነበብኩት ቁጥር ከባድ ጉጉትን ስለሚፈጥርብኝ፣ አዘውትሬ የማሰላስለው ምንባብ ነው፡፡ ይህንን ጸሎት በግለሰብ ደረጃ ደጋግመን ሳናቋርጥ ለራሳችን ልንጸልየው ይገባል የሚል እምነት አለኝ፡፡ በዚህ ጽሑፌ “በመንፈሱ በውስጥ ሰውነታችሁ በኃይል እንድትጠነክሩ” በሚለው ሐሳብ ላይ አተኩራለሁ፡፡
ለክርስትያን “የመንፈስ መጠንከር” ዋጋ ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ ነው፡፡ መጽሐፍ ነቢዩ ኤልያስ ከዚያ ከነበረበት ድካም መብልም በልቶ እንደበረታ፣ በዚያም ኃይል ያንን የእግዚአብሔር ተራራ ያለ ድካም እንደወጣ ይናገራል (1 ነገ 19፡8)፡፡ እኛም ከፊት ለፊት ያለውን የክርስትና ተግዳሮት ጥሶ ለማለፍና ፍልሚያ የሚጠይቀውን ሕይወት ለማሸነፍ፣ እግዚአብሔር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያቀረበልን መንፈሳዊ ምግብ ሳናሰልስ ልንበላ ይገባናል፡፡
ልናጠናው፣ ልናሰላስለው ይገባል፡፡ ታዲያ ያኔ ነው መንፈሳችን የሚጠነክረው፡፡ ያኔ ጸያፍ ነገሮችንና ከእግዚአብሔር ሐሳብ ያፈነገጡ ነገሮችን እምቢ ለማድረግ በቂ አቅም ይኖረናል፡፡ ቀድሞ ውስጣችን በደህናው ጊዜ የሰበሰብነውና የግል ያደረግነው ቃል መንፈሱን እንዳሳዝን ጉልበት እንደሚሆነን ንጉሥ ዳዊት ሲገልጽ፣ “አንተን እንዳልበድል ቃልህን በልቤ ሰወርሁ” (መዝ 119፡11) ብሎ ተናግሯል፡፡ ይህ አገላለጽ ቀድሞ የቤት ሥራ እንዳለን በግልጽ የሚያሳይ ነው፡፡
አዎ! ቃሉ በልባችን ጽላት ላይ መጻፍ ይገባዋል፡፡ ቃሉን በልባችን የምንሰውርበት መንገድ ደግሞ፣ ከቃሉ ጋር የምናደርገው ያላሰለሰ ቁርኝት መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ በሌላ በኩል የውስጡ መንፈሳችን እንዲጠነክር ካስፈለገ፣ ዕለት ተዕለት መታደስ አለበት (2ቆሮ 4፡16)፡፡ ለዚህ ደግሞ በቀጣይነት ሳናቋርጥ በጸጋው ዙፋን ፊት መውደቅ ይኖርብናል፤ መቃተት ይኖርብናል፤ አብዝተን መጮኽ ይገባናል፤ እንዲህ ተብሎ ተጽፏልና፡- “እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ” (ዕብ 4፡16)፡፡
ባጭሩ ይህ ክፍል በራሳችሁ ምንም ማድረግ አትችሉም፤ የሚደግፍና የሚያጠነክር ነገር ያስፈልጋችኋል ማለቱ ነው፡፡ በመጨረሻም ቃሉን በተግባር ደረጃ መለማመድ፣ ማለትም ወደ መንፈሳችን የሚመጣውን ምሪት በመታዘዝ እሺ ብሎ ማድረግ መንፈሳችንን ያጠነክረዋል፡፡ እያንዳንዱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የሚስማማ ውሳኔ፣ ርምጃና ተግባር በቀጣይ የሚመጡ ፈተናዎችን ለማለፍ እንደ መልካም አጋጣሚ ሊታይ ይችላል፡፡
ወደ ምድር አውርደን እንግለጸው ከተባለ፣ መንፈሳችን ሲጠነክር፣ ኃጢአትን “እምቢ” የማለት አቅምን እናገኛለን – የበደሉንን ይቅር ማለት አይከብደንም – ያለ ስስት “መቆረስ” ቀላል ይሆንልናል – ወደ ፊት ፈተና ሲመጣም አንርበተበትም – እንዳውም በጽናት እንጋፈጠዋለን – በቀላሉ ስልቹና ታካች አንሆንም ስለዚህ የውስጡ መንፈሳችን እንዲጠነክርና በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ የማፍራት ብቃት እንዲኖረን ከምንጩ ጋር በሚገባ እንጣበቅ! ተባረኩ!
----------
ወንድማችን ዶ/ር በቀለ መልዕክቱን ከወደዳችሁለት ዘወትር ቅዳሜ በዲቮሽናችን ላይ ሊያገለግለን ይችላልና እስኪ ፍቅራችሁን ግለጹለት፡፡ መልዕክቱን ላይክ ያድርጉ፡፡

No comments:
Post a Comment