ዲቮሽን 214/07፥ እሁድ፣ ሚያዝያ 4/07 ዓ/ም
(በፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)
(በፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)
‹‹ኢየሱስ ተሰርቋል››!
እኛ
ተኝተን ሳለን ደቀ መዛሙርቱ በሌሊት መጥተው ሰረቁት በሉ። ይህም በገዢው ዘንድ የተሰማ እንደ ሆነ፥ እኛ እናስረዳዋለን እናንተም
ያለ ሥጋት እንድትሆኑ እናደርጋለን አሉአቸው። እነርሱም ገንዘቡን ተቀብለው እንደ አስተማሩአቸው አደረጉ። ይህም ነገር በአይሁድ
ዘንድ እስከ ዛሬ ድረስ ሲወራ ይኖራል (ማቴ 28፡13-15)።
በጣም የሚገርም ነገር ነው፣
ጌታ ከሞት እንደሚነሣ ከሦስት
ጊዜ በላይ ያስተማራቸውን ደቀመዛሙርቱ ድብን
አርገው
ረስተዋል፡፡
ከሦስት
ቀን በኋላ፣ ከሞት እንደሚነሣ
የተናገረውን
የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ግን ሊረሱት አልቻሉም፡፡ ለዚህም ነው፣ እስከሦስተኛው
ቀን ድረስ ከመቃብሩ ደጃፍ ማንም እንዳይጠጋ ማሕተሙን አትመው፣ ጥበቃው እንዲወጠር ትዕዛዝ ያስተላለፉት፡፡
ወገኖች ሆይ፣ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያኑ ጌታን ቢያስገድሉም፣ በዚህ አላረፉም! ከሙታን ቢነሣ፥ የሚከተለውን ጉድ ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ ‹‹በሐሰት አትመስክር›› የሚለውን ሕጋቸውን ጥሰው፣ ንጹሁን ሰው በሐሰት አስመስክረው ከባድ ኃጢአት ሠርተዋል፡፡ ይህን ኃጢአት እንደሠሩ ሕሊናቸው ያውቃል፡፡ ለዚህም ነው፣ ወደ ባለሥልጣኑ ሄደው፣ ‹‹የኋለኛይቱ ስሕተት ከፊተኛይቱ ይልቅ የከፋች ትሆናለችና መቃብሩ እስከ ሦስተኛ ቀን ድረስ በጥብቅ እንዲጠበቅ ብለው የጠየቁት፡፡
ታውቃላችሁ፣ የሐይማኖት መሪዎች ፈርሃ
እግዚአብሔር ሲጥሉ፣ የንጹሐንን ደም በከንቱ በማፍሰስ ጥፋት ያደርሳሉ! ፈርሃ እግዚአብሔር የሌላቸው መሪዎች የሰሩትን ኃጢአት በሌላ
ኃጢአት ለመሸፈን ይንቀሳቀሳሉ! የአይሁድ መሪዎች፣ የአስቆሮቱን ይሁዳ በገንዘብ ደልለው ጌታን ሰቅለውታል፡፡
ይህም ብቻ አልበቃም፣ ከሞትም ሲነሣ ወታደሮቹንና ባለሥልጣናቱንም በገንዘብ ደልለው አስተባብለዋል፡፡
ወገኖች ሆይ፣ ፈርሃ
እግዚአብሔር የሌላቸው መሪዎች የሠሩትን ኃጢአት ለመሸፈን የሚሠሩት ሥራ ሁሌ አይሣካምና፣ የጌታ ትንሣኤ ለአርባ ቀናት ሁሉ ለብዙዎች
ታየ፣ የወጉት እያዩት በክብር ደመና ወደ ላይ አረገ፡፡
ታውቃላችሁ፣ ፈርሃ እግዚአብሔር የሌላቸው
መሪዎች አንዳንዴ የሚጫወቱት ፖለቲካ የሚገርምና የማይመስል ነው፡፡ ጌታ በተያዘ ጊዜ ጥለውት
የሸሹ፣ በሞት ፍርሃት ተይዘው ወደየአቅጣጫው የተበታተኑ፣ በገረድ ፊት የካዱት፣ ተነስቷል ተብሎ ሲነገራቸው እንኳ የተጠራጠሩ ደቀመዛሙርት፣
ከአውሬ ይልቅ የሚያፈሩ የሮማ ወታደሮችን ደፍረው፣ የጌታን አስከሬን ሰረቁ፣ ብሎ ማስወራት የማይመስል ጨዋታ ነው!
ታውቃላችሁ፣ የወታደሮቹ ተኝተው ሳሉ
አስከሬን ተሰረቀ ብሎ ማስወራቱም፣ የማይመስል ጨዋታ ነው! አስቡት እስኪ፣ ‹‹ያ አሳች በሕይወቱ ገና ሳለ። 'ከሦስት ቀን በኋላ እነሣለሁ' ብሏልና፣ ከሞት እንዳይነሳ መቃብሩ
በጥብቅ ይጠበቅልን ብለው የአይሁድ መሪዎች አመልክተው፣ በከፍተኛ ባለሥልጣን ትዕዛዝ የተመደቡ ወታደሮችን ‹‹ተኝተው አደሩ›› ብሎ
ማስወራቱ የማይመስል ነው፡፡ ተኝተውስ ከሆነ አስከሬኑን የሰረቀው ማን እንደሆነ እንዴት ሊያውቁ ቻሉ?
ወገኖች ሆይ፣ ጌታችን ሲነሣ የሮማ ወታደሮች
ተኝተው አልነበረም! ይልቁንም፣ ጦርና ጋሻቸውን፣ ሰይፍና ጭሬያቸውን በተጠንቀቅ ይዘው፣ አካባቢውን
ሁሉ በከፍተኛ ጥርጣሬ እየቃኙ ሳለ፣ የጌታ መልአክ ከሰማይ ስለ ወረደ፡፡ ይህን ተከትሎ ምድር ተናወጠ፡፡ ይህን ተከትሎ የጌታ
መልዐክ የመቃብሩን ድንጋይ አንከባለለውና በላዩ ተቀመጠ፡፡ መልኩም እንደ መብረቅ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበረና ወታደሮቹም
እርሱን ከመፍራት የተነሣ ተናወጡ እንደ ሞቱም ሆኑ። ይኼ ነው እውነቱ! ታዲያ ይኼ እውነት ሪፖርት ሲደረግ፣ መነገር ያለበት፣
‹‹ከትንሣኤው የተነሣ ወታደሮቹ እንደሞቱ ሆኑ፣ እሩሃቸውን ሳቱ፣ ፌንታ ሠሩ›› ነው እንጂ ‹‹ወታደሮች ተኙ›› ተብሎ
አልነበረም!
ወገኖች ሆይ፣ ‹‹የኋለኛይቱ ስሕተት ከፊተኛይቱ
ይልቅ የከፋች ትሆናለችና መቃብሩ እስከ ሦስተኛ ቀን ድረስ በጥብቅ እንዲጠበቅ ብለው የጠየቁት፣ ትንሣኤ ፈርተው ነው! በሐሰት መስክረው
የገደሉት ጌታ ሞትን አሸንፎ የተነሣ እንደሁ፣ ምን ሊከተል እንደሚችል ጠንቅቀው ያውቃሉ! በተዋረደ ስፍራ ተወልዶ ያደገው፣ በሐሰት
ተከስሶ በውርደት ሞቶ በውርደት የተቀበረው፣ መቃብር ፈንቅሎ ቢነሣ የትንሣኤው ዜና ምድርን እንደሚሞላ ልባቸው ያውቀዋል!
ታውቃላችሁ፣ የተፈራው አልቀረምና፣ ኢየሱስ
ተነሣ! ለፍርሃታቸውም ስልታዊ እቅድ ነበራቸውና መቃብር ፈንቅሎ የተነሣውን ጌታ ‹‹ተነስቷል›› ከማለት ‹‹ኢየሱስ ተሰርቋል››
ብለው የውሸት አዋጅ አስለፈፉ! ይኼ ውሸታቸው እስከዛሬ ድረስ መላው አይሁዶችን በድቅድቅ ጨለማ እንደዋጠ ነው፡፡
ወገኖች ሆይ፣ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን
ሕግና ነቢያት የተናገሩለትን፣ ሰብዓ ሰገሎቹ የመሰከሩለትን፣ መጥምቁ ዮሐንስ የዓለምን ኃጢአትን የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ
መሆኑን የመሰክረለትን፣ ሰማያት ተከፍተው የእግዚአብሔር ልጅነቱን በገዛ ቋንቋቸው ያረጋገጡለትን፣ መሲሁን ኢየሱስ ሲሰብክ ሲያስተምርም
በአይነሥጋቸው የተመለከቱትን፣ ሌላም ሌላም እውነት ክደው፣ የሚመሩትን ሕዝብ ከብርሃን አስተው ለ2000 ዓመታት በድቅድቅ ጨለማ
ጥለውት አለፉ፡፡
ታውቃላችሁ፣ መሪዎች የሚመሩትን ሕዝብ
አንድም ወደ ብርሃን፣ አሊያም ወደ ጨለማ ሊከትቱ ይችላሉ፡፡ ለዚህም ነው፣ የእስራኤል ሕዝብ፣ ላለፉት 2ሺ ዓመታት በድቅድቅ ጨለማ
ውስጥ ያሉት! ከኢየሱስ ሌላ መዳን በሌላ በማንም የለምና ከአይሁድ መሪዎች የተነሣ እስራኤላዊያን ጌታ ኢየሱስን እንደ ግል አዳኛቸው
አድርገው ሳይቀበሉ ወደ ሲኦል እየወረዱ ያሉት!
ወገኖች ሆይ፣ ለመላው እስራኤል መዳን እንዲሆን እንጸልይላቸው! መላው የሰው ልጆች ጌታን
ተቀብለው ድነት እንዲያገኙ እንጸልይላቸው! ይህን መዳን እኛም እንዳንል ጥንቃቄ እናድርግ!
መልካም የትንሣኤ በዓል!
No comments:
Post a Comment