Wednesday, March 25, 2015

በቴኦሎጂ ዶክትሬት የጫኑ – ለምን ያመነዝራሉ?



ዲቮሽን .196/07፣ ረቡዕ መጋቢት 16/07 ..
(
በጆን ፒፐር)

በቴኦሎጂ ዶክትሬት የጫኑ ለምን ያመነዝራሉ?

የገዛ ሕይወትህን፣ ቤተክርስቲያንህንም ተመልከት፡፡ ምን ያህል ክርስቲያኖች  እግዚአብሔርን የበለጠ ለማወቅ ሲተጉ ታያቸዋለህ – በሙሉ ኃይላቸው ዝቅ ብለው የበለጠውን እውነት፣ የበለጠ አጥርተው፣ በበለጠ ጣዕም ለማወቅ ጥረት እያደረጉ ነው? ወይስ፣ እያየህ ያለኸው በሺዎች የሚቆጠሩ የድህረምረቃ ትምህርት ቤቶች ኃጢአቶችን በሰዋሰዋዊ ትምህርት ዕውቀት እግዚአብሔርን በማወቅ ሲታገሉ?

አንዳንዶቻችሁ፣ ‹‹ለካስ፣ ብዙዎች በቴኦሎጂ ዶክትሬት የጫኑቱ፣ ብዙም ካልተማሩቱ እኩል ዝሙት ይሠራሉ›› ትሉ ይሆናል፡፡ እኔ እንደውም፣ ‹‹ምናልባት ሳይበልጡ አይቀሩም›› ነው የምለው፡፡ ግን ለምንድነው በቴኦሎጂ ዶክትሬት የጫኑ ሰዎች የሚዘሙቱት? እግዚአብሔርን ስለማያውቁ ነው፡፡

ቴኦሎጂን በቀን ለ10 ሰዓታት ለአርባ ዓመታት ያህል ታጠና ይሆናል፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ውበት እና ሁሉን የሚያረካ መሆኑን – የሕይወትህም ከፍተኛው ውድ እንቁ እንደሆነ አድርገህ ላታውቀው ትችላለህ፡፡ ዲያብሎስ እግዚአብሔርን የሚያውቀውን ያህል ለማወቅ ግድ የሚለው ማነው? እርሱ እያንዳንዱን ሰው ይጠላል፡፡ ስለእግዚአብሔር ያለው ዕውቀት ሰዎችን እንዲጠላ ረድቶታል፡፡

እግዚአብሔርን ስለማወቅ እያወራን ያለነው በ1ኛ ተሰሎንቄ ተንተርሰን ነው፡፡ እነርሱ እግዚአብሔርን አያውቁትም፡፡ እግዚአብሔርን በእግዚአብሔርነቱ አያውቁትም፡፡ ነፍሳችን የተፈጠረችው ማለቂያ የሌለው ጥቅሙን፣ ፍጻሜ የሌለው ውበቱን፣ ፍጻሜ የሌለው የሕይወት አርኪነቱን ተጠቃሚ እንድትሆን መሆኑን አያውቁም፡፡ በቀኙ የሚገኙ ብዙ ደስታዎች፣ በመገኘቱም የሚገኙ ብዙ ዘላለማዊ ሐሴቶች፣ ፍቅረኛሞች ተነፋፍቀው ሲገናኙ ከሚያገኙት ደስታ ይልቅ አስር ሺህ ጊዜ ይበልጣል፡፡ 

ይህን ካወቅህ፣ ኃጢአት በሕይወትህ ላይ ያለውን የገዥነት አቅም ያጣል፡፡

------------------------------------------
(ትምህርቱ ጠቅምዎታል? እንግዲያውስ ላይክ ያድርጉ፣ ጌታ ይባርክዎ!) 

 (John Piper. http://www.desiringgod.org/sermons/why-phds-in-theology-commit-adultery. March 19, 2015)

No comments:

Post a Comment