ዲቮሽን ቁ.197/07፣ ሐሙስ፥ መጋቢት 17/07 ዓ.ም.
(በፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)
(በፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)
በረከትና
መርገም – ከከተማ እስከ ገጠር!
የአምላክህንም የእግዚአብሔርን ቃል ብትሰማ እነዚህ በረከቶች ሁሉ ይመጡልሃል
ያገኙህማል። በከተማ
ቡሩክ ትሆናለህ፥ በእርሻም ቡሩክ ትሆናለህ። …ነገር ግን የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል
ባትሰማ፥ ዛሬም ያዘዝሁህን ሥርዓቱንና ትእዛዙን ሁሉ ባትጠብቅ ባታደርግም፥ እነዚህ መርገሞች ሁሉ ይመጡብሃል ያገኙህማል። በከተማ
ርጉም ትሆናለህ፥ በእርሻም ርጉም ትሆናለህ (ዘዳ 28)።
ዘዳግም ምዕራፍ 28 መልዕክቶች ሁሉ አቢይ መልዕክት ሆኖ ይገኛል – በረከት
ወይም መርገም፡፡ ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ ያሉ ስድሳ ስድስቱ ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ የመልዕክታቸው ዋና ጭብጥ በዘዳግም 28 ዙሪያ
የሚያጠነጥን ነው – በረከት ወይም መርገም!
ወገኖች ሆይ፣
የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ቃል መስማት፣ ሥርዓቱንና ትእዛዙን ሁሉ መጠበቅና ማድረግ የእግዚአብሔርን በረከቶች ሁሉ የሚያመጣ
ሲሆን፣ ቃሉን አለመስማት፥ ሥርዓቱንና ትእዛዙን ሁሉ አለመጠበቅ አለማድረግም፥ መርገሞችን ሁሉ የሚያስከትል እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ታውቃላችሁ፣ በረከትና
መርገም እንደ 'ራዳር' ናቸው! በረከትና መርገም እንደ 'ራዳር' የገባንበት ገብተው የወጣንበት
ወጥተው ፈልገው ያገኙናል፣ ካለንበት ቦታ
ተከትለው ይመጡልናል አሊያም ይመጡብናል!
ታውቃላችሁ፣ በረከትና
መርገም እንደ 'ራዳር' ናቸውና አናመልጣቸውም! ቃሉን ስንታዘዝ የእግዚአብሔር በረከቶች የገባንበት ገብተው ፈልገው ያገኙናል፣ የወጣንበት
ወጥተው ይገናኙናል! ቃሉን ካልታዘዝን መርገሞቹ
ሁሉ የገባንበት ገብተው ፈልገው ያገኙናል፣ የወጣንበት ወጥተው ይገናኙናል!
ታውቃላችሁ፣ በረከትና
መርገም እንደ 'ራዳር' ናቸውና ከተማም ብንገባ፣ ገጠርም ብንሄድ አናመልጣቸውም! ነጋዴም ብንሆን፣ ገበሬም ብንሆን፣ መሐይምም ብንሆን
ምሁርም ብንሆን፣ ድሃና ሀብታምም፣ ትልቅም ትንሽም ከእግዚአብሔር ራዳር ልናመልጥ አንችልም!
------------------------------------------
(ትምህርቱ ጠቅምዎታል? እንግዲያውስ ላይክ ያድርጉ፣ ጌታ
ይባርክዎ!)
No comments:
Post a Comment