ዲቮሽን 181/07፥ ማክሰኞ፥ መጋቢት 1/07 ዓ.ም.
(በፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)
(በፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)
ዘፈቀደ ሕይወት!
በዚያን ዘመን በእስራኤን ዘንድ ንጉስ አልነበረም፥ ሰው ሁሉ በፊቱ መልካም መስሎ የታየውን ያደርግ ነበር (መሳ 21፡25)፡፡
ከኢያሱ ሞት በኋላ የእስራኤል ሕዝብ ለአራት ትውልድ ያህል ማለትም ለአራት መቶ ዓመታት ያህል ጠቅላይ መሪ ወይንም ንጉስ አልነበረውም፡፡ በእነዚህ ሁሉ ዓመታት ሰው ሁሉ በፊቱ መልካም መስሎ የታየውን ያደርግ ነበር፡፡
ወገኖች ሆይ፥ የእግዚአብሔር ሕዝብ በእግዚአብሔር ሕግና ስርዓት ሊወጣና ሊገባ፥ እንደ ቃሉ ሊኖር ሊመላለስ ይገባል! ይህ ስርዓት ተጥሶ የእግዚአብሔር ሕዝብ በመሰለው መንገድ ቢወጣ ቢገባ፥ ዘፈቀደ ሕይወት ቢኖር ቢመላለስ አደጋ ይመጣል!
ታውቃላችሁ፥ የአማኞች የሕይወት ስታንዳርድ የመንግስታቱ ድርጅት ሕገ መንግስት ሳይሆን፥ የነገስታቱ ንጉስ ሕገ መጽሐፍ ቅዱስ ነው!
ታውቃላችሁ፥ የአማኞች የሕይወት ስታንዳርድ መለኪያ ስፖርት ስታቲስቲክ ሳይሆን የእግዚአብሔር ቃል ነው!
ታውቃላችሁ፥ የአማኞች ሕይወት ስታንዳርድ አፍሪካና ኤዥያ፥ ዩሮፕ አሜሪካ ሳይሆን መንግስተ ሰማያት ነው!
ወገኖች ሆይ፥ አማኞች በዚህች ምድር የሚኖሩት ወቅቱ እንደፈቀደ፥ የጊዜው ሁኔታ፥ ፓርቲ ፖለቲካ እንደፈቀደ ሳይሆን፥ ጌታ እንደፈቀደ ነው!
ወገኖች ሆይ፥ የአማኞች ኑሮ፥ የክርስቲያኖች እምነት፥ የጻድቃን ሕይወት፥ ተግባር ምግባራቸው፥ እንደ አሕዛብ ሁሉ፥ እንደ ዓለማዊያን ሁሉ፥ እንዳልዳኑት ሁሉ፥ እንደ ምድር ወገኖች ሳይሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ልጆች፥ እንደ መንግስቱ ዜጎች በመንፈስ የሚመሩ መሆን ይገባቸዋል!
ታውቃላችሁ፥ የእግዚአብሔር ሕዝብ እንደመሳፍንቱ ዘመን ሁሉ በመሰለው ሕይወት፥ በመሰለው ትምህርት፥ በመሰለው ስብከት፥ በመሰለው ትንቢት፥ በመሰለው ባህል፥ በመሰለው ፋሽን…የሚሄድ ከሆነ አደጋ ይመጣል!
የእግዚአብሔር ሕዝብ በመንፈስ ተሞልቶ በመንፈስ የሚመራው መንፈሳዊ መሪ ካጣ፥ ሕዝቡ መረን ይወጣል! በእውነትና መንፈስ ሕዝቡን የሚመራ እውነተኛ መሪ ከታጣ፥ በሰው ፍልስፍና በመሰለው መንገድ ሕዝብን የሚመራ መሪ ከተተካ ሕዝቡን አስከትሎ መረን ይለቅቀዋል!
No comments:
Post a Comment