Monday, February 23, 2015

የምድረበዳው ምሪት!



ዲቮሽን .166/07፣ ሰኞ የካቲት 16/07 ..
(
በፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)


የምድረበዳው ምሪት!

አምላክህ እግዚአብሔር ይፈትንህ ዘንድ፥ በልብህም ያለውን ትእዛዙን ትጠብቅ ወይም አትጠብቅ እንደሆነ ያውቅ ዘንድ፥ ሊያስጨንቅህ በእነዚህ በአርባ ዓመታት በምድረ በዳ የመራህን መንገድ ሁሉ አስብ(ዘዳ 82)

እምነታችንን ሊያጠነክር እግዚአብሔር አንዳንዴ በምድረ በዳ ሊመራን ይችላል፡፡ ወዳጄ ሆይ፣ ምድረበዳ ምን እንደሆነ ያውቃሉ? ምንም በሌለበት፣ የማይወደድ፣ እና የማይመረጥ ነገር ነው! አየሩ፣ አካባቢው፣ ሁኔታው፣ ዙሪያ ገባው ሁሉ የማይመች፣ የሚያሰለች፣ የሚያስለቅስና የሚያስነክስ ነው!

ወገኖች ሆይ፣ እግዚአብሔር በምድረበዳ ሲያሳልፈን ሊፈትነን ነው፡፡ የፈተናውም ምክንያት ከሁኔታዎች ይልቅ እርሱን አስበልጠን እንወድደው እንደሆነ ለማወቅ ነው፡፡ በአጠገባችን ከጌታ በስተቀር ሌላ ምንም ነገር ባይኖር፣ በእርሱ መገኘት ብቻ እንደሰት እንደሁ ለማወቅ ነው፡፡ ሁሉ ነገር ጠፍቶ፣ ቃልና ሥርዓቱን በልባችን ይዘን የእውነት ለመደሰት እንችል እንደሁ ለማወቅ ፈልጎ ነው፡፡

ታውቃላችሁ፣ የእግዚአብሔርን ሕዝብ፣ ከምድረበዳው በኋላ የተስፋዪቱ ምድር ትጠብቃለችና፣ የምድረበዳው ምሪት ወደ ተስፋዪቱ ምድር የሚያደርስ መንገድ ነው!

ታውቃላችሁ፣ የምድረበዳው ምሪት ፍጻሜው ያማረ፣ የድልና ስኬት፣ የመውረስ ማሸነፍ ነው!

ታውቃላችሁ፣ የምድረበዳው ምሪት፣ ሕመምናጭንቀት፣ ሐዘንናለቅሶ ቢበዛበትም፣ ፍጻሜው ያማረ፣ የድልናስኬት፣ የመውረስማሸነፍ፣ የመጠርመስየመንገስ ነው!

ወዳጄ ሆይ፣ የምድረበዳዎ ምሪት የረዘመ ቢመስልዎትም ማብቃቱ አይቀርም፡፡ ነገር ግን፣ ወዳጄ፣ ምድረበዳዎ አልቆ፣ የተዘጋጀልዎን በረከት ሲወርሱ ጌታን እንዳይረሱ፡፡ እርስዎን ለማስተማር በምድረ በዳው መንገድ የመራዎትንና እነዚያን ተአምራቶች ያሳየዎትን ነገር ሁሉ አስብ!
--------------------------------
(ትምህርቱ ጠቅምዎታል? እንግዲያውስ ላይክ ያድርጉ፣ ጌታ ይባርክዎ!)

No comments:

Post a Comment