Tuesday, February 24, 2015

ጽኑ ግንብ!

ዲቮሽን .167/07፣ ማክሰኞ የካቲት 17/07 ..
(
በፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)


ጽኑ ግንብ!

አንተ መጠጊያዬ፣ ከጠላትም የምተገንብህ ጽኑ ግንብ ሆነኸኛልና (መዝ 61፡3)

ሃሌሉያ! ደምን ለማፍሰስ እግራቸው ፈጣን ከሆኑ ጠላቶቼ አድነኸኛልና አመሰግንሃለሁ! ጥፋትና ጕስቍልና በመንገዳቸው ካለ ከአሳዳጆቼ፣ ከአጥፊ፣ ከጠላቶቼ ጠብቀኸኛልና አመሰግንሃለሁ!

አምላኬ ሆይ፣ አንተ መጠጊያዬ፣ ከጠላትም የምተገንብህ ጽኑ ግንብ ሆነኸኛልና አመሰግንሃለሁ! ቀስተኛውን ሰብረህ፣ ጦረኛውን መትተህ፣ ሰልፈኛ በትነህ አድነኸኛልና አመሰግንሃለሁ! የኔ ልዑል፣ የኔ ጠባቂ፣ የኔ ጋሻና መከታዬ ሆይ፣ ነፍሴን ከሞት፣ እግሬን ከመሰናከል አድነኸኛልና አመሰግንሃለሁ!

አንተ ጽኑ ግንብ የሆንኸኝ አምላኬ ሆይ፣ ከአዳኝ ወጥመድ፣ ከሚያስደነግጥ ነገር፣ ከጠላት ንክሻ፣ ከቀስት ከፍላጻ፣ ከአደጋ ከመቅሰፍት፣ ከአጋንንት ከጋኔን፣ ከሸማቂ ጠላት፣ ከድንገተኛ ጥፋት፣ ከማንኛውም ክፉ ነገር ጠብቀኸኛልና አመሰግንሃለሁ!

አንተ መጠጊያዬ፣ ከጠላትም የምተገንብህ ጽኑ ግንብ ሆይ፣ ውኆች ሲናወጡ፣ ማዕበሉ ሲቆጣ፣ በወጀብ በአውሎንፋስ አልተለየኸኝምና አመሰግንሃለሁ!

ሃሌሉያ! ሊውጠኝ ፈልጎ ዙሪያዬን ከሚዞር ከጨካኝ አንበሣ፣ ነጥቆ ከሚበላ ከአውሬው ከተኩላው፣ ከእባቡና ዘንዶው ጠብቀኸኛልና አመሰግንሃለሁ!

አምላኬ ሆይ፣ ጠላቴን አሳድደህ ስለምትመታው፣ በአጠገቤ ሺህ፣ በቀኜ አሥር ሺህ፣ ከፊት ከኋላዬ ሺህ ጊዜ ሺህ፣ እልፍ ጊዜ እልፍ ጠላት መትተህ ስለምትጥል አመሰግንሃለሁ!

አምላኬ ሆይ፣ አንተ ጽኑ ግንብ በጠላት ፊት ተስፋዬም ሆነኸኛልና፣ በአንተ መጠጊያዬ፣ ከጠላትም የምተገንብህ ጽኑ ግንብ ሆነኸኛልና አመሰግንሃለሁ!

አምላኬ መጠጊያዬና ኃይሌ፥ በሚያገኘኝ በታላቅ መከራም ረዳቴ ነህና፣ ምድር ብትነዋወጥ፥ ተራሮችም ወደ ባሕር ልብ ቢወሰዱ አልፈራም! ለምን ብዬ? ሃሌሉያ!
--------------------------------

(ትምህርቱ ጠቅምዎታል? እንግዲያውስ ላይክ ያድርጉ፣ ጌታ ይባርክዎ!)

No comments:

Post a Comment