ዲቮሽን
ቁ.153/07፣
ማክሰኞ፥
የካቲት
3/07 ዓ.ም.
(በፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)
(በፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ)
ሕይወትና ጥፊ!
ድካምንና ጣርን
አይ ዘንድ ዘመኔም በእፍረት ታልቅ ዘንድ ስለ ምን ከማኅፀን ወጣሁ? (ኤር 20፡18)።
በሕይወታችን ከሚያጋጥሙ
ማዕበሎችናና መሰናክሎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ፈተናዎች የተነሣ መራራ እንባ የምናለቅባቸው ጊዜዎች አሉ፡፡ ከእነዚህ የሕይወት ገጠመኞች
የተነሣ አንዳንዴ በሕይወት መኖራችን ቅር የሚለን ጊዜም አለ፡፡ ምነው ባልተፈጠርኩ ኖሮ! ምነው በእናቴ ማሕጸን ውሃ ሆኜ በቀረሁ
ኖሮ! እንላለን፡፡
ወገኖች ሆይ፣
ይህ ዓይነቱ ምኞት አዲስ አይደለም! በሕይወት ፈተናዎች የተነሣ ተስፋ መቁረጥ በእኛ ላይ ብቻ የተጀመረ
አይደለም፡፡ ጻድቁ ኢዮብም የተወለደበትን ቀን ተራግሟል፣ ነቢዩ ኤርሚያስም በመወለዱ ተጸጽቷል!
ዳዊትም ስለተወለደበት ቀን በጸጸት ዘምሯል!
ታውቃላችሁ፣ ሕይወት በአዋላጆች ጥፊ ትጀምራለች! የእናታችንን ማሕጸን ለቅቀን ወደዚህች ምድር ገና ከመምጣታችን አዋላጆቻችን ጀርባችን ላይ በጥፊ ይሉናል፡፡ ያኔ እኛ ማንቀስ እንጀምራለን፡፡
ታውቃላችሁ፣ እኛ ማልቀስ ስንጀምር
አድማጮቻችን በደስታ ይዘልላሉ! እኛ እያለቀስን እነርሱ እልል ይላሉ! የመሞቻ ሰዓታችን ደርሶ እኛ በተራችን ፈገግ ስንል እነርሱ
ያለቅሳሉ! እኛ ዝም ስንል እነርሱ እንባቸውን እያዘሩ፣ ከመሬት ላይ ወድቀው እየተንፈራፈሩ መራራ ለቅሶ
ያለቅሳሉ!
ታውቃላችሁ፣ ስንወለድ ጥፊ ካልቀመስን
ሕይወት ትክክል አይሆንም፡፡ ይህ ካልሆነ ማልቀስ የለም፡፡ ለቅሶያችን በሕይወት
ለመኖራችን ምልክት ነው! ታውቃላችሁ፣ ማልቀስ ሕይወት መሥራት ለመጀመሩ ምልክት ነው!
ወገኖች ሆይ፣
ሕይወትና ለቅሶ የማይነጣጠሉ መንትዮች ናቸው! ሕይወትና
ለቅሶ ገና ስንወለድ ጀምሮ አብረውን የመጡ መሆናቸውን አንርሳ፡፡ የሰው ልጅ ሕይወትን እያለቀሰ ጀምሮ እያለቀሰ እንደሚያድገው ሁሉ፣ መከራና ችግር በሕይወታችን ቢያጋጥሙንም ማደጋችንን እንቀጥል!
ወገኖች ሆይ፣
ሰው ሲሞት አጋጥሟችኋል? ሰው ሊሞት ሲቃረብ ማልቀስ ያቆማል! ሰው ሲሞት ፈገግ እያለ ይሞታል! እያለቀሰ ተወልዶ፣ እያለቀሰ አድጎ
ሲሞት ግን ፈገግ እያለ ይሞታል፡፡ ወገኖች ሆይ፣ ማልቀስ የሚቆመው ስንሞት ብቻ ነውና፣ በዚህች ምድር ላይ የሚያስለቅሱ ነገሮች
ሲያጋጥሙ ቻል እናድርገው! በርታ እንበል!
ወገኖች ሆይ፣ በማልቀስ የሚጨምረው ነገር የለምና በጌታ እንጽናና! ለቅሷችንን ወደ ደስታ ሊቀይር የሚችል ጌታ አለና ልባችንን በጌታ እንደግፍ! በጌታ ልባችን ይጽናና! በለቅሶ ሸለቆ ውስጥ በወሰነው ሥፍራ የሕግ መምህር በረከትን ይሰጣልና፣ ልባችን በጌታ ይጽናና! (መዝ 84፡6)፡፡
----
በዚህ ብሎግ የሚከታተሉ እስከዛሬ ድረስ 4,056 አንባቢዎች የጎበኙ መሆናቸውን መረጃው ያመለክታል፡፡
ሆኖም፣ እስከዛሬ አንድም ሰው ትምህርቱ እየጠቀመው ይሆን ወይም አልጠቀመው እንደሆነ መረጃ አልሰጡኝም፡፡ ይህም ጉዳይ ጥያቄ አጭሮብኛል፡፡
ውድ አንባቢዎች ሆይ፣ እስኪ ድምጻችሁን ልስማው? ሁሉ ደህና ነው ወይ?
No comments:
Post a Comment