Thursday, February 5, 2015

ማስታወቂያ Announcement! I will be out of Addis preaching on a 4-day conference.

የተወደዳችሁ የዕለታዊ ዲቮሽን ተከታታዮች፣ ሰላም ለእናንተ ይሁን!

ለአራት ቀን አገልግሎት ወደ ክልል ወጥቻለሁ፡፡ ከቦታው ኔትወርክ የማይገኝበት ስለሆነ፣ ጌታ ቢፈቅድ ከነገ ጠዋት ጀምሮ እስከ ሰኞ ድረስ ያሉ ዲቮሽኖችን፣ በፌስቡክ ታይምላይኔ ላይ በየቀኑ በሚያስተላልፋቸው ጠንካራ መልዕክቶቹ የምናውቀው ወንድም ጌታሁን ሐሌፎም ያገለግለናል፡፡ ሁላችንም፣ ጠንካራ ተሳትፎ በማድረግ ታበረታቱት ዘንድ በጌታ ፍቅር እጠይቃለሁ፡፡

የናንተ ላይክና ሼር ማድረግ መልዐክቱን ከርቀት ለሚያስተላፍ ሰው ምን ያህል እንደሚያስደስት ታውቁ የለ! በሰው ፊት ቆመን ስናገለግል፣ ‹‹አሜን ነው?›› ስልን ሕዝቡም ‹‹አሜን›› ብሎ ሲመልስ እንደሚያስደስት ሁሉ፣ ላይክና ሼር ስታደርጉ፣ ትምህርቱን መከታተላችሁን ያሳያልና እባካችሁን ተጋባዥ እንግዳዬን ላይክና ሼር በማድረግ እንዲበረታ አድርጉልኝ፡፡

ስለጌታሁን ሐለፎም ማንነትና አገልግሎት ጥቂት እነግራችኋለሁና በጉጉት ጠብቁኝ፡፡ ጌታ ይባርካችሁ፡፡

በተጨማሪም፣ በዚህ ብሎግ ለአራት ቀናት ፖስቶች ላይኖሩ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን የምችለውን ሁሉ አደርጋለሁ፡፡ እባካችሁን፣ እስኪ ለአራት ቀናት ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ፖስቶች ባይኖሩ፡ በሁሉም አህጉራት የምትገኙ ወገኖች በዚህ ብሎግና ጎግል ፕላስ ግቡና እስከዛሬ በተማራችሁትወይንም በግል ጌታ ያስተማራችሁን ነገር በማካፈል፣ ብሎጉ ክፍት እንዳይሆን ተወያዩበት፡፡

የናንተው አገልጋይ፣

ፓ/ር ተስፋሁን ሐጢያ

No comments:

Post a Comment